ዝነኛዋ ቱኒዚያዊት ጦማሪ በ36 ዓመቷ አረፈች

ዝነኛዋ ቱኒዚያዊት ጦማሪ በ36 ዓመቷ አረፈች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ,

ቱኒዚያዊት ጦማሪ ሊና ቤን ማሄኒ

ዝነኛዋ ቱኒዚያዊት ጦማሪ ሊና ቤን ማሄኒ በ36 ዓመቷ ከዚህ ዓመት በሞት ተለየች።

ሊና የአረብ አብዮትን በዝርዝር መዘገቧ በብዙዎች ዘንድ ዝነኛ አድርጓት ነበር።

ለረዥም ዓመታት ምንነቱ ባልተጠቀሰ ህመም ስትሰቃይ መቆየቷ የተነገረ ሲሆን ዛሬ ጠዋት የህልፈቷ ዜና ተሰምቷል።

የአረብ አብዮት ከመቀስቀሱ በፊት ሊና ወደ ቱኒዚያ ገጠራማ እና የድሆች መንደር በማቅናት የዜጎች ትክክለኛ የኑሮ ገጽታን ለአንባቢዎች ስታቀርብ ቆይታለች።

ሊና የቀድሞ የቱኒዚያ ፕሬዝደንት ቤን አሊ መንግሥት አስተኛ ተቃውሞዎች ሲገጥሙት አንስቶ እስከ የመጨረሻው የመንግሥታቸው ውድቀት ድረስ 'ቱኒዚያን ገርል' በሚለው ድረ-ገጿ ላይ ብዙ መረጃዎችን አጠናቅራ አስቀምጣላች።

ከአረብ አብዮት በኋላም በእንግሊዘኛ፣ አረብኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ የምትጽፋቸው ጽሁፎቿ በቱኒዚያ የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚጠይቁ ነበሩ።

ሊና ባለፉት ሳምንታት በድረ-ገጿ ላይ በቱኒዚያ መዲና የሚገኙ ሆስፒታሎች ያለባቸው የጥራት ጉድለት አስነብባ ነበር።

ሊና እአአ 2011 ላይ የኖቤል ሽልማት እጩዎች መካከል አንዷ እርሷ ነበረች።