Got a TV Licence?

You need one to watch live TV on any channel or device, and BBC programmes on iPlayer. It’s the law.

Find out more
I don’t have a TV Licence.

ቀጥታ ዘገባ

የተጠቀሱት ሰዓቶቸ የዩናይትድ ኪንግደም ናቸዉ

 1. ጭር ያለ የከተማ ውስጥ ጎዳና

  እርግጥ ነው ከቤት ሆኖ መሥራት በድኅረ ኮሮናቫይረስ ዘመን ደንብ የሚሆንባቸው መሥሪያ ቤቶች እንደሚኖሩ ከወዲሁ እየተነገረ ነው። ይህ ሀቅ ከኩባንያ ኩባንያ ቢለያይም ቅሉ፤ ቀጣሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሠራተኞቻቸው ከቤት ሲሰሩ ኩባንያቸው ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ እንደሚሆን በትንሹም ቢሆን ተረድተዋል። በዚህ ሀሳብ ገፍተውበት ቢሮ ድርሽ እንዳትሉ ቢሉንስ?

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 2. በአሜሪካ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው የኮሮናቫይረስ ህሙማንን የመሞት እድል 12 በመቶ መጨመሩ ተገለፀ

  በአሜሪካ የኮሮና ህመምተኛ ሲቀበር

  ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው አሜሪካውያን በኮቪድ-19 ከተያዙ ሆስፒታል ተኝተው የመታከም ሁኔታቸው ስድስት እጥፍ የሚጨምር ሲሆን የመሞት እድላቸው ደግሞ 12 እጥፍ ከፍ ያለ መሆኑን የአሜሪካ በሽታ መቆጣጣርና መከላከል (ሲዲሲ) አስታወቀ።

  ድርጅቱ ባደረገው ጥናት በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎችን ለማከም አዳጋች ከሚያደርጉ ተያያዥ የጤና ችግሮች መካከል የልብ ሕመም አንዱ ነው ብሏል።

  ሲዲሲ 1.3 ሚሊየን የኮቪድ-19 ሕሙማንን ፋይል አገላብጦ ስኳር እና ከባድ የሆነ የሳንባ ሕመም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን አክሞ ለማዳን አዳጋች ከሚያደርጉ በሽታዎች መካከል ናቸው ሲል አስታውቋል።

  ይህ የድርጅቱ ሪፖርት በኮቪድ-19 ከተያዙ ሰዎች መካከል 15 በመቶዎቹ ሆስፒታል ተኝተው መታከም ሲያስፈልጋቸው አምስት በመቶዎቹ ደግሞ ይሞታሉ ብሏል።

 3. በሃዋይ የለይቶ ማቆያ ደንብን የተላለፉ ተጓዦች ግዛቲቱን ለቀው እንዲወጡ ተደረገ

  ሃዋኢ

  በሃዋይ የለይቶ ማቆያን ደንብ ተላልፈዋል የተባሉ ተጓዦች ከግዛቲቱ ለቅቀው ለመውጣት ተስማሙ።

  ከተጓዦቹ መካከል አንዱ እንደገለፀው ወደ ግዛቲቱ ከደረሱ በኋላ ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ መግባት እንዳለባቸው መመሪያ የተቀመጠ ሲሆን ይህንን ጥሰዋል በሚል ጥርጣሬ ከተያዙ በኋላ የሞት ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል።

  ተጓዦቹ በሃዋይ በዚህ ወር ከመድረሳቸው በፊት በማዕከላዊ አሜሪካ ለሁለት ዓመት ያህል ሲጓዙ ቆይተዋል።

  ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው 21 ሰዎች ያሉበት የተጓዦች ቡድን ከለይቶ ማቆያ በመውጣት በውቅያኖስ ዳርቻዎች አካባቢ ታይቷል።

  "ሰዎች ወደ ቤታችን በመምጣት አፋቸው ላይ የመጣላቸውን ስድብ ሁሉ ይሰድቡን ጀመር" ሲሉ ለፈረንሳዩ የዜኛ ወኪል የተናገሩት ከመንገደኞቹ መካከል አንዷ የሆኑት ኬንድራ ካርተር ሲሆኑ አክለውም "በፌስቡክ ገፃችን በኩል የሞት ማስፈራሪያ ደርሶናል" ብለዋል።

  እንደ አካባቢው የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ ከሆነ የቡድኑ አንድ አባል በጊዜ ገደብ የተቀመጠ የእስር ጊዜ ተፈርዶበት ክሱ ተዘግቷል።

  ቡድኑ በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ ላይ ድርጊታቸው ተገቢ አለመሆኑን በማመን ይቅርታ ጠይቋል።

 4. ድምጻዊውን ወደ ሙዚቃ ድግሱ ያጓጓዘው አየር መንገድ ታገደ

  ድምፃዊ አዚዝ ፋሾላ

  በናይጄሪያ የሚገኘው አየር መንገድ ድምጻዊ ናይራ ማርሊንን፣ ቅዳሜ እለት ከሌጎስ አሳፍሮ አቡጃ ላይ ለነበረው የሙዚቃ ድግስ በመውሰዱ የአገሪቱን የአቪየሽን ሚኒስትርን ይቅርታ ጠየቀ።

  የአየር መንገዱ አስፈላጊ ያልሆነን በረራ በማመቻቸቱ እና መንግሥት የኮሮናቫይረስን ስርጭት ለመዋጋት ያስቀመጠውን መመሪያ በመጣሱ አግዶታል።

  ለአቪየሽን ሚኒስቴር፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኃላፊው ሳም ኡዉአጆኩ፣ በጻፉት የይቅርታ ደብዳቤ ላይ እንዳሉት በረራው ተዘጋጅቶ የነበረው እሁድ እለት ለሚጓዙ ዳኛ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ሃሳባቸውን መለወጣቸውን አስፍረዋል።

  አክለውም የቅዳሜውን በረራ የፈቀዱት መንገደኛው ያቀረበውን ሰነድ ከተመለከቱና አንዱ መንገደኛ የመንግሥት ሚኒስትር መስለዋቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

  ድምፃዊው በእውነተኛ ስሙ አዚዝ ፋሾላ የሚባል ሲሆን ከእርሱ ስም ጋር ተመሳሳይ የሆነ ስም ያላቸው ናይጄሪያዊ ሚኒስትር አሉ።

 5. ዴክሳሜታሶን ሕይወት አድን የኮሮናቫይረስ መድሃኒት?

  ዴክሳሜታሶን

  በርካሽ ዋጋና በስፋት የሚገኘው ዴክሳማታሶኔ በኮቪድ-19 በጽኑ የታመሙ ሰዎች ሕይወት አድን መሆኑን የዩናይትድ ኪንግደም ባለሙያዎች ገለፁ።

  መድሃኒቱን በአነስተኛ መጠን በመስጠት ማከም ይህንን ገዳይ ቫይረስ በመዋጋት ረገድ ወሳኝ መሆኑን ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

  በቬንትሌተር የሚተነፍሱ የኮቪድ-19 ሕሙማንን ሞት በአንድ ሶስተኛ፣ በኦክስጅን ተገጥሞላቸው የሚተነፍሱትን ደግሞ በአንድ አምስተኛ እንደሚቀንስ ተናግረዋል።

  መድሃኒቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለኮሮናቫይረስ ፈዋሽ መሆን አለመሆኑ ሙከራ እየተደረገባቸው ካሉ መድሃኒቶች መካከል አንዱ ነው።

  ተመራማሪዎች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ እንደተከሰተ በዩናይትድ ኪንግደም መድሃኒቱ በስፋት ቢገኝ ኖሮ እስካሁን ድረስ የ5000 ሰዎችን ሕይወት ማዳን ይቻል ነበር ብለዋል።

  ምክንያታቸው ደግሞ ርካሽ መሆኑ ሲሆን ከፍተኛ የኮቪድ-19 ሕሙማን ባሏቸው ደሃ አገራት ውስጥም ቢሆን በርካታ ጥቅም እንዳለው ያስረዳሉ።

  መድሃኒቱ ለጽኑ ሕሙማን በደም ስር የሚሰጥ ሲሆን፣ ሕመማቸው ላልፀናባቸው ደግሞ በክኒን መልክ እንዲወስዱት ይደረጋል ተብሏል።

  የኮቪድ-19 ሕሙማንን እንዲያገግሙ ከሚረዱ መድሃኒቶች መካከል፣ ለኢቦላ ታማሚዎችን ለማከም የሚውለው ፀረ ቫይረስ መድሃኒት፣ ሬምዴሲቪር ይገኝበታል።

 6. ዶናልድ ትራምፕ

  ለወባ እጅግ ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ የሚነገርለት ሀይድሮክሲክሎሮኪን ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝት ተከትሎ ዝነኛ ለመሆን የተገደደ መድኃኒት ነው ማለት ይቻላል፡፡ መድኃኒቱ ዝናው ከፍ እያለ በመምጣቱ ትልቋ የመድኃኒቱ አምራች ሕንድ ይህን መድኃኒት ወደ ውጭ መላክን በአዋጅ እስከማስከልከል ደርሳ ነበር፡፡ ሀይድሮክሲክሎሮኪን በተለይም ዶናልድ ትራምፕ "ተአምራዊ ፈውስ ይሰጣል" ብለው በሚያስገርም እርግጠኛነት ሲያሞካሹት የነበረ መድኃኒት ነው፡፡

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 7. በኢትዮጵያ 109 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ 738 ሰዎች ከኮሮናቫይረስ አገገሙ

  እለታዊ መግለጫ

  ዛሬ የጤና ሚኒስቴርና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጡት እለታዊ መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 5102 ሰዎች መካከል 109 የኮቪድ-19 ተገኘባቸው።

  ከእነዚህም መካከል 81 ከአዲስ አበባ፣ ዘጠኝ ከኦሮሚያ፣ አራት ከሶማሊ፣ አራት ከደቡብ ሕዝቦችና ብሔር ብሔረሰቦች፣ ሶስት ደግሞ ከአማራ፣ ሶስት ከትግራይ እንዲሁም ሶስት ከአፋር ሁለት ደግሞ ከሐረሪ ክልሎች መሆናቸውን ሪፖርቱ አስታውቋል።

  በተጨማሪ በዛሬው ዕለት የአንድ ሰው ሕይወት ያለፈ ሲሆን ይህም በአጠቃላይ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር 61 አድርሶታል።

  በትናንትናው እለት 118 ሰዎች በመላው አገሪቱ ማገገማቸውን የገለፀው ሪፖርቱ እነዚህም 113 ከአዲስ አበባ፣ አምስቱ ደግሞ ከትግራይ መሆናቸው አክሎ ገልጿል።

  እስካሁን ድረስ በመላ አገሪቱ 192 ሺህ 087 ምርመራዎች ሲከናወኑ፣ ከእነዚህም መካከል 3 ሺህ 630 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

 8. የታንዛንያው ፕሬዝዳንት በመላ አገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ አዘዙ

  ትምሀርት ቤቶች በታንዛንያ

  የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ከሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንዲከፈቱ አዘዙ።

  ፕሬዝዳንቱ አክለውም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ታንዛንያውያን አቋርጠውት የነበረውን የማህበራዊ ሕይወታቸውንም ሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

  ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ በፈጣሪ እርዳታ አገራቸው በፈጣሪ እርዳታ ከወረርሽኙ መትረፏን ገልፀዋል። ይህ ንግግራቸው ግን በሁሉም ዘንድ እኩል ተቀባይነትን አላገኘም።

  ሰኞ እለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ቃሲም ማያሊዋ እንዳሉት ከአገሪቱ 26 ክልሎች በአስሩ ብቻ 66 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖራቸውን አስታውቀው ነበር።

  በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች መማር ጀምረው ነበር።ሌሎቹ ደግሞ እስካሁን ድረስ ትምህርት አልጀመሩም።

 9. ምርመራ ሲደረግ

  ከዚህ ቀደም ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 የተገኘባቸው አሉ። ከነዚህ መካከልም አዲስ አበባ ልደታ አካባቢ ይኖሩ የነበሩት አዛውንት ይጠቀሳሉ። አዛውንቷ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈጽሞ፤ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሀዘን ተቀምጠው ሳለ ነበር ከአስክሬናቸው በተወሰደ ናሙና ኮቪድ-19 እንዳለባቸው የታወቀው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለጥቂት ቀናት እንቅስቃሴ ገትተው እንደነበርም ይታወሳል። ታዲያ በአስክሬን ምርመራ ኮቪድ-19 መገኘቱ ምን ያመላክታል?

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 10. ሰሜን ሸዋ

  ባለፈው ሳምንት ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሆኖ በደረሰባቸው አደጋ በህክምና ላይ ሳሉ ህይወታቸው አልፎ ወደ ትውልድ መንደራቸው በተወሰዱ ግለሰብ ሐዘንና ቀብር ላይ ከተሳተፉ ሰዎች መካከል በአራቱ ላይ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘ ተነገረ።

  ተጨማሪ ያንብቡ
  next
 11. የፈረንሳይ ጤና ባለሙያዎቸ አድማ ላይ ይገኛሉ

  የፈረንሳይ የጤና ባለሙያዎች

  የፈረንሳይ ዶክተሮች እና ነርሶች ፓሪስ በሚገኘው የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር ደጃፍ ላይ የተቃውሞ ስለፍ እያካሄዱ ይገኛሉ።

  ሌሎች ተመሳሳይ ሰልፎችም በመላው ፈረንሳይ ለማድረግ ቀጠሮ ተይዟል።

  የጤና ባለሙያዎች ህብረት እንደሚለው ከሆነ፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ፈረንሳይን ባስጨነቀ ወቅት ህዝቡ ለጤና ባለሙያዎች ባሳያው ድጋፍ ተደስተዋል ይሁን እንጂ ተግባር መቅደም አለበት። ለጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲሁም በጤና ተቋማት ውስጥ ተጨማሪ አልጋዎች መኖር አለባቸው የሚለው ጥያቄ የጤና ባለሙያዎች ይዘውት ከተነሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

  የኢማኑኤል ማክሮን መንግሥት በጤና ስርዓቱ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እና በወረርሽኙ ወቅት ሲሰሩ ለነበሩ ሰራተኞች ጉርሻ ለመስጠት በእቅድ ላይ ይገኛል።

  የሠራተኞች ማህበራት ግን ኮቪድ-19 የፈረንሳይ የጤና ስርዓት ደካማ መሆኑን አጋልጧል ስለዚህ የጤና ስርዓቱን የሚያሻሽል ከፍተኛ የሆነ ኢንቨስትመንት ያስፈልጋል ይላሉ።

 12. ኤርትራ ተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ 13 ሰዎችን አገኘች

  Asmara

  ኤርትራ ተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ 13 ሰዎች ማግኘቷን የአገሪቱ ጤና ሚንስቴር አስታወቀ።

  የኤርትራ ጤና ሚንሰቴር ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጡ 31 ሰዎችን መገኘታቸውን አስታውቆ ነበር።

  ትናንት በቫይረሱ መያዛቸው የተገለጹት 13 ሰዎች በሙሉ ኤርትራውያን መሆናቸውን እና ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ከሱዳን የተመለሱ ናቸው ተብሏል።

  ጤና ሚንስቴሩ እንዳለው ምንም እንኳ የእንቅስቃሴ ገደብ በቀጠናው ባሉ አገራት ቢጣልም፤ ባለፉት ሁለት ወራት 7764 የሚሆኑ ኤርትራውያን ትክክለኛ ባልሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ እና የመን በመንገድ እና በባህር ወደ ኤርትራ ተመልሰዋል።

  በኤርትራ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር 109 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 70 የሚሆኑት አሁንም በጤና ተቋማት ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

  በኮቪድ-19 ምክንያት በኤርትራ እስካሁን የተመዘገበ ሞት የለም።

 13. በኡጋንዳ የአደባባይ ምርጫ ቅስቀሳ ታገደ

  የሙሴቪኒ ተቀናቃኝ ቦቢ ዋይን
  Image caption: የሙሴቪኒ ተቀናቃኝ ቦቢ ዋይን

  የኡጋንዳ የምርጫ ኮሚሽን ተፎካካሪዎች የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳያካሂዱ ውሳኔ አስተላልፏል። እጩዎች በመገናኛ ብዙኅን ቅስቀሳ እንዲያደርጉም ተነግሯቸዋል።

  ኮሚሽኑ እንዳለው፤ በቀጣይ ዓመት ጥር ላይ ብሔራዊ ምርጫ ይካሄዳል። መራጮችን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል ጥብቅ እርምጃዎች እንደሚወሰዱም ተገልጿል።

  በምርጫው ቀን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅና እጅ ማጽዳት ግዴታ ይሆናል።

  ኮሚሽኑ ተፎካካሪዎች ይፋ የሚደረጉበትን ጊዜ ከስድስት ወር በታች እንዲሆን አድርጓል።

  በምርጫው የአገሪቱ ፕሬዘዳንት፣ የፓርላማ አባላትና የየአካባቢው መሪዎች ይመረጣሉ።

  አምስተኛ የአስተዳደር ዘመናቸው ላይ ያሉት ፕሬዘዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ለሌላ የሥልጣን ዘመን መወዳደር ይችላሉ። በምርጫው ስለመሳተፋቸው ግን ያሉት ነገር የለም።

 14. በዩኬ የደሞዝተኞች ቁጥር በ600 ሺህ ቀነሰ

  ሥራ

  በዩናይትድ ኪንግደም ከመጋቢት እስከ ግንቦት ከ600 ሺህ በላይ ሰዎች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ተነገረ። ሚያዝያ ላይ የሥራ አጥነት ደረጃው 3.9 በመቶ ነበር።

  የብሔራዊ ስታትስቲክስ ተቋም ምክትል ኃላፊ ጆናታን አቶው እንዳሉት፤ የደሞዝተኞች ቁጥር መቀነሱ ኮሮናቫይረስ በሥራ ዘርፎች ያሳደረውን ተጽዕኖ ያመለክታል።

  “እስከ ሚያዝያ የተሰበሰበው መረጃ የሥራ ሰዓት ዘጠኝ በመቶ መቀነሱን ያሳያል” ብለዋል። ይህ የተከሰተው ወደ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች ወደ ሥራ እየሄዱ ስላልሆነ ነው።

 15. ቦትስዋና በቅርቡ የመረመረቻቸው ሰዎች ነፃ ስለሆኑ ገደብ አነሳች

  ቦትስዋና

  በቦትስዋና በቅርቡ የኮሮናቫይረስ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ነፃ መሆናቸውን ተከትሎ፤ በመዲናዋ ጋቦሮኔ ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ተነስቷል።

  እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ጥብቅ እገዳ የተነሳው ግንቦት 21 ቢሆንም በበሽታው የተያዙ ሰዎች በመገኘታቸው አዲስ እገዳ ተጥሎ ነበር።

  የጤና ሚንስትሩ እንዳሉት፤ በቫይረሱ ተይዘው ይሆናል በሚል ከተመረመሩ 16 ሰዎች አስሩ ነፃ ሆነዋል። የተቀሩት ስድስት ሰዎች ውጤት ደግሞ ገና አልታወቀም።

  ምርመራው የተካሄደው በመንግሥት እንዲሁም በግል ቤተ ሙከራዎችም ነው።

 16. ኬንያ የጠፉትን የጃክ ማ የእርዳታ ቁሳ ቁሶች እያፈላለገች ነው

  የኬንያ ጤና ሚንስትር ከቻይናዊው ቢልየነር ጃክ ማ ተለግሰው ‘ጠፉ’ የተባሉትን የህክምና ቁሳ ቁሶች ጉዳይ እየመረመረ መሆኑን አስታወቀ።

  የኮቪድ-19 መመርመሪያና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ጠፉ ከተባሉት ቁሳ ቁሶች መካከል ይገኙበታል። እርዳታው ናይሮቢ፣ ኬንያ የደረሰው መጋቢት 24 ነበር።

  የጤና ሚንስትሩ ሙታይ ካግዌ ለጋዜጠኞች እንዳሉት፤ ጠፉ የተባሉት ቁሳ ቁሶች ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

  “እንዲህ አይነት ነገር ስለመፈጠሩ እናውቃለን። ምርመራ ላይ ስለሆንን ብዙ መናገር አልችልም” ብለዋል ሚንስትሩ።

  በኬንያ የሀኪሞች መገልገያ (ፒፒኢ) እጥረት መኖሩ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

  በአገሪቱ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 3,500 ደርሷል።

  የህክምና ቁሳ ቁሶች
 17. የኩዌት እና የባህሬን መተግበሪያዎች ግላዊ መብት ይጥሳሉ ተባለ

  መተግበሪያ
  Image caption: 'ቢአዌር' መተግበሪያ

  በኩዌት እና በባህሬን በኮቪድ-19 ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን የሚጠቁሙ መተግበሪያዎች የግለሰቦችን መብት እንደሚጋፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተናገሩ።

  አምንስቲ እንዳለው፤ ‘ቢአዌር ባህሬን’ እና ‘ሽሎኒክ’ የተባሉት መተግበሪያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች ያሉበትን ቦታ በጂፒኤስ ያለሟቋረጥ ይከታተላሉ። ይህም የግላዊነት መብትን ይጋፋል ተብሏል።

  ለኮቪድ-19 የተሠሩ መተግበሪያዎች በዋነኛነት ብሉቱዝ ይጠቀማሉ። የባህሬን እና የክዌት መተግበሪያዎች ግን ሰዎች ያሉበትን ቦታ በጂፒኤስ በማግኘት መረጃውን ወደ ማዕከላዊ ቋት (ዳታቤዝ) ይልካሉ።

  በመተግበሪያዎቹ ላይ ጥናት የሠሩ ተመራማሪዎች እንደሚሉት፤ ይህ መረጃ ከአንድ ሰው መታወቂያ ቁጥር ጋር በቀላሉ መተሳሰር ይችላል።

  አምንስቲ እነዚህን መተግበሪያዎች መጠቀም መቆም አለበት ብሏል።

 18. ናይጄሪያ ሦስት ዓመት የሚዘልቅ የኮቪድ-19 መከላከያ እቅድ ነደፈች

  ምርመራ ሲደረግ
  Image caption: ምርመራ ሲደረግ

  የናይጄሪያ መንግሥት ለሦስት ዓመታት የሚቆይ የኮሮናቫይረስ መከላከያ እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ።

  ትምህር ቤቶች ጨምሮ በብዛት ሰዎች የሚሰበሰቡባቸውን ተቋማት ለመክፈት ጊዜው ገና ነውም ተብሏል።

  የጤና ሚንስትሩ ኦሴጂ ኤህናሬ “ወረርሽኙ አብሮን ይኖራል። ለወደፊቱም ትምህርት እየወሰድን እንቀጥላለን” ብለዋል።

  በሽታውን ለመከላከል የወጣው እቅድ፤ የአጭር፣ የረዥምና የመካከለኛ ጊዜ በሚል ተከፋፍሏል።

  ምርመራ ማካሄድ፣ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች ማሰስም የእቅዱ አካል ነው።

  በሌላ በኩል በገበያና በሌሎችም አካባቢዎች ብዙዎች ያለ አፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሲንቀሳቀሱ፣ አካላዊ ርቀት ሳይጠብቁም መታየታቸው ሚንስትሩን አስቆጥቷል።

 19. ቤጂንግ ለበሽታው የተጋለጡ ሰዎች ከግዛቷ እንዳይወጡ አገደች

  ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እገዳ ከተጣለባቸው መካከል ይጠቀሳሉ
  Image caption: ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እገዳ ከተጣለባቸው መካከል ይጠቀሳሉ

  የቻይና መዲና ቤጂንግ ለበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ ሰዎች ከከተማው እንዳይወጡ እገዳ ጥላለች።

  ቫይረሱ ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሰዎች እገዳ ከተጣለባቸው መካከል ይጠቀሳሉ። ታክሲዎች እና ረዥም ርቀት የሚጓዙ አውቶብሶችም ታግደዋል።

  ውሳኔው የተላለፈው በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ነው። አዲስ የተመዘገቡ ህሙማን በከተማው ከሚገኝ የችርቻሮ ገበያ ጋር ንክኪ ያላቸው ናቸው ተብሏል።

  ባለፈው ሀሙስ የመጀመሪያ ታማሚ ከተገኘ በኋላ በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች ጨምረዋል።

  በቤጂንግ ለ50 ተከታታይ ቀናት በበሽታው የተያዘ ሰው አልተመዘገበም ነበር።

 20. በደቡብ ሱዳን ካምፕ በመተንፈሻ አካል ህመም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ

  ካምፑ ውስጥ 111,766 ሰዎች ይኖራሉ።
  Image caption: ካምፑ ውስጥ 111,766 ሰዎች ይኖራሉ

  በደቡብ ሱዳን በቤንቱ ካምፕ ውስጥ ከመተንፈሻ አካል ህመም ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

  ካምፑን የሚያስተዳድረው የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ክንፍ ሲሆን፤ ካምፑ ውስጥ 111,766 ሰዎች ይኖራሉ። እነዚህ በመንግሥትና በአማጽያን ውጊያ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ናቸው።

  የዓለም ጤና ድርጅት አመራሩ ዶ/ር ጆሴፍ ዋማላ ጁባ ውስጥ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ ካምፑ ውስጥ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሰዎች ስላሉ የበሽታው ሥርጭት አስጊ ነው።

  “በመተንፈሻ ህመም ሳቢያ የተከሰቱት ሞቶች ከኮቪድ-19 ጋር ስለመያያዛቸው ገና ምርመራ እያደረግን ነው” ብለዋል።

  በደቡብ ሱዳን በሽታው የተያዙ ሰዎች 1,693 ሲሆኑ 27 ሰዎች ሞተዋል። 49 ደግሞ አገግመዋል።