ወደ ኬንያ ተወስደው በልመና ላይ በመሰማራት የሚበዘበዙ ልጆች

በገጠሪቱ የታንዛኒያ ክፍል የሚኖሩ ወላጆች አካል ጉዳተኛ ልጆቻቸውን የተሻለ ኑሮ ያገኙልናል ወይም ደግሞ ገንዘብ ያስገኙልናል በሚል አሳልፈው ይሰጣሉ።

ልጆቻቸው ግን ወደ ኬንያ ናይሮቢ ከመጡ በኋላ ጎዳና ላይ እንዲለምኑ ይገደዳሉ። ከሚለምኑት ገንዘብም ለቤተሰቦቻቸውም ሆነ ለራሳቸው የሚያገኙት ነገር የለም።

ይልቁንም አለቆቻቸው ሁሉንም ገንዘብ ከመውሰድ ባሻገር ይደበድቧቸዋል። ይህንን ጭካኔ የተሞላበት የገንዘብ ማግኛ ሰንሰለት ቢቢሲ በድብቅ ሲከታተል ቆይቶ አዘዋዋሪዎቹን አጋልጧል።