የሶሪያ ጦርነት፡ ማን ከማን ጋር እየተዋጋ ነው?

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በሶሪያ ጦርነት እጃቸውን ያሰገቡ ሀገራትና ቡድኖች በየጊዜው እየጨመሩ ነው

የሶሪያ ጦርነት ጅማሮ ዜጎች ''ዲሞክራሲ ይስፈን ሙስናም ይብቃ'' በሚል አደባባይ የወጡበት የአውሮፓውያኑ መጋቢት 2011 ነበር።

ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ላይ የተነሳው የህዝብ ተቃውሞ በፍጥነት ወደ ለየለት ጦርነት ተቀየረ።

ይሀው እስካሁንም መቋጫ ያለተገኘለት የእርስ በርስ ግጭት ሆኖ እንደቀጠለ ነው።

የአለም ኃያላን ሀገራትም ጎራ ይዘው የጦርነቱ አካል መሆናቸው ደግሞ ጉዳዩን ይበልጥ አወሳስቦታል።

በፕሬዝዳንት አሳድ በኩል

  • ሩሲያ -በአየር ጥቃትና ለተባበሩት መንግስታት የፖለቲካ እገዛ በማድረግ።
  • ኢራን - በመሳሪያ በጦር አማካሪዎች እና በተዋጊ ጦር አቅርቦት
  • ሄዝቦላህ- በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎችን በማቅረብ
  • የሺአ ሙስሊም ታጣቂዎች- በኢራን በኩል ከኢራቅ አፍጋኒስታንና ከየመን በመመልመል

በተቃዋሚዎች በኩል

•ቱርክ -በመሳሪያ አቅርቦት፤ በወታደራዊና ፖሊቲካዊ ድጋፍ

•የባህረሰላጤ የአረብ ሃገራት፤-በገንዘብና በመሳሪያ አቅርቦት

•አሜሪካ- በመሳሪያ በስልጠና የለዘብተኛ ቡድኖች ወታደራዊ ድጋፍ

•ዮርዳኖስ፡ በቁሳዊ ድጋፍና በስልጠና

ገራቱ ለምን በጦርነቱ መሳተፍ ፈለጉ ?

ሩሲያ ብቸኛው የሚዲትራኒያን የባህር ኃይል ጦር ማዘዣና በላቲካ ግዛት ባለው የአየር ጦር ማዘኛ ምክኒያት በሶርያ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቅም ታገኛለች

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት በጦርነቱ ቁልፍ ተዋናይ በመሆን በመካከለኛው ምስራቅና በዓለምቀፍ ጉዳዮች ተጽዕኖ የመፍጠር አቅሟንም ማሳደግ ትፈልጋለች።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የሩሲያ ተሳትፎ የአሳድን እጣ ፈንታ በመቀየር በኩል ትልቅ እገዛ አድርጓል

ኢራን ከአረብ ሀገራት ሶሪያን እንደዋነኛ አጋሯ ታያታለች፤ወደ ሂዝቦላህና እና ወደ ሊባኖስ የምትልካቸው መሳሪያዎችም የሚያልፉት በሶሪያ በኩል ነው።

ሳዑዲአረቢያ ኢራን ከህዝብ ቁጥሯ አብዛኛቹ ሱኒዎች በሆኑባት ሶሪያ የምትፈጥረውን ተጽእኖ ትቃወማለች።

አሜሪካ ተቃዋሚዎችን መደገፍ የጀመረችው የአሳድን ጨካኔ የተሞላበት ተግባር ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም በሚል ነው

ይሁንና ባለፉት ሁለት ዓመታት አይ ኤ ስን በማዋጋት ላይ አተኩራለች፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕም አሳድን ከስልጣን ማውረድ ቀዳሚ አጀንዳቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል።

'' የጠላቴ ጠላት ወዳጄ'' ነው የሚለው ብሂል አይ ኤስ ጋር አይሰራም፤ የአሳድ መንግስትሞ ሆነ ጦርነት የገጠሙትን ተቃዋሚዎች በጠላትነት ፈርጇቸዋል።

ስለዚህ ጦርነቱን የገጠሙት የሶርያ ተቃዋሚዎች ከመንግስት፡ ከደጋፊዎቹና ከአይ ኤስ ፤የአሳድ መንግስት ደግሞ ከተቃዋሚዎችና ከአይ ኤስ፡ አይ ኤስ ደግሞ ከማንም ጋር ሳይወግን ሁለቱንም ጎራዎች በመዋጋት ነው።