ኡጋንዳ፡ በፓርላማ የሰው ጭንቅላት ይዞ የመጣው ግለሰብ የጠፋ ህፃን ልጅ መሆኑ ታወቀ

የኡጋንዳ ፓርላማ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በዚህ ሳምንት በኡጋንዳ አንድ አስደንጋጭ ሁኔታ ተከስቷል።

አንድ ግለሰብ የተቆረጠ የሰው ጭንቅላት ይዞ ወደ ፓርላማ ለመግባት ሞክሯል። ጭንቅላቱም ማሳካ በምትባል ግዛት ያለ ጭንቅላት የተገኘው አስከሬን አካል ነው ተብሏል።

አሰቃቂ የተባለውን ጭንቅላት ወደ ፖርላማ ይዞ የመጣው የ22 አመቱ ጆሴፍ ኑዋሻባ የሚባል ሲሆን በአገሪቱም የወንጀል ምርመራ ክፍልም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ተብሏል።

በማሳካ የሚገኙ ቤተሰቦች ልጃቸው መጥፋቱን ለፖሊስ ሪፖርት አድርገው የነበረ ሲሆን፤ የተገኘውም ጭንቅላት በእርግጥ የሞተው ልጃቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የጄኔቲክስ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ጆሴፍ ልጃቸው በጠፋባቸው ቤተሰብ ውስጥ የእርሻ ስራ እንዲሰራም ተቀጥሮ የነበረ መሆኑን ቤተሰቡ ለአገሪቱ ሚዲያ ተናግረዋል።

የአዕምሮ ህክምናም ለመርመር ቀጠሮም ተይዞ ነበር።

ጆሴፍ ኑዋሽባ የሟቹን ጭንቅላት ወደ ፓርላማ ይዞ የመጣው ለፓርላማው አፈ ጉባኤ ሬቤካ ካዳጋ ለመስጠት እንደነበር ለፖሊሶች ተናግሯል።

አፈ ጉባኤዋ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የፖሊስ ምርመራ ውጤት እየጠበቁ እንደሆነም አፈ ጉባኤዋ ለፓርላማ አባላት ተናግረዋል።