አሜሪካዊው ጆ ባይደን ራሳቸውን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ለማስተካከል በመሞከራቸው መዘባበቻ ሆነዋል

ኔልሰን ማንዴላ ፈገግ ብለው ከነግርማ ሞገሳቸው ይታያሉ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ማንዴላ ያን ጊዜ በሮበን ደሴት እስር ላይ ነበሩ

ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ለመሆን ተፍ ተፍ የሚሉት ጆ ባይደን የምርጫ ቅስቀሳቸውን እያጧጧፉት ነው። በአንድ መድረክ ላይ የሚከተለውን ተናገሩ።

"የዛሬ 30 ዓመት በዚህ ቀን ደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ስትሰቃይ እኔ ወንድማችሁ ኔልሰን ማንዴላን ለመጠየቅ እስር ቤት ሄድኩላችሁ፤ ታዲያ መንገድ ላይ ፖሊስ አስሮኝ ነበር። እኮራለሁ በዚህ ድርጊቴ" ካሉ በኋላ "ለዚህ ጀግንነቴ ማንዴላ ራሳቸው አሞካሽተውኛል" ሲሉ አከሉበት።

ይህን ንግግር መጀመርያ ያደረጉት ሳውዝ ካሮላይና ውስጥ ነበር፤ ለዚያም ሺዎች በተገኙበት የምርጫ ቅስቀሳ። ይህንኑ ንግግር ሞቅ አድርገው ሌላም መድረክ ላይ ደገሙት። ታስረን የነበርንው እንዳውም እኔ ብቻ ሳልሆን የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደርም ነበሩበት አሉ።

ሆስኒ ሙባረክና የአዲስ አበባው የግድያ ሙከራ

"እልም ያለ ሥርዓት አልበኝነት ሊፈጠር ይችላል" ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌ.)

ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ነገሩን ማጣራት ጀመረ። በዚያን ጊዜ አብረዋቸው ነበሩ የተባሉት አምባሳደር "እረ በሕግ እንዲህ አይነት ነገር አልተከሰተም፤ ባይደን ምን ነካው?" ብለዋል።

ጆ ባይደን ምናልባት ይህን "ነጭ ውሸት የዋሹት" ለምረጡኝ ቅስቀሳ የጥቁር አሜሪካዊያንን ልብ ለመግዛት ሊሆን ይችላል የሚሉ ግምቶች እየወጡ ነው። በቀጣይ ቀናት ባይደን ነገሩን ያስተባብላሉ ወይም ሁነኛ መረጃ ይዘው ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። አልያ መዘባበቻ ሆነው መቅረታቸው ነው።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ጆ ባይደን እንዲያውም ለዚህ ጀግንነቴ ማንዴላ "ጎበዝ!" ብለውኛል ብለዋል

"ማንዴላ አመስግነውኛል!"

በባራክ ኦባማ ጊዜ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ጆ ባይደን ያኔ ድሮ ሴናተር ነበሩ፤ የአሜሪካ የዴላዌር ግዛትን የሚወክሉ ሴናተር።

ያኔ ከአንድ የአሜሪካ ልዑካ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸው እውነት ነው። በዚያውም ኔልሰን ማንዴላን ጎብኝቷል፤ ያው ልዑኩ። ያኔ ማንዴላ በሮበን ደሴት እስረኛ ነበሩ።

ነገር ግን ባይደን በንግግራቸው በቀጥታ የተናገሩት የሚከተለውን ነው።

ጀርመን 'በገዛ ፈቃድ ራስን የማጥፋት' ሕጓን አላላች

"ያኔ በሶዌቶ ከተማ ጎዳና ማንዴላን ለማየት ስንሄድ... በዚያ ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አምባሳደራችን ጋር ታሰርን። በእውነቱ ማንዴላን ለማየት ስል በመታሰሬ ክብርና ኩራት ይሰማኛል"

ይህንን ደቡብ ኮሮላይና የተናገሩትን ንግግር ባለፈው ሳምንት ለጥቁሮች ታሪክ ክብር በተዘጋጀ እራት ላይ ደገሙት ባይደን። "ለዚህ ተግባሬ ማንዴላ አመስግነውኛል" አሉ። "ኔልሰን ማንዴላ እጃቸውን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርገው 'ባይደን ሆይ እጅግ ላመሰግንህ እወዳለሁ' አሉኝ። ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ሆይ! ለምንድነው የሚያመሰግኑኝ ስላቸው፤ " እኔን እስር ቤት ለመጎብኘት ስትመጣ በመታሰርህ ነው" አሉኝ።

ይህን ንግግር ተከትሎ ኒውዮርክ ታይምስ ነገሩን ለማጣራት ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ያኔ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩትና ባይደን አብረውኝ ታስረዋል ያሏቸው አምባሳደር አንድሩ ያንግ "ለመሆኑ ከባይደን ጋር ማንዴላ ለመጠየቅ ስትሄዱ ታስራችሁ ነበር ወይ ሲባሉ? በድጋሚ "እረ በፍጹም!" ብለዋል። የአሜሪካ ልኡክ በፍጹም ከደቡብ አፍሪካ መንግሥት እስር ሊገጥመው አይችልም ሲሉ አብራርተዋል።

ዛሬ ከዘገየ አንድ የባይደን የምርጫ ቅስቀሳ መኮንን ነገሩን ለማስተባበል ሞክሯል።

"ባይደን ለማለት የፈለጉት ያኔ የጥቁርና የነጭ መግቢያ በር ነበረ፤ እና በጆበርግ አውሮፕላን ጣቢያ እርሳቸውን ከተቀረው ልኡክ ፖሊስ ነጠል አድርጎ ወስዷቸው ነበር፤ ለነጮች በተዘጋጀ በር ይግቡ ሲባሉ አሻፈረኝ ብለዋል" ሲል እምብዛምም ስሜት የማይሰጥ ማስተባበያ ነገር ሰጥቷል።

በቀጣይ ቀናት ነገሩ እየጠራ ይሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።