ቻይና ተላላፊውን በሽታ ለመግታት በ6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ ነው

በ6 ቀናት የሚጠናቀቀው የቻይና ሆስፒታል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በ6 ቀናት የሚጠናቀቀው የቻይና ሆስፒታል

የቻይናዋ ዉሃን ግዛት በ6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ መሆኗን አስታውቃለች።

የውሃን ግዛት ሆስፒታሉን በአስቸኳይ የምትገነባው ቻይና ውስጥ ተከስቶ መዳረሻውን ብዙ የዓለም አገራት እያደረገ ያለውን የኮሮና ቫይረስን ለማከም ነው።

ቫይረሱ በግዛቷ ከተከሰተ ወዲህ 830 ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው ታውቋል። 41 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል።

11 ሚሊዮን ዜጎች በሚኖሩባት ውሃን ግዛት በቫይረሱ በታመሙ ታካሚዎች ሆስፒታሎች ተጨናንቀው ከፍተኛ የመድኃኒተ እጥረትም ተከስቷል።

የአገሪቱ ብሔራዊ ብዙሃን መገናኛ እንደዘገበው አዲሱ በ6 ቀናት ውስጥ የሚጠናቀቀው ሆስፒታል 1 ሺህ የመኝታ አልጋዎች እንዲኖሩት ተደርጎ የሚሰራ ነው።

የተለቀቁ የተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ቆፋሪ ማሽኖች በቦታው የደረሱ ሲሆን በ25 ሺህ ሄክታር ላይ የሚያርፈውን ሆስፒታል መቆፈር ጀምረዋል።

አሁን የሚሰራው ሆስፒታል በ2003 (እ.አ.አ) የሳርስ ቫይረስን ለማከም በቤጂንግ ከተሰራው ሆስፒታል ጋር ተመሳሳይ ነው ተብሏል።

Image copyright Getty Images

እንዴት በ6 ቀናት ብቻ ሆስፒታል መራት ይቻላል?

ይህን ዜና ተከትሎ በርካቶች አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ። "ቻይና እንደዚህ አይነት ወቅታዊ ችግሮችን ለማለፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የምትታማ አይደለችም" በማለት ያንዙንግ ሁዋንግ የተባሉ ዓለም አቀፍ የጤና ሞያተኛ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

እርሳቸው እንደሚሉት በቤጂንግ በ2003 የተሰራው ሆስፒታል በሰባት ቀናት ነበርና የጠተናቀቀው ይህኛውን ሆስፒታል በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ የሚያስቸግር ነገር የለም።

"ውሳኔው ከላይ ካሉት ባለስልጣናት የተሰጠ በመሆኑ የቢሮክራሲና የፋይናንስ ሰንሰለቶች ስለማይኖሩትና ሁሉም አቅርቦቶች በበቂ ደረጃ የሚሟላለት በመሆኑ ሆስፒታሉ በተባለው ጊዜ ይጠናቀቃል" የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት መሃንዲሶቹ ከመላው ቻይና ተሰባስበዋል። ቻይና በምህንድስናው ዘርፍ እጅግ የተዋጣላት ነች፤ ምናልባት ምዕራባዊያን ላያምኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ዕውን መሆኑን ለማረጋገጥ 6 ቀናትን ብቻ ይታገሱ በማለት የቻይናዊያንን የምህንድስና ፍጥነት አድንቃዋል።

ይህ ከሆነ በኋላ ዉሃን ግዛት መድሃኒቶችን ከጎረቤት ሆስፒታል ታስመጣለች ወይም ደግሞ ቀጥታ ከፋብሪካዎች ታስመጣለች።

ሳርስ ቫይረስ ሲከሰት ምን ነበር የሆነው?

በ2003 በቻይና ተከስቶ የነበረውን የሳርስ ቫይረስ ለማከም ሲባል ዢያኦታንግሻን ሆስፒታል በቤጂንግ ተገነባ። የዓለማችን ፈጣኑ ግንባታ በመሆን በሰባት ቀናት ብቻ ነበር የተገነባው። በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ 4 ሺ የሚሆኑ ሙያተኞች ሌትና ቀን በስራው ተሳትፈውበታል።

በውስጡ የኤክስሬይ ክፍል፣ የሲቲ ስካን ክፍል፣ ከፍተኛ-እንክብካቤ የሚሰጥበት ክፍልና ላቦራቶሪ ነበረው። እያንዳንዱ ክፍል የራሱ የሆነ የመታጠቢያ ቤት አለው።

በሁለት ወራት ውስጥ ሆስፒታሉ የሳርስ በሽታ በመላ አገሪቱ ከታየባቸው ቻይናውያን መካከል አንድ ሰባተኛ የሚሆኑትን በመፈወስ በህክምና ታሪክ ተዓምር የተሠራበት ነው ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ