በአሜሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት የተቸገሩ ኢትዮጵያውያንን እየረዱ የሚገኙ ወገኖች

በአሜሪካ በኮቪድ-19 ምክንያት የተቸገሩ ኢትዮጵያውያንን እየረዱ የሚገኙ ወገኖች

በኮሮናቫይረስ ምክንያት ብዙ ሰዎች በአሜሪካ ከሥራ ውጭ ሆነዋል።

የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ዜጎች ደግሞ በዚህ ጊዜ የበለጠ ለችግሩ ተጋልጠዋል። እነዚህን ወገኖች ለማገዝ የፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተሩ ቴዎድሮስ ለገሰ እና በአሜሪካ ምግብ ቤት ባለቤት የሆነው አይናለም ዘለቀ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

የምግብ ችግር የሚያጋጥማቸው ወገኖች በምግብ ቤቱ መጥተው በነጻ እንዲመገቡ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በገንዘብ እና በተለያዩ ቁሳቁሶች ማገዛቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።