ሶማሊያ የዓለማችን ሙስና የተጠናወታት አገር ተባለች

ዶላር Image copyright Getty Images

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለማቀፍ ድርጅት ሶማሊያ ሙስና የተጠናወታት አገር ናት ሲል ፈረጃት።

ሙስናን የሚዋጋው ድርጅት ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶሪያ የዓለማችን ሙሰኛ አገራት ናቸው ሲል በቅድመ ተከተል አስፍሯቸዋል። ሙስና የራቃቸው አገራት ዝርዝር ላይ ደግሞ ኒውዚላንድ፣ ዴንማርክ፣ ፊልላንድ፣ ሲንጋፖር እና ስዊድን ተቀምጠዋል።

ከሰሃራ በታች የሚኙ አገራት ሙስና የተንሰራፋባቸው አገራት መሆናቸውን ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የገለጸ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ከ180 አገራት 96ኛ ደረጃን ይዛለች።

የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች

ቤት ለመከራየት ግማሽ ሚሊዮን ብር ቀብድ የሚጠየቅባት ከተማ

ድርጅቱ አገራት ሙስናን በመዋጋት ረገድ ያሳዩት ለውጥ እጅግ ዘገምተኛ ነው ብሏል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ሙስናን ማቃለል ከቻሉ ጥቂት አገሮች መካከል ግሪክ እና ሰሜን አውሮፓዊቷ ኢስቶኒያ ተጠቃሽ ሆነዋል።

ጥናቱን ይፋ ያደረገው ቡድን እንደሚለው ከሆነ ሙስና በስፋት የሚነሰራፋው ለምርጫ ቅስቀሳ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ፈሰስ ሲደረግ እና መንግሥታት ለባለጸጎች ብቻ ጆሯቸውን ሲሰጡ ነው።

180 አገራትን ያሳተፈው ጥናት የተለያዩ መለኪያዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለአገራቱ ከዜሮ እስከ 100 ድረስ ነጥብ ሰጥቷል። ዜሮ ማለት እጅግ ሙስና የበዛበት አገር ሲሆን 100 ደግሞ ከሙስና የጸዳ ማለት ነው።

"ኢስላማዊ ባንክ ለኢትዮጵያ ምን ይፈይዳል?"

ኒው ዚላንድ እና ዴንማርክ 87 ነጥብ ሲያስመዘግቡ፤ ሱማሊያ 9፣ ደቡብ ሱዳን 12 እና ሲሪያ ደግሞ 13 አስመዝገበዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ ከ 100 ሀገራት ተወዳድራ ከአጠቃላይ 100 ነጥብ 37 ማግኘት ችላለች።

በዚህም ከጠቅላለው 180 አገራት ሁለት ሶስተኛው ያገኙት ነጥብ ከ50 በታች ሆኗል።

ተያያዥ ርዕሶች