ቅሬታዎን ለቢቢሲ አማርኛ ይላኩ

ቅሬታዎን በ bbcamharic_complaints@bbc.co.uk ቢልኩልን ይደርሰናል::

ለቅሬታዎ በ14 ቀናት ውስጥ ምላሽ እንሰጣለን:: ነገር ግን ይህ ባቀረቡት የቅሬታ አይነት እንዲሁም በሌሎች ቀርበው ምርመራና ምላሽ በሚፈልጉ ቅሬታዎች ብዛት ላይ የሚወሰን ይሆናል::

የሚደርሱንን ቅሬታዎችንና ሌሎች አስተያየቶችን የምናስተናግድበትን አሰራር ለመረዳት እባክዎን በእንግሊዘኛ የተፃፈውን What happens to your complaint' የሚለውን ክፍል ያንብቡ::

አጠቃላይ ለሆኑ ጥያቄዎች እባክዎን የአስተያየት መስጫ ገፃችንን ይጠቀሙ feedback page

የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና የታዳሚዎችን ተሳትፎ በአግባቡ ለመያዝ እንዲሁም በሚሰጡን አስተያየቶች ላይ ሪፖርት ለማዘጋጀት ያግዘን ዘንድ ከእርስዎ የምናገኘውን ግላዊ መረጃ በቢቢሲና እምነት በምንጥልባቸው አገልግሎት ሰጪዎች አማካይነት እንዲጠናቀሩ እናደርጋለን።

ቢቢሲና አገልግሎት የሚሰጡን ተቋማት የእርስዎን መረጃ በድርጅታችን የመረጃ አያያዝ ፖሊሲና በመረጃ ጥበቃ ሕግ መሠረት በተገቢው ሁኔታ እንዲያዙ ያደርጋሉ። ቢቢሲም ከእርስዎ የሚያገኘውን መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን ሥራው ተስማሚ በሆነ መንገድ የታዳሚዎችን አስተያየቶችና ቅሬታዎችን ለማስተናገድና ምላሽ ለመስጠት በተገቢው ሁኔታ ያጠናቅራል።

ቢቢሲ ከእርስዎ ያገኘውን መረጃ በምን መልኩ እንደሚይዝ የበለጠ ለመረዳት (በእንግሊዝኛ የተጻፈውን) Privacy and Cookies Policy የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።

ግላዊ መረጃዎን በተመለከተ በቢቢሲ አያያዝ ላይ ቅሬታ አቅርበው ባገኙት ምላሽ ካልረኩ፤ ለመረጃ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ቅሬታዎን ማቅረብ ይችላሉ።

የአድራሻ ዝርዝር መረጃዎችዎ
ማስታወቂያ