በኮንጎ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ከቀብር ሲመለሱ ከነበሩት 15ቱ ሞቱ

እቃ እና ሰዎች ማመላለሻ ትልቅ ጀልባ Image copyright Getty Images

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች ሞቱ።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምዕራባዊ አካባቢ በሚገኝ ሐይቅ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች መሞታቸውን ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል የአካባቢውን ከንቲባ ጠቅሶ ዘግቧል።

በማይ ንዶምቤ ሐይቅ ባሳለፍነው ሰኞ በደረሰው በዚህ አደጋ በርካታ ሰዎች መጥፋታቸውም ታውቋል።

ጀልባዋ ከከተማዋ 35 ኪሎ ሜትር ከሚርቅ ሥፍራ ከቀብር ሥነ ሥርዓት በመመለስ ላይ የነበሩ 30 የሚሆኑ ሰዎችን አሳፍራ ነበር።

የአደጋው ምክንያት አልታወቀም።

በጥምቀት በዓል ጎንደር እና ሐረር የተከሰተው ምንድነው?

እውን አዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር?

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር 400 ሰዎችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ በዚሁ ሐይቅ ሰምጣ ቢያንስ 45 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።

አብዛኞቹ ደመወዛቸውን ለመቀበል ለመሄድ ተሳፍረው የነበሩ መምህራን ነበሩ።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጀልባዎች ከአቅም በላይ በመጫናቸውና በቂ ጥገና ስለማይደረግላቸው ተመሳሳይ አደጋ በተደጋጋሚ ያጋጥማል።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ጀልባ ሰጥሞ 34 ሰዎች ሞቱ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ