Got a TV Licence?

You need one to watch live TV on any channel or device, and BBC programmes on iPlayer. It’s the law.

Find out more
I don’t have a TV Licence.

ጭምቅ ሃሳብ

 1. ፕሬዝዳንት አልበሺር ከስልጣን ወረዱ
 2. ሱዳን ለሁለት ዓመት በሽግግር መንግስት ትመራለች
 3. በፕሬዝዳንቱ ላይ ተቃውሞ መሰማት የጀመረው ባለፈው ሕዳር ወር ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ነበር
 4. በርካታ ሰዎች በሃገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተሰባስበዋል
 5. ባለፈው ቅዳሜ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ተቃውሟቸውን ወደ ጦር ሠራዊቱ ዋና መስሪያ ቤት ደጃፍ አዙረውታል
 6. ጦር ሠራዊቱ ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን እንዲለቁ ጫና ያደርግባቸዋል የሚሉ ጥርጣሬዎች አሉ
 7. አልበሽር በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጦር ወንጀል ተከሰው ይፈለጋሉ

ቀጥታ ዘገባ

የተጠቀሱት ሰዓቶቸ የዩናይትድ ኪንግደም ናቸዉ

 1. በካርቱሙ ተቃውሞ የሴቶች ሚና

  "በካርቱም ሴቶች ለተቃውሞ እንዲህ በነቂስ ወጥተው ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው"

  በሱዳኑ ተቃውሞ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ተነገሯል።

  በሱዳን ካርቱም የጀግኒት ኢትዮጵያውያን ሴቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አስቴር ጌታሁን ነዋሪነታቸው በካርቱም አቡሃማማ የተባለ ስፍራ ነው።

  “ሴቶች እንዲህ በነቂስ ወጥተው የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያሰሙ ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ይላሉ።

  እኝህ ነዋሪ እንደሚሉት በርካታ ሴቶች "ፍርድ እንፈልጋለን፣ እንዲወርድ እንፈልጋለን ፣ ነፃነት እንፈልጋለን” በማለት አደባባይ ወጥተው በጣታቸው የድል (V) ምልክት እያሳዩ፣ እያጨበጨቡ በድፍረት በየአደባባዩ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፤ ደስታቸውንም እየገለፁ ነው።

  በሃገሪቱ ከዚህ ቀደም በነበሩት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በሃይማኖትና ሌሎች ምክንያቶች የሴቶች ተሳትፎ እምብዛም አልነበረም ያሉት ነዋሪዋ “ አሁን እየተማሩና የማህበረሰቡ አስተሳሰብ እየተለወጠ ሲመጣ ግንባር ቀደም ሆነው ተገኝተዋል” ብለዋል።

  በአብዛኛው ሰልፉን ሲመሩት የነበሩት ሴቶች ናቸው የሚሉት ነዋሪዋ ወንዶችም ከኋላ በመሆን በሕብረትና በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ገልፀውልናል።

  "ሴቶቹ ለውጥ እንዲመጣ እንደጮኹት ሁሉ አሁንም ለውጥን አጥብቀው ይሻሉ።" ሲሉም ያክላሉ።

  አሁን ለታየው ለውጥም የሴቶቹ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የታዘቡትን አካፍለውናል።

 2. መግለጫውን ያነበቡት የጦሩ አለቃ ማን ናቸው?

  አዋድ ሞሐመድ አህመድ ኢብን ኡፍ

  ኦማር አል-በሽር ከስልጣን ተነስተው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ስለመደረጋቸው በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው ያነበቡት የጦር አለቃ አዋድ ሞሐመድ አህመድ ኢብን ኡፍ ይሰኛሉ።

  እኚህ ሰው የቀድሞ ፕሬዝደንት ኦማር አል-በሽር ምክትል እና የመከላከያ ሚንስትር ናቸው።

  የ65 ዓመቱ ሉትናንት ጀኔራል የፕሬዝደንቱ ቢሮ እና የጦሩ የደህንነት ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል። ዲፕሎማሲያዊ ክህሎታቸው፣ የጦር እና የፖለቲካ ልምዳቸው ሁነኛ የአል-በሽር ተተኪ አድርጓቸው ቆይቷል።

  በዳርፉር ተከስቶ በነበረው ግጭት እጃቸው አለበት ተብለው በአሜሪካ መንግሥት ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከሚገኙ ግለሰቦች መካከል አዋድ ሞሐመድ አህመድ ኢብን ኡፍ አንዱ ናቸው።

 3. ተቃዋሚዎች በጦሩ መግለጫ ደስተኛ አይደሉም

  View more on twitter

  ተቃዋሚዎች በጦሩ መግለጫ ደስተኛ አለመሆናቸውን ተናገሩ። ሬም አባስ የተባለች ጋዜጠኛ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ጦሩ በመግለጫው ስለ ሲቪል የሽግግር መንግሥት ያለው ነገር የለም።

  ጦሩ በመግለጫው ካነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል-በሽር በቁጥጥር ሥር ውለው ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ እንደሚወሰዱ፣ ለሶስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚታወጅ፣ ሽግግሩን የሚመራ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እንደሚቋቋም እና የ2005 ህገ-መንግሥት ውድቅ እንደሚደረግ ይገኙበታል።

  ተዋሚዎች ጥያቄያቸው ምላሽ እንዳላገኘ እና ጦሩ ፕሬዝዳንቱን ከማንሳቱ ውጪ አሁንም ተመሳሳይ ሥርዓት ሃገሪቱን እንደተቆጣጠረ ይገኛል እያሉ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው።

  የተቃዋሚዎች መሪ የሆኑ ቡድኖች ተቃዋሚዎች የጦሩ ዋና ቢሮ አካባቢ ተሰባስበው እንዲቆዩ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

 4. የአል በሽር ምስሎች ከአደባባይ እየተነሱ ነው

  View more on twitter

  ለሰላሳ ዓመታት ያህል ሱዳንን ሲመሩ የቆዩት አል-በሽር ከስልጣን መነሳታቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚንስትር አስታውቀዋል።

  የኑሮ ውድነት ወደ አደባባይ ያወጣቸው ተቃዋሚዎች፤ የአል-በሽርን ከስልጣን መነሳት አደባባይ በመውጣት ሲጠይቁ መሰንበታቸው ይታወሳል።

  ተቃዋሚዎች በአደባባይ ተሰቅለው የሚገኙ የፕሬዚዳንቱን ምስል ሲያነሱ ተስተውለዋል።

 5. ጦሩ ከሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች

  የሱዳን ጦር አዛዥ

  ከደቂቃዎች በፊት ጦሩ በሰጠው መግለጫ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።

  • የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር አል-በሽር በቁጥጥር ሥር ውለው ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ ይወሰዳሉ።

  • ለሶስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል።

  • ሽግግሩን የሚመራ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ይቋቋማል። ስለ ሽግግር ምክር ቤት ዝርዝር መረጃ በቀጣይ መግለጫ ይፋ ይሆናል።

  • የ2005 ህገ-መንግሥት ውድቅ ይደረጋል።

 6. ሰበርሱዳን ለሁለት ዓመታት በሽግግር መንግስት ትመራለች

  ፕሬዝዳንት አል በሽር

  የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር በመግለጫቸው እንዳሉት የበላይ ኮሚቴው ለሁለት ዓመት ያህል ወታደራዊ የሽግግር መንግስት መመስረቱን ገልጠው ፕሬዝዳንት አል በሽር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

  ለሶስት ወር ያህል የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ተደንግጓል።

 7. የሱዳናውያን ተቃውሞ ምልክት የሆነችው ሴት!

  የሱዳን ነዋሪዎች በሙዚቃና በዳንስ የተቃውሞ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ ሰነበቱ። መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። በስፍራውም ውጥረት መንገሱን ለቢቢሲ መልዕክት የላኩ ሰልፈኞች አስታውቀዋል።

  Video content

  Video caption: የሱዳናውያን ተቃውሞ ምልክት የሆነችው ሴት!
 8. "ውጥረት ነግሷል”

  በሱዳን የተቃውሞ ሰልፉ የሚካሄደው ቀንም ለሊትም ነው። ይህች ሴት የሱዳናውያን ተቃውሞ ምልክት ተደርጋ ተወስዳለች።

  ከወታደራዊ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት የተሰባሰቡት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ለቢቢሲ መልእክት እየላኩ ነው። በመልእክታቸውም “ሰልፈኞቹ መግለጫውን እየጠበቁ በመሆኑ ውጥረት ነግሷል” ሲሉ ተናግረዋል።

  ሰልፈኞቹ በጦር ኃይሉ ይሰጣል የተባለውን መግለጫ ሲጠብቁ ሰባት ሰዓት አልፏቸዋል። የብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያው አሁንም የሚያሰማው ወታደራዊ ሙዚቃ ብቻ ነው።

  ወታደሩ ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከሰልጣን እንዲወርዱ ጫና ያደርጋል የሚል ጭምጭምታ አለ።

 9. ተቃዋሚ ሰልፈኞችና ወታደሮች

  ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ሲተሙ
  Image caption: ተቃዋሚ ሰልፈኞች ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ሲተሙ

  በተቃዋሚ ሰልፈኞችና በወታደሩ መካከል ያለው ግንኙነት የፕሬዝዳንት አልበሺር እጣ ፈንታን የሚወስን ይመስላል።

  ይህ በካርቱም ጎዳናዎች ላይ የሚታይ ምስል ፍንጭ ይሰጥ ይሆናል።

  ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ወታደሮች ከመፋጠጥ ይልቅ ተቀራርበው ይታያሉ።

  ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተሰባስበው
  Image caption: ተቃዋሚ ሰልፈኞች ከጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ተሰባስበው የሚታዩ ሲሆን ወታደሮች በስፍራው ቢኖሩም በሁለቱ መካከል መፋጠጥ አይታይም
  የሠራዊቱ አባላት በተቃውሞ ሰልፈኞች አጠገብ ሲያልፉና ሰልፈኞቹ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሲሰጧቸው
  Image caption: የሠራዊቱ አባላት በተቃውሞ ሰልፈኞች አጠገብ ሲያልፉና ሰልፈኞቹ ሞቅ ያለ ሰላምታ ሲሰጧቸው
  ፕሬዝዳንቱ በማንኛውም ሰዓት ካሉበት ወጥተው ሰልፈኞቹን ያነጋግራሉ በሚል ጥበቃው ቀጥሏል
  Image caption: ከመንግሥት ቢሮው ውጪ ጥበቃው ቀጥሏል
 10. ተቃዋሚ ሰልፈኞች እንዲረጋጉ ተጠየቀ

  ፕሬዝዳንት አል በሺር

  ፕሬዝዳንት ኦማር አል በሺር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቀውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ያስተባበሩ አካላት፣ ሰልፈኞች እንዲረጋጉ፣ የመንግሥት እና የግለሰብ ንብረቶችን “እንዳያጠቁ” ጥሪ ማቅረባቸውን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘገበ።

  ሕብረት ለነፃነት እና ለለውጥ የተሰኘው ቡድን በመግለጫው ላይ እንዳስቀመጠው “ ሕዝባችንን የምንጠይቀው ራሳቸውን አንዲቆጣጠሩ፣ የግለሰብም ሆነ የመንግሥት ንብረት ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይፈፅሙ ነው” ብሏል።

  “ማንኛውም ግለሰብ ይህንን ሲያደርግ ቢገኝ በሕግ ተጠያቂ ይሆናል። አብዮታችን ሰላማዊ፣ ሰላማዊና ሰላማዊ ነው” በማለት አክለዋል።

  ከጦር ኃይሉ ወሳኝ ያሉትን መግለጫም እየጠበቁ ነው። መግለጫው ይሰጣል ተብሎ መጠበቅ ከጀመረ ስድስት ሰዓታት አልፈውታል።

 11. የተቃውሞ ምልክት የሆነችው ሱዳናዊት!

  የሱዳን ነዋሪዎች በሙዚቃና በዳንስ የተቃውሞ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ ሰነበቱ ... መጨረሻውን ለማየት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ለማየት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። የፌስ ቡክ ገፃችንን ይውደዱ። ያጋሩ!

  View more on facebook
 12. በካርቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ምክትል ሊቀመንበር ስለዛሬዋ እለት

  "የሚኖረው ተስፋና ስጋት፤ በሚመጣው የሚወሰን ነው የሚሆነው"

  ሰላማዊ ሰልፈኞች በካርቱም ጎዳና

  በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ሐዋሪያ አስራት ይልማ ኢትዮጵያውያን የሱዳንን ሰላም ከምንም በላይ ይሻሉ ይላሉ።

  "በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደ አገራቸው እየኖሩ፣ እየሰሩ ያሉበት ስለሆነ አገሪቱ ሰላም ካልሆነች ይህ ሊሆን ስለማይችል የአገራቸውን ያህል ለሱዳን ሰላምን ይናፍቃሉ" የሚሉት ሐዋሪያ አስራት በአሁኑ ሰዓት ፕሬዚዳንት አልበሺር ስልጣኑን ለመልቀቅ የተለያዩ አካላት ጋር በውይይት ላይ እንዳሉ መስማታቸውን ገልፀዋል።

  ሕዝቡ በሰላም ወጥቶ ደስታውን እየገለፀ፤ እየጨፈረ ውጤቱን እየተጠባበቀም ተመልክተዋል። ስለ ተቃውሞው ሲናገሩም እጅግ ሰላማዊ መሆኑን ገልፀው "እንደዚህ ዓይነት ተቃውሞ ገጥሞኝ አያውቅም" ሲሉ ይገልፁታል።

  እርሳቸው እንደሚሉት በተቃውሞው የተለያዩ አገራት ላይ እንደሚታየው ንብረት ማውደም፣ ሰው ላይ ጉዳት ማድረስ አልታየም፤ ወደ አደባባይ ያልወጡት ነዋሪዎች የንግድ ድርጅታቸውንም ሆነ መስሪያ ቤታቸውን ከፍተው እየሰሩ እንደሚገኙም ታዝበዋል።

  "እስከዛሬ እንዲህ ዓይነት ሰላማዊ ተቃውሞ አይቼ አላውቅም" ያስባላቸውም ይኼው ነው።

  ይመጣል ተብሎ በሚጠበቀው ለውጥ የሚኖራቸው ተስፋና ስጋትን ተጠይቀው ሲመልሱ፤ ማነው የሚመራው? ከዚህ በፊት በነበረው አካሄድ ነው የሚቀጥለው? የሚለው ብዙዎች ላይ ተፅዕኖ ስለሚያመጣ እኛ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎችም ለውጡን በጉጉት እየተጠባበቅን ነው ብለውናል።

 13. ወታደሮች የገዢውን ፓርቲ ጽህፈት ቤቶች ሰብረው ገቡ

  የሱዳን ወታደሮች የገዢውን ፓርቲ ጽህፈት ቤቶች ሰብረው ገቡ

  ተቃዋሚ ሰልፈኞች

  የሱዳን ወታደሮች ካርቱም ካለው የፕሬዝዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር ገዢ ፓርቲ ከሆነው ከናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለትን ቡድን ጽህፈት ቤቶች ሰብረው መግባታቸውን ኤኤፍፒ እና ሮይተርስ የዜና ወኪሎች ዘገቡ።

  ወታደሮቹ ሰብረው የገቡት የሱዳን ገዢ ፓርቲ ዋነኛ አባል የሆነውን ኢስላሚክ ሙቭመንት የተባለውን ቡድን ጽህፈት ቤቶችን ነው።

 14. የሱዳን ጦር ሠራዊትና መንግሥት

  የሱዳን ጦር ሠራዊት በሀገሪቱ ፖለቲካ ያለው ተሳትፎ

  ፕሬዝዳንት አልበሺር

  የሱዳን ጦር ሠራዊትና መንግሥት

  ሱዳን ነጻ ከወጣችበት ከ1956 (እኤአ) ጀምሮ የሱዳን ጦር ሠራዊት በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ሲጫወት እስካሁን ድረስ ዘልቋል። በዚህም ሠራዊቱ የሕዝቡን ብሶት በመጠቀም ስልጣን ላይ በመውጣት የሕዝቡን ጥያቄ ችላ ብሎ ጨቋኝ አገዛዝን በመመስረት ይወቀሳል።

  • ሱዳን ነጻ ከወጣች ከሁለት ዓመት በኋላ በ1958 (እኤአ) የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄነራል ኢብራሂም አቡድ ደም ባላፋሰሰ መፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ያዙ።

  • በ1964 (እኤአ) የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ወታደራዊውን መንግሥት ከስልጣን እንዲወርድ አስገደደው።

  • ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ በኮሎኔል ጃፋር ኤል ኒሜሪ የተመራ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶ ወታደራዊ መንግሥት ስልጣን ያዘ። የኒሜሪ መንግሥትም ተከታታይ ተቃውሞዎችና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች አጋጥመውታል።

  • በ1985 (እኤአ) በሌፍተናንት ጄነራል አብደል ራህማን ስዋር አልዳሃብ የተመራ የወታደራዊ መኮንኖች ቡድን ኤል ኒሜሪን ከስልጣን አስወገደ።

  • ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ አልዳሃብ ስልጣናቸውን በሕዝብ ለተመረጠው የጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልማሃዲ አስረከቡ።

  • ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በኋላ በሰኔ ወር 1989 (እኤአ) በብርጋዲየር ኦማር አል በሽር የተመሩት እስላማዊ ወታደራዊ መኮንኖች ያልተረጋጋውን የአልመሃዲ መንግሥትን ከመንበሩ ገለበጡት።

  ምንም እንኳን የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟቸውም አልበሽር ለሰላሳ ዓመታት የሱዳን መሪ በመሆን ቆይተዋል።

 15. ለ34 ዓመታት በካርቱም የኖሩት ኢትዮጵያዊ

  " ፕሬዚዳንቱ ከስልጣን ወርደዋል የሚል ወሬ አለ፤ እስካሁን በሱዳን ቴሌቪዢን የሰማነው የለም"

  ፕሬዝዳንት አልበሺር በወታደራዊ ስነ ስርዓት ታጅበው

  ከፕሬዚደንት አልበሽር አስተዳድር በፊት ጀምሮ፣ ለ34 ዓመታት በካርቱም የኖሩት አቶ ነጋሲ ተፈራ በተቃውሞው በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰ ምንም ችግር አለመኖሩንና ነዋሪዎች በሰላማዊ መልኩ ደስታቸውን እያሰሙ፣ በመኪና እየተዘዋወሩ እንደሚገኙ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

  "አሁን ወታደራዊ መንግሥት ስልጣኑን እንደያዘው እየተነገረ ነው፤ በሚቀጥለው ዓመት ምርጫ ሌላ ይመረጣል የሚል ተስፋ አለ" ሲሉ የታዘቡትን ነግረውናል።

  "የፕሬዚደንት አልበሽር አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን ምቹ ነበር፤ እንደ አባት ነበሩ" የሚሉት አቶ ነጋሲ የስልጣኑ ተረካቢ ወታደሩ ከሆኑ ፈታኝ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ይሁን እንጂ ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ለውጥ ግን የኑሮ ውድነቱን ያሻሽላል የሚል ተስፋ ሰጥቷቸዋል።

  ወደፊት ስለሚሆነው ግን አሁን መናገር እንደማይችሉ አቶ ነጋሲ ገልፀውልናል።

 16. ሱዳናውያን በካርቱም በነቂስ ወጥተዋል

  የፕሬዝዳንት አልበሺርን ከስልጣን መውረድ ዜና በጉጉት የሚጠባበቁ ሱዳናውያን ወደ ጦር ኃይሉ መስሪያ ቤት እያመሩ ነው

  Video content

  Video caption: Sudan protests: Demonstrators march through Khartoum

  ሱዳናውያን በነቂስ ወጥተው ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት እያመሩ ነው።

 17. የሱዳን ጦር ሠራዊትና መንግሥት

  የሱዳን ጦር ሠራዊትና መንግሥት

  ሱዳን ነጻ ከወጣችበት ከ1956 (እኤአ) ጀምሮ የሱዳን ጦር ሠራዊት በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና ሲጫወት እስካሁን ድረስ ዘልቋል። በዚህም ሠራዊቱ የሕዝቡን ብሶት በመጠቀም ስልጣን ላይ በመውጣት የሕዝቡን ጥያቄ ችላ ብሎ ጨቋኝ አገዛዝን በመመስረት ይወቀሳል።

  • ሱዳን ነጻ ከወጣች ከሁለት ዓመት በኋላ በ1958 (እኤአ) የሠራዊቱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄነራል ኢብራሂም አቡድ ደም ባላፋሰሰ መፈንቅለ መንግሥት ስልጣን ያዙ።

  • በ1964 (እኤአ) የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ወታደራዊውን መንግሥት ከስልጣን እንዲወርድ አስገደደው።

  • ከአምስት ዓመታት በኋላ ደግሞ በኮሎኔል ጃፋር ኤል ኒሜሪ የተመራ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶ ወታደራዊ መንግሥት ስልጣን ያዘ። የኒሜሪ መንግሥትም ተከታታይ ተቃውሞዎችና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎች አጋጥመውታል።

  • በ1985 (እኤአ) በሌፍተናንት ጄነራል አብደል ራህማን ስዋር አልዳሃብ የተመራ የወታደራዊ መኮንኖች ቡድን ኤል ኒሜሪን ከስልጣን አስወገደ።

  • ከአንድ ዓመት በኋላ ደግሞ አልዳሃብ ስልጣናቸውን በሕዝብ ለተመረጣው የጠቅላይ ሚኒስትር ሳዲቅ አልማሃዲ አስረከቡ።

  • ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በኋላ በሰኔ ወር 1989 (እኤአ) በብርጋዲየር ኦማር አል በሽር የተመሩት እስላማዊ ወታደራዊ መኮንኖች ያልተረጋጋውን የአልመሃዲ መንግሥትን ከመንበሩ ገለበጡት።

  ምንም እንኳን የተለያዩ ፈተናዎች ቢገጥሟቸውም አልበሽር ለሰላሳ ዓመታት የሱዳን መሪ በመሆን ቆይተዋል።

 18. በሱዳን ካርቱም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስተያየት

  "ሥራ ያልተስተጓጎለበት፤ ሰው ያልተጎዳበት፤ መንግስትም ጥንቃቄ ያደረገበት ነው"

  ሱዳናውያን ደስታቸውን ሲገልጡ

  ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የካርቱም ነዋሪ ዛሬ ሕዝቡ በሰላም ደስታውን በአደባባይ እየገለፀ እንደሚገኝ ነግረውናል። እርሳቸው እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ሰው ከቤት ወጥቶ በየአደባባዩ የመኪና መብራት እያበራና ክላክስ እያደረገ ደስታውን እየገለፀ ውጤቱንም እየተጠባባቀ ይገኛል። "እንቅስቃሴውም በጣም ሰላማዊ ነው" የሚሉት ነዋሪው እርሳቸውም መኪና እያሽከረከሩ ሕዝቡን እንደተቀላቀሉ ገልፀውልናል።

  የመከላከያ ሚንስትሩ እና ምክትል ፕሬዚደንቱ ስልጣኑን ይረከባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ህዝቡ እርሳቸውንም ስለማይመርጥ ውይይት ላይ እንደሚገኙ ነው የሰማሁትም ብለዋል።

  ውይይቱ እንደተጠናቀቀ መግለጫ ይሰጣል ብለው እየተጠባባቁ እንደሚገኙ የሚናገሩት ኢትዮጵያዊው ትናንት የፕሬዚደንቱ ደጋፊዎች ይወጣሉ ተብሎ ተጠብቆ ስለነበር ስጋት ነበር፤ ነገር ግን ስለተሰረዘ ፍፁም ሰላማዊ ሆኗል በማለት ያክላሉ።

  "ስራ ያልተስተጓጎለበት፣ ሰው ያልተጎዳበት ፣በመንግስትም ጥንቃቄ የተደረገበት ነው" ሲሉ ያለውን ሁኔታ ገልፀውታል።

  View more on twitter
 19. ሱዳናውያን ፕሬዝዳንቱ ወርደዋል በማለት ደስታቸውን እየገለጡ ነው

  ሱዳናውያን ፕሬዝዳንቱ ወርደዋል በማለት ደስታቸውን እየገለጡ ነው

  እንደ ፈረንሳዩ የዜና ወኪል ዘገባ ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ በካርቱም የሚኖሩ ሱዳናውያን “ፕሬዝዳንቱ ወርደዋል” በማለት ወደ ጦር ኃይሉ ዋና መስሪያ ቤት እየተመሙ ነው።

  እስካሁን ድረስ ይፋዊ መግለጫ የተሰጠ ባይሆንም “ትልቁን ዜና እየጠበቅን ነው” ሲል አንድ የሰልፉ ተሳታፊ ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል።

  የተቃውሞ ሰልፈኛው አክሎም “ ዜናውን ሳንሰማ ከዚህ ንቅንቅ አንልም። እርግጥ ነው አል በሺር መውረዱን አውቀናል” ብሏል።

  ተቃዋሚ ሰልፈኞች ባንዲራ እያውለበለቡ