በኡጋንዳ ተራራማ አካባቢዎች "ራቁታቸውን" ያመለጡ እስረኞች እየተፈለጉ ነው

የካራሞጃ ተራራ

የፎቶው ባለመብት, Google

በሰሜናዊ ምሥራቅ ኡጋንዳ ከሚገኝ እስር ቤት ውስጥ ካመለጡ 219 ታራሚዎች መካከል ሰባቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለስልጣናት ተናገሩ።

የተወሰኑ እስረኞች ማረሚያ ቤቱ የሰጣቸውን ቢጫ የደንብ ልብስ አውልቀው፣ ራቁታቸውን በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ተራራ ማምለጣቸውነ ተናግሯል።

እስረኞቹ በሚኣመልጡበት ወቅት መሳሪያ ዘርፈው መውሰዳቸው ተሰምቷል።

ከማረሚያ ቤቱ ያመለጡግለሰቦች ተራራውን የተጠቀሙት ወደ ኬንያ በድንበር በኩል ለመሻገር አስበው ነው ተብሏል።

እስረኞቹ ረብዑ እለት ይገኙበት የነበረውን ሞሮቶ ማረሚያ ቤት ሰብረው ሲያመልጡ አንድ ወታደር መግደላቸው ተነግሯል።

የወታደራዊ ኃይሉ ቃል አቀባይ ካመለጡት መካከል ሁለት ታራሚዎች መገደላቸውን ገልፀዋል።

የወታደራዊ ኃይሉ እና የማረሚያ ቤቱ ባለስልጣናት፣ 15 የጦር መሳሪያ ይዘዋል የተባሉትን ታራሚዎች እየፈለጉ ይገኛሉ።

ማረሚያ ቤቱ 600 ያህል ታራሚዎች ያሉት ሲሆን በሞሮቶ ተራራ ስር ከከተማ ወጣ ብሎ የተገነባ ነው።

የፎቶው ባለመብት, Uganda Peoples' Defence Forces

ታራሚዎቹ እንዴት ከእስር ቤቱ ሊያመልጡ ቻሉ የሚለው እስኪጣራ ድረስ አካባቢው ላይ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ረብዑ እለት የነበረው የተኩስ ልውውጥ የከተማዋን እንቅስቃሴ አቋርጦት ነበር።

ሞሮቶ ከፊል አርብቶ አደር አካባቢ ሲሆን በኡጋንዳዋ ካራሞጃ ካሉ ከተሞች ትልቁ ነው። በአካባቢው በተደጋጋሚ የከብት ዘረፋ እና በመሳሪያ የታገዘ ግጭት መስማት የተለመደ ነው።

መንግሥት ትጥቅ ማስፈታት በሚል በ2000 ዓ.ም በበርካታ ንፁኀን ዜጎች የጦር መሳሪያ ቢሰበስብም አሁንም ግን ድንገት የሚያገረሹ ግጭቶችን ማስቆም አልተቻለም።