ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ከሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎች እንዴት እራስዎችን መጠበቅ ይችላሉ?

ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ከሚሰራጩ ሃሰተኛ መረጃዎች ይቆጠቡ Image copyright Getty Images

በቅርቡ በኮሮናቫይረስ የተያዘ በኢትዮጵያ ተገኘ የሚሉ ሐሰተኛ ዜናዎች በስፋት ሲሰራጩ ተሰተውሏል።

የቫይረሱን ስርጭት እና እየተወሰዱ ስላሉ እርምጃዎች በተመለከተ በመንግሥት ተቋማት እና ተዓማኒ ምንጮች የሚሰጡ መረጃዎችን ብቻ መቀበል ይመከራል።

ስለ ቫይረሱ የጠራ ግንዛቤ ይኑርዎ፡

የቫይረሱ ምልክቶች

በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል።

በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል።

አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ኮሮናቫይረስ መድሃኒት አለው?

ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው።

ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው?

  • የዓለም ጤና ድርጅት የሚከትሉትን እንዲያደርጉ ይመክርዎታል።
  • እጅዎን ይታጠቡ - ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች
  • በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ፤ በእጅዎ ዓይን፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።
  • ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ። ቢያንስ የ1 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።
  • ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ - ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ። ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ

እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ።

8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ