136 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የፈፀመው በዕድሜ ይፍታህ ተቀጣ

136 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች የፈፀመው

የፎቶው ባለመብት, POLICE HANDOUT

159 ወሲባዊ ጥቃቶችን በማድረስ የተከሰሰው ግለሰብ በዕድሜ ይፍታህ ተቀጥቷል፤ ዳኛውም የመፍታት ተስፋው የመነመነ ሲሉ ገልፀውታል።

ሬይናርድ ሲናጋ የተሰኘው ግለሰብ የእንግሊዟ የማንችስተር ከተማ ነዋሪ 48 ወንዶችን በመድኃኒት በማደንዘዝ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰድ ወሲባዊ ጥቃት አድርሷል፤ ድርጊቱን በካሜራም ቀርጿል።

ፖሊስ የ36 ዓመቱ ሲናጋ ቢያንስ 190 ሰዎችን ዒላማ እንዳደረገ ማስረጃ አለኝ ብሏል።

የዕድሜ ይፍታህ ፍርድ የበየኑበት ዳኛ ግለሰቡ ቢያንስ ለ30 ዓመታት ከርቸሌ እንዲከርም ይሁን ብለዋል።

ግለሰቤ እስኪረድበት ድረስ ማንነቱ በመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንዳይሆን ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዳኛው ፍርዱን ካስተላለፉ በኋላ ማንነቱ ይፋ እንዲሆን ተደርጓል።

የድህረ-ምረቃ ተማሪው ግለሰብ አሁን ከተበየነበት ፍርድ ቀድሞ በሌሎች ሁለት ጥፋቶች 20 ዓመታት ተፈርዶበት እሥር ቤት ውስጥ ይገኛል።

ከኢንዶኔዥያ የመጣው ግለሰቡ በአንድ ጊዜ አራት ክሶችን ይከታተል ነበር። ፍርደኛው 48 ተጠቂዎች ላይ 136 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች፣ 8 የአስገድዶ መድፈር ሙከራዎች፣ 14 ወሲባዊ ፈጽሟል በሚል ተከሶ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

መርማሪዎች ሌሎች 70 ተጠቂዎች ወደ ፖሊስ ባለመቅረባቸው ምክንያት ክስ መመሥረት አልቻልንም እንጂ ግለሰቡ ተጨማሪ የሚጠረጥርባቸው ወንጀሎች አሉ ይላሉ። በግለሰቡ ጥቃት ደርሶብናል ያሉ ለፖሊስ አቤት እንዲሉም ጥሩ አቅርበዋል።

ዳኛ ሱዛን ጎዳርድ 'ይህ ሠይጣናዊነት የተጠናወተው ወሲባዊ ጥቃት አድራሽ በርካታ ወጣት ወንዶች ላይ ወንጀል ፈፅሟል' ሲሉ ተደምጠዋል።

ግለሰቡ ጥቃት የሚያደርስባቸው ወንዶች ከምሽት ክለቦች ሲወጡ ይጠብቅና ከመረዛቸው በኋላ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰድ ራሳቸውን በሳቱበት ወሲባዊ ጥቃት ያደርስባቸዋል ይላል የፖሊስ መዝገብ። ብዙዎች ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶች ከነቁ በኋላ ምን እንደተፈጠረ እንደማያስታውሱ አስረድተዋል።

ምንም ዓይነት ወንጀል አልፈፀምኩም የሚለው ግለሰብ ወሲብ የፈፀምኩት በግለሰበቹ ፍቃድ ነው፤ ቀረፃውንም ቢሆን እንደዚሁ ሲል ተከራክሯል። ፍርድ ቤት ግን ማስተባበያውን ውድቅ አድርጎታል።

ሊድስ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የዶክትሬት ድግሪውን ይከታተል የነበረው ሲናጋ ለመጀረመሪያ ጊዜ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ሰኔ 2017 ነበር። ከሳሾቹ ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት እያደረሰባቸው የነቁ ግለሰቦች ናቸው።

ግሰለቡ በእንግሊዝ ሕግ መዝገብ በጣም አሰቃቂ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመ ተብሏል።