ከምላጭ የመነጨ ምላጭ ዘዴ

የመገበያያ ዘይቤአችንን ምላጭ እንዴት ቀየረ? Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የመገበያያ ዘይቤአችንን ምላጭ እንዴት ቀየረ?

ከዚህ ቀደም የፕሪንተር ቀለም ለመተካት ፈልጎ የሚያውቅ ሰው ምንም ያህል ቢያደናግርም የቀለሙ ዋጋ ከፕሪንተሩ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ሆኖ ሊያገኘው ይችላል።

ይህም ሊሆን የቻለው ዓለምን ከቀየሩት ሃሳቦች አንዱ ምክንያት ነው።

እሱም ኪንግ ካምፕ ጂሌት የምላጭ አምራች ድርጅት መሥራች የሆነው ጂሌት እንግዳ የሆነ የፍልስፍና ሃሳብ ስለነበረው። ሃሳቡም ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ምላጭን መሸጥ ነበር።

Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ አቶ ጂሌት ምላጭና ስለት ለይቶ መሸጥ ጀመሩ

የአቶ ጂሌት ሐሳብ ከጺም መላጨት ባለፈ የዓለምን ኢኮኖሚ እስከ ዛሬ የቀየረ ነው። ይህ በሁለት የተከፈለ የክፍያ ዘዴ 'መላጫና ምላጭ' በመባል ይታወቃል ስሙንም ያገኘው ከፂም መላጫ ንግድ አዲስ ዘይቤ የተወሰደ በመሆኑ ነው።

ፕሪንተርና ቀለሙን እነደ ምሳሌ ብንወስድ፥ፕሪንተርን የሚያክል መሣሪያ በፕላሰቲክ ውስጥ ከሚሸጠው ቀለም ዋጋ ጋር ሲነፃፀር እንዴት ትንሽ ልዩነት ሊኖረው እንደቻለ አጠያያቂ ነው።

ለሻጩ ግን ገንዘብ የሚያስገኝለት ፕሪንተሩን በትንሽ ገንዘብ ሽጦ ተለዋጩን ቀለም በከፍተኛ ዋጋ መሸጡ ነው። መቼም ቀለሙን በከፈተኛ ዋጋ ላለመግዛት ከተወዳዳሪ ድርጅት አዲስ ፕሪንተር ይገዛል ተብሎ አይጠበቅም።

ስለዚህም ቀለሙን በተመደበለት ዋጋ መግዛት ቀዳሚው አማራጭ ይሆናል።

Image copyright Alamy

ለተጠቃሚዎች መላጫውን እንዲገዙት በሚጋብዝ ቀላል ክፍያ ሸጦ በየጊዜው ለሚቀየረው ምላጭ ግን ከፍ ያለ ዋጋን የመጠየቅ ዘዴ ነው።

ኪንግ ካምፕ ጂሌት ሥራ ከመጀመሩ በፊት ምላጮች ትልቅ ወፍራምና ኪስ የማይጎዱ ነበሩ። ምክንያቱም በሚዶለዱሙበት ጊዜ ይሳላሉ እንጂ አይጣሉም ነበር።

ጂሌትም ምላጯን አስገብቶ አጥብቆ የሚይዝለትን መላጫ መፍጠር ቢችል ሳሳ ያለ ምላጭ ሰርቶ በዝቅተኛ ዋጋ መሸጥ እንደሚችል ተገነዘበ።

የሁለት ጊዜ ክፍያ ዘዴውን ወዲያውኑ ተግባራዊ ሳያደርግ በወቅቱ ሁለቱንም ምርቶቹን በውድ ዋጋ ነበረ ለገበያ ያቀረበው። አንድ የጂሌት መላጫ በ5 ዶላር ማለትም የአንድ ሠራተኛ የሳምንት ደምውዝ አንድ ሦስተኛ በሚያክል ዋጋ ይሸጥነበረ።

ነገር ግን ከጊዜ በኋላ አዲሱን የማስከፈል ዘዴ ጀምሮ እስካሁን ብዙ ድርጅቶች የሚጠቀሙበት ዘዴ ሊሆን ቻለ።

ለምሳሌ በጣም ታዋቂ የሆነውን ፕሌይስቴሽን የተሰኘው መጫወቻውን ብንወስድ ሶኒ አንድ ፕሌይስቴሽን በሚሸጥበት ጊዜ ብዙም ገንዘብ አያገኝበትም። ሆኖም ግን ሶኒ ገንዘቡን ማግኘት የሚጀምርው ፕሌይስቴሽን ላላቸው ሰዎች የመጫወቻ ሲዲዎችን በሚሸጥበት ጊዜ ነው።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የሶኒ ፕሌይስቴሽን ቁጥር 4 እ.አ.አ በ2013 ሲሸጥ በዓለም ዙሪያ 40 ሚልዮን አልፎ ነበር

የቋሚነት ጥቅም

ይህ ዘዴ እንዲሠራ ግን የጂሌት መላጫን የሚጠቀሙ ሰዎች ምላጩን በሌላ ርካሽ ምላጭ አለመተካታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ይህንም ለማረጋገጥ እንዲቻል ደግሞ የመጀመሪያው አማራጭ በሕጋዊ መንገድ በፈጠራ መብት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በቴክኖሎጂ ነው። ፕሌይስቴሽን ላይ ሌሎች የጨዋታ ጌሞች ውይም ደግሞ የፕሪንተር ቀለሞች ከራሳቸው ቀለም ውጪ እንደማይሠሩት ሁሉ ሌሎች ድርጅቶችም እነዲህ አይነቱን መላ እየተጠቀሙ ነው።

ነገር ግን ይህም ዘዴ ቢሆን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ብቻ ነው የሚሠራው። ምክንያቱም ተመሳሳይ ሆኖ በረከሰ ዕቃ ለመቀየር ቢፈለግ እንኳን አንዴ ዋናው መሣሪያ ከተገዛ በኋላ ከባድ ይሆናል።

ለምሳሌ ያህል የአዶቤን ፎቶሾፕ ለለመደ ሰው ረከስ ያለ አማራጭ ከመጠቀም ይልቅ ትንሽ ገንዘብ ከፍሎ ያንኑ መጠቀም ይመረጣል።

ለዚህም ነው ብዙ የሶፍትዌር ሻጮች ለመጀመሪያ ወራት ነጻ አገልግሎት የሚሰጡት ዋጋውን ቀስ ብለው ሲጨምሩም ተጠቃሚው ያለ ምንም ማጉረምረም መክፈላቸውን ይቀጥላሉ ማለት ነው።

አገራጋሪ ተቀባይነት

የምንገለገልበትን ዕቃ ለመለወጥ ለምርቱ ካዳበርነው ሥነ-ልቦናዊ ታማኝነት ጋር የሚያያዝ ውሳኔ ይሆናል። ለዚህም ነው የጂሌት የሽያጭ ክፍል ተመሳስለው የተሰሩ ምላጮች በጥሩ ሁኔታ የመላጨት አቅም የላቸውም ብሎ ከነገረን ተጨማሪ እየከፈልንም ቢሆን የጂሌትን ምላጭ ያለማመንታት እንጠቀማለን።

በሁለት ጊዜ የማስከፈል ዘዴን መጠቀም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፤ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎችም ስለምን ሸማቾች ይህን ዘዴ ተቀብለው ደንበኛ እንደሚሆኑ እቆቅልሽ ሆኖባቸዋል። ነገር ግን አሳማኝ ሊሆን የሚችለው ምላሽ ግን ግራ መጋባት ያስከተለው ውጤት ሊሆን ይችላል።

ተጠቃሚዎች ወደፊት ብዙ ገንዘብ በመክፈል ሊበዘበዙ መሆኑን አልተገነዘቡትም አሊያ ደግሞ ቢገነዘቡትም የወደፊቱን አስበው የተሻለውን የተሻለውን አማራጭ ከወዲሁ ለመምረጥ ቸግሯቸው ይሆናል።

የሚያስገርመው ነገር ግን ይህ የመላጫና የምላጭ የንግድ ስልት ተጠቃሚውን ለዕለት ከዕለት መገልገያዎች ከፍ ያለ ዋጋን የማስከፈል ዘዴ ነው። ነገር ግን የኪንግ ካምፕ ጂሌት እሳቤ መነሻው ከአንድ ኩባንያ ለኑሮ መሰረታዊ የሆኑ ምርቶችን በጣም በርካሽ ዋጋ ማቅረብ ነበረ።

በተጨባጭ ሲታይ ግን፤ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ሳይሆን ለንግድ ተቋማት አዲስ ዘዴን በመፍጠር ስኬታማ አድርጓቸዋል።ከምላጭ የመነጨ ምላጭ ዘዴ ።