የዓለም ዋንጫን የምታስተናግደው የኳታር ፈታኙ ሙቀት

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ,

የዓለም ዋንጫን የምታስተናግደው የኳታር ፈታኙ ሙቀት

በመጪው ዓመት ኅደር ወር የሚጀመረውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ውድድርን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ያለችው ኳታር ከባድ ወቀሳ እየቀረበባት ነው።

ኳታር ያላት ከፍተኛ ሙቀት ለስፖርት ውድድሮች አዳጋች መሆኑ ከሦስት ዓመት በፊት በተደረገው የአትሌቲስክስ ሻምፒዮና ወቅት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ ስፖርተኞችን አስቸግሮ ውጤት ለማስመዝገብ ሳይችሉ ቀርተዋል።

የቢቢሲ የአረብኛ ቋንቋ አገለግሎት በቅርቡ ባደረገው ምርመራ ኳታር ውስጥ በተለያዩ የሙያ መስኮች ላይ የተሰማሩ የውጭ አገር ዜጎች ሕይወታቸውን አስከሚያሳጣ ችግር እየተዳረጉ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

በተለይ የአገሪቱ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሁኔታ ውስጥ በሚሠሩበት ጊዜ አስፈላጊው ጥንቃቄና ድጋፍ ስለማይደረግላቸው ለጉዳት እየተደረጉ ነው።