ስሪ ላንካ በመንትያ ቁጥር ክብረ ወሰን ለመስበር ያደረገችው ሙከራ ከሸፈ

ስሪላንካዊያን መንትዮች Image copyright AFP

ስሪ ላንካ በመንትያ ቁጥር ክብረ ወሰን ለመስበር ያደረገችው ሙከራ ሳይሳካላት ቀርቷል።

በሲሪ ላንካ የሚገኙ መንተዮች በሙሉ በመዲናዋ ኮሎምቦ በአንድ ስታዲየም ውስጥ እነዲሰባሰቡ ጥሪ ተደርጎላቸው ነበር። ዓላማውም በፈረንጆቹ 1999 ላይ በታይዋን ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ለመስበር ነበር።

ታይዋን 3 ሺ 961 መንትያዎችን፣ 37 በአንዴ ሦስት ሆነው የተወለዱ መንትያዎች እንዲሁም 4 ሆነው የተወለዱ አራት መንትያዎችን በአንድ ስፍራ በማሰባሰብ በዓለም የድንቃ ድንቅ መንዘገብ ላይ ተመዝግባ ትገኛለች።

ሰሪ ላንካውያኑ በርካታ መንትያዎችን በአደባባይ ጠርተው ለዕይታ ቢያበቁም በታይዋን የተያዘውን ሪኮርድ ግን መስበር አልተቻላቸውም።

ጥሪውን ተከትሎ ከተጠበቀው በላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ መንትዮች ተገኝተዋል። ታዲያ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ መስፍርቶችን ለማሟላት እና የልደት የምስክር ወረቀቶችን ለማረጋገጥ በቂ ጊዜ ማግኘት አልተቻለም።

Image copyright AFP

መንትዮቹ የተሰባሰቡት አገራቸውን በዓለም ክብረወስን ለማስመዝገብ ነበር።

Image copyright Reuters
Image copyright Reuters

አዘጋጆቹ 5 ሺህ መንትያዎችን በመመዝገብ ክብረወሰኑን ለመስበር ግብ አስቀምጠው ነበር።

Image copyright Reuters

ኤኤፍፒ እንደዘገበው ከሆነ ግን 14 ሺህ ሰዎች በማስታወቂያው መሰረት ለዝግጅቱ ተመዝግበው ነበር።

Image copyright AFP
Image copyright EPA
Image copyright Reuters

መንትዮቹም በድጋሜ መጥተው ለመመዝገብና በታይዋን ተይዞ የሚገኘውን ክብረወሰን ለመስበር ሁሌም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ