Got a TV Licence?

You need one to watch live TV on any channel or device, and BBC programmes on iPlayer. It’s the law.

Find out more
I don’t have a TV Licence.

ቀጥታ ዘገባ

የተጠቀሱት ሰዓቶቸ የዩናይትድ ኪንግደም ናቸዉ

 1. ለሟች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የተደረገ መታሰቢያ

  በትናንትናው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የመታሰቢ ዝግጅት ተደርጓል

  View more on facebook
 2. በቁፋሮ የወጡ ቁሳቁሶች

  የትናንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302 አውሮፕላን የተከሰከሰበት ቦታ በቁፋሮ የወጡ ነገሮችን ከተንቀሳቃሽ ምስሉ መመልከት ይቻላል።

  View more on facebook
 3. በርካታ ተሳፋሪዎች ሊታደሙበት በነበረው የናይሮቢው የዩኤን ስብሰባ የህሊና ፀሎት ተደረገላቸው

  ትናንት ከተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መንገደኞች ጥቂት የማይባሉት ዛሬ በተጀመረው በናይሮቢው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ስብሰባ ለመታደም ነበር አውሮፕላኑን የተሳፈሩት። ዛሬ ግን ሊታደሙ ባሰቡበት ስብሰባ የህሊና ፀሎት ተደርጎላቸዋል።

  የዩኤን ስብሰባ በናይሮቢ
  የዩኤን ስብሰባ በናይሮቢ
 4. የአውሮፕላኑ ሞተርና ጎማዎች ተገኝተዋል

  በሶስት ኤክስካቬትር እየተደረገ ባለው ቁፋሮ እስካሁን የET 302 አውሮፕላን ሞተርና ጎማዎች ተገኝተዋል። እንዲሁም የአውሮፐላን ስብርባሪና ልብሶች ማየታቸውን ቦታው ላይ የተገኙት ባልደረቦቻችን ገልፀውልናል።

 5. Post update

  የትናንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302 አውሮፕላን የተከሰከሰበት ቦታ ላይ ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ፎረን ሲክ ምርመራ ቡድን እና የቀይ መስቀል በጎ ፍቃደኞች የተገኙ ሲሆን በሶስት ኤክስካቬተር ቁፋሮ እየተካሄደ እንደሆነ ከተንቀሳቃሽ ምስሉ መረዳት ይቻላል።

  View more on facebook
 6. የህሊና ፀሎት በዩኤን ኢሲኤ ቅጥር

  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኢሲኤ ሰራተኞች በኢሲኤ ቅጥር በአደጋው ህይታቸውን ላጡ ባልደረቦቻቸው የህሊና ፀሎት አድርገዋል

  UN ECA
  UN ECA
 7. በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡት ኢትዮጵያዊያን ወዳጅ ጓደኞቻቸው ያሉት

  View more on facebook
  View more on facebook
  View more on facebook
  View more on facebook
  ሃሰን ካቴንዴ ፌስቡክ
 8. ሰበርኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጊዜው ቦይንግ 737-8 Max ን መጠቀም ማቆሙን አስታወቀ

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትናንትናው አደጋ እስኪጣራና ለበረራ ደህንነት ሲል ለጊዜው ቦይንግ 737 Max 8 መጠቀም ማቆሙን ባወጣው አምሰተኛ የአደጋ ሪፖርት አስታውቋል።

  የትናንቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ET302አውሮፕላን መከስከስን ተከትሎ የአሜሪካኑ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ ኩባንያ ላይ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።

  ባለፉት አምስት ወራት ቦይንግ በአዲስ መልክ የሰራው ቦይንግ 737-8 Max የተሰኘው ይህ አውሮፕላን ሲከሰከስ የትናንቱ ሁለተኛ ነው።

  ብዙዎች የትናንቱን አውሮፕላን አደጋ ከጥቂት ወራት በፊት በላየን አየር መንገድ ከደረሰው የተመሳሳይ ቦይንግ አውሮፕላን አደጋ ጋር እያመሳሰሉት ቢሆንም የአቬሽን ኤክስፐርቶች ግን የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ እስኪታወቅ ምንም ለማለት ጊዜ ገና ነው ብለዋል።

  በሌላ በኩል የትናንቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ተከትሎ የቻይና አቬይሽን በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች ቦይንግ 737-8 Max ን አውሮፕላንን መጠቀም እንዲያቆሙ ትእዛዝ አስተላልፏል።

  ቦይንግ በአዲስ መልክ የሰራው ይህ አውሮፕላን ስራ ላይ የዋለው እንደ አውሮፓውያኑ ከ2017 ወዲህ ነው።

  ከአምስት ወር በፊት የላየን አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737-8 Max አውሮፕላን ከኢንዶኔዥያ ጃካርታ እንደተነሳ ወዲያው የተከሰከሰ ሲሆን ተሳፋሪ የነበሩት 189 ሰዎች በሙሉ መሞታቸው ይታወሳል።

  View more on twitter
 9. ብሔራዊ የሀዘን ቀን ታወጀ

  በትናንትናው ዕለት በቦይንግ 737 በረራ ቁጥር ET302 የ157 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ በትናንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 2 2011 ዓ.ም የብሔራዊ ሐዘን ቀን እንዲሆን አውጇል።

  View more on twitter
 10. ቢቢሲ አማርኛ በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል

  ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በቢሾፍቱ በተከሰከሰውና የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 157 ሰዎችን አሳፍሮ በነበረው ET 302 ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ላጣችሁ ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን። ስለ አደጋው የነበረንን የቀጥታ ዘገባ አጠናቅቀናል።

  የሃሰን ሻማ
 11. አደጋውን የሚመረምር ኮሚቴ ተዋቀረ

  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ተሳፋሪ የነበሩ 149 መንገደኞችና ስምንት የበረራ ሰራተኞችን ሞት ተከትሎ አየር መንገዱ አደጋውን የሚመረምር ኮሚቴ እንዳዋቀረ በትዊተር ገፁ አስታውቋል። አየር መንገዱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የኢትዮጵያ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣንና የኢትዯጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የአደጋውን መንስኤ ይመረምራሉ።

  የሟቾችን ማንነት ከታወቀ በኋላ አስከሬናቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚሰጥ አየር መንገዱ አስታውቋል። በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦችም መርዶው ተነግሯቸዋል።

  View more on twitter
 12. በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦች መርዶ ተነገራቸው

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የET 302 ተሳፋሪ ከነበሩ 149 መንገደኞችና 8 የበረራ ሰራተኞች የ18ቱ ሟች ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦችን ከአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ምንም የተረፈ እንደ እንደሌለ በመግለፅ ማርዳቱን ፋና ዘግቧል።

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሎጎ
 13. የአውሮፕላኑ አብራሪዎች ልምድ

  ቢሾፍቱ ላይ የተከሰከሰው ET 302ዋና አብራሪ የነበረው ያሬድ ሙልጌታ ከ 8 ሺህ ሰዓት በላያ ያበረረ ፓይለት ሲሆን ረዳት አብራሪው አህመድ ኑር ሞሃመድ ደግሞ 2 መቶ ሰዓት ያበረረ ፓይለት እንደሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትዊተር ገፁ ስለ አደጋው ያወጣውን ሶስተኛ ሪፖርት አያይዞ አስፍሯል።

  View more on twitter
 14. ከሟቾቹ ጥቂቱ

  የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሮቶኮል ሻሀድ አብዲሻኩር በአውሮፕላን አደጋው ከሞቱት አንዱ መሆኑን ራዲዮ ዳልሰን ተብሎ የሚጠራው የሶማሊያ የግል ሚዲያ ዘግቧል።

  ከዚህ በተጨማሪ የስሎቫኪያ የፓርላማ አባል ሚስቱንና ልጁን አጥቷል። የስሎቫክ ናሺናል ፓርቲ አባል የሆነው የፓርላማ አባል አንቶን ሄርንኮ ፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው በአደጋው እንዳጡ ገልፀዋል።

  የምግብና መስተንግዶ ድርጅት ታማሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጆናታን ሴክስ በአደጋው ከሞቱት መካከል አንዱ ናቸው። በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ብዙ ቁጥር ያላቸው ሬስቶራንቶች ባለቤት የሆነው ይህ ድርጅት የህልፈታቸውን ዜና ያሳወቀው በፌስቡክ ገፁ ነው።

  በጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቤተሰብ፣ ዘመድና ወዳጆቻቸውን እየጠበቁ ለነበሩም የህልፈታቸው ዜና ተነግሯቸዋል።

  በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ የሶስት ሟቾችን በትዊተር ገፁ ላይ ያሰፈረ ሲሆን ከቤተሰቦቻቸውም ጋር ለመገናኘት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ገልጿል።

  የአልጀዚራ ጋዜጠኛ በትዊተር ገጿ እንዳሰፈረችውም የተባበሩት መንግስታት መልእክተኞች ከሟቾቹ መካከል ናቸው። የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ ስብሰባ በኬንያ መዲና ናይሮቢ ለመካፈል ሲጓዙ እንደነበር ተገልጿል። በዚህ ስብሰባ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

  1. 125:11 PM - Mar 10, 2019Twitter Ads info and privacy
  View more on twitter
  View more on twitter
  View more on twitter
  View more on facebook
 15. ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ አደጋ የደረሰበትን ቦታ ጎበኙ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ዛሬ ከሰዓት በኋላ ET 302 የተከሰከሰበት ቦታ እንደተገኙ ጽ/ቤታቸው በትዊተር ገፁ አስፍሯል። በተጨማሪም አመሻሹ ላይ በቴሌቪዥን የሀዘን መግለጫ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ላጡትም መፅናናትን ተመኝተዋል።

  View more on twitter
  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ
 16. አደጋው የደረሰበት ቦታ በተንቀሳቃሽ ምስል

  ቦይንግ 737 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET 302 በቢሾፍቱ የተከሰከሰበት አካባቢ በተንቀሳቃሽ ምስል

  View more on facebook
 17. የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል

  በኢትዮጵያ ሲቪል አቬን ቅጥር በተከፈተው የድንገተኛ አደጋ ማእከል በርካታ የመንገደኛ ቤተሰቦች ተገኝተዋል። የተረበሹና የሚያለቅሱም ብዙዎች ሲሆኑ በማእከሉ የተገኙ የአየር መንገዱ ሰራተኞችም ሃዘን ይነበብባቸዋል።

  የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል
  የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል
  የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል
  የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል
  የመንገደኛ ቤተሰቦች በድንገተኛ ማዕከል
 18. አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል

  በዛሬው ዕለት ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረው ቦይንግ 737 ቢሾፍቱ የተከሰከሰበት አካባቢ።

  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት ቦታ
  አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል
  አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል
  አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል
  አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል
  አደጋው የደረሰበት አካባቢ በምስል