የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ ሴናፍ ዋቁማ

ሴናፍ ዋቁማ

የሉሲዎቹና የአዳማ ክለብ ጎል አዳኝ የፊት መስመር ተጫዋች ነች፤ ሴናፍ ዋቁማ። ትውልድና እድገቷ በነቀምት ነው።

ለእግር ኳስ ያላትን ፍቅር ስትገልጽ "ትምህርት ቤት እያለሁ ለኳስ ካለኝ ፍቅር የተነሳ እጫወት የነበረው ከወንዶቹ ጋር ነበር" ትላለች።

ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ለኳስ ከሰጠች በኋላ ነቀምት በሚገኙ የእግር ኳስ ፕሮጀክቶች ውስጥ ታቅፋ ስልጠናዎችን ወስዳለች። ከዚያም በነበራት አቋም ተመርጣ ወደ አሰላ በመሄድ ለአራት ዓመታት ስልጠና ወስዳለች።

"በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"

በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አቃቤ ሕግ አስታወቀ

የሕዝብ እንደራሴዎችን ጎራ አስለይቶ ያሟገተው ሕግ

"የሰዎች አመለካከት ጥሩ አልነበረም" የምትለው ሴናፍ፤ በእግር ኳስ ህይወቷ ማህበረሰቡ ሴቶች እግር ኳስ መጫወታቸውን በበጎ አለመመልከቱ የእግር ኳስ ህይወቷን ፈታኝ አድርጎባት እንደነበረ ታስረዳለች።

"ሴቶች ከቤት መውጣት የለባቸውም የሚል አመለካከት ነበር። እግር ኳስ መጫወት ደግሞ እንደ ሃፍረት ነበር የሚቆጠረው" የምትለው ሴናፍ፤ የማህብረሰቡ አመለካከት በወላጆቿ ላይ ጭምር ጫና በማሳደሩ ወላጆቿ እግር ኳስ መጫወት ማቆም እንዳለባት ሲነግሯት እንደነበረ ታስታውሳለች።

"እኔ ግን ይህ ሁሉ አመለካከት ወደ ኋላ አላስቀረኝም። ዓላማዬ አድርጌ ይዤው ስለነበረ ማንም ሊያስቆመኝ አልቻለም። ቤተሰቦቼም ይህን ሲረዱ እኔን መደገፍ ጀመሩ" ትላለች።

ሴናፍ ተማሪ እያለች ፍቅሯ ለእግር ኳስ እንጂ ለትምህርት አልነበረም። በዚህም ብዙ ጊዜዋን የምታሳለፍው ኳስ በመጫወት ነበር።

"አገርን ወክሎ እንደመሳተፍ የሚያስደስት ነገር የለም" የምትለው ሴናፍ፤ በ2011 በሁለት ዘርፎች የውድድር አሸናፊ ነበረች።

በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21 ጎሎችን በማሰቆጠር ኮከብ ግብ አግቢ እና የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሸልማለች።

ክለቧ አዳማም፣ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኖ እንዲጨርስ የራሷን አስተዋጽኦ አበርክታለች።

የ25 ዓመቷ እግር ኳሰኛ ሴናፍ፤ ወደፊት በእግር ኳሱ ዓለም ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሆና መቀጠል ምኞቷ ነው።

"አንድ ሰው ከቆረጠ እና በያዘው ላይ ካተኮረ ያሰበበትን ማሳካት አይሳነውም" በማለት ከራሷ የህይወት ተሞክሮ በመነሳት የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋችነት ህልሟን እንደምታሳካ በልበ ሙሉነት ትናገራለች።

አንድነት ነገር ማሳካት እንደማይቻል የምናስብ ከሆነ ከስኬት መድረስ እንችልም ስለዚህ ያሰብነው እንዲሳካ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርብናል ትላለች።

ሴናፍ የኔይማር ጁኒየር አድናቂ መሆኗን ትናገራለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ