ጉንዳኖች የሚረጩትን ንጥረ-ነገር በመጠቀም የሚንቀሳቀሰው አዉቶብስ

ቲም ፋስት Image copyright CHRIST CLIJSEN
አጭር የምስል መግለጫ የቲም ፋስት አባላት ለኣብነት የሠሩት አውቶብስ

የተወሰኑ ተማሪዎች ከተለዋጭ ታዳሽ ነዳጆች ይልቅ ተግባራዊና የበለጠ ተግባራዊ እና ዘላቂነት ያለው ኃይል ለማከማቸት የሚያስችል መፍትሔ ኣግኝተዋል ።

ብልሆቹ ወጣቶች ዓለምን በኣንድ አዉቶብስ በመጀመር ቀስ በቀስ ዓለምን የመለወጥ ፍላጎት እንዳላቸዉ ገልጸዋል ።

ከኤይንድሆቨን የቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር የተቆራኘ "ቲም ፋስት" ከተሰኘ ኩባንያ የመጣዉ ሉካስ ቫን ካፕሊለን ፈጠራቸዉን እንዲህ በማለት ገልጿል

" የሃይድሮጂን ዓይነት ግልጋሎት ያለዉ፤ ነገር ግን እጅግ በጣም ርካሽ መፍትሄ ሆኖ የሚያገለግለውን የዓለምን አውቶቡስ ሠርተናል" በመቀጠልም "የራሳችንን የወደፊት ሕይወት እየገነባን ነው" ብሏል።

አብረዉት የሚማሩትም 40 የሚሆኑት ተማሪዎች በከባቢ አየር ላይ የሚከሰተውን ዓለም አቀፋዊ ትግል ለማገዝ የሚረዳውን የነጻ ኃይል ማጓጓዣ አማራጮችን ለማልማት ጥረት እያደረጉ ነው።

እነሱም ወደፊት የራሳቸውን ሥራ የመሥራት ፍላጎት ስላላቸዉ በዚህ ዘርፍ ባለሙያ ለመሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

ፎርሚክ አሲድ በመባል የሚታወቀዉ አሲድ በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እሱም በጉንዳኖች እና በሌሎች ነፍሳት መንደፊያ በኩል የሚተላለፍ ሲሆን የጉንዳን የላቲን ቃሉ ደግሞ "ፎርሚካ" በመባል ይታወቃል።

በተጨማሪም ይህ ቀላል የካርቦክሲሊክ አሲድ (በኬሚካላዊ አወቃቀሩ ኤች ሲ ኦ ኦ ኤች የተሰኘዉ) በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳ ምርት ማቀነባበሪያ ድርጅቶች፣ የከብቶች ምግብ ከመበላሸት እንዲከላከልና ኣንዳንድ ግዜም ደግሞ የቤት ቧንቧ ሻጋታ ማስወገጃዎች ውስጥም ይገኛል።

Image copyright TEAM FAST
አጭር የምስል መግለጫ በኃይድሮዛይን የተሞላዉ ተጎታች በአውቶብሱ የጀርባ ኣካል ላይ ይያያዛል

የቲም ፋስት ቡድን አሲዱ በቀላሉና በጥሩ ሁኔታ ለሃይድሮጂን የነዳጅ ሴሎች የሚስፈልጓቸዉን ነገሮችና የኤሌክትሪክ መኪናዎች የሚጠቀሙበትን ኃይል ማጓጓዝ የሚቻልበትን መንገድ አግኝተዉታል።

ይህም ነዳጅ ቡድኑ እንደሰየመዉ ኃድሮዛይን የነዳጅ ፈሳሽ ሲሆን ከተለመደዉ ነዳጅ ጋር ሲነጻጸር በቀላሉ ማጓጓዝና ተሽከርካሪዎችን ለመሙላት ጊዜ የማይፈጅ ነዉ።

በዋነኝነት ይህንን ነዳጅ ልዩ የሚያደርገዉ ደግሞ በጣም ንፁህ መሆኑ ነው።

ቫን ካፕሊን እንደገለፀው "የጭስ ማዉጫዉ ካርቦን ዳይኦክይሳድና ውሃ ብቻ ብቻ ነዉ የሚያስወግደዉ" በመቀጠልም "እንደ ናይትሪክ ኦክሳይድ፣ጥላሸት ወይም ሰልፈሪክ ኦክሳይድ የመሳሰሉ ሌሎች ጎጂ ጋዞችን ኣያስወግድም"

ይህንን ጽንሰ ሃሳብ ኣዋጪነት ለማረጋገጥ በኔዘርላንድ አንድ የኤሌክትሪክ አውቶብስ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ በተለመዱት የአውቶብስ መስመሮች፣ በንግድ ሥራዎችና በኢንዱስትሪ ኤግዚብሽን ማዕከል ለእይታ ይቀርባል።

ቪዲኤል በመባል የሚታወቀዉ የአውቶቡስ ኣምራች የዚህን አውቶብስ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያዉን የሠራ ሲሆን አውቶብሱ ተጨማሪ ኃይል ከኋላዉ በሚገኘዉ ተጎታች ፎርሚክ አሲድ በማግኘት ይጓዛል።

"300 ሊትር የመያዝ ኣቅም ስላለዉ የአውቶቡሱን መስመሮችን በ 200 ኪ.ሜ (180 ማይል) እናራዝማለን ፤ ሆኖም የታንኩን የመያዝ ኣቅም በቀላሉ መጨመርም እንችላለን" በማለት ቫን ካፕሊን ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።

Image copyright BART VAN OVERBEEKE FOTOGRAFIE
አጭር የምስል መግለጫ ኤሌክትሪከ መኪና ወይስ አውቶብስ ?

በአሁኑ ወቅት የአውቶቡሶች የሃይድሮጂን ነዳጅ ሴሎች እስከ 400 ኪ.ሜ መንገድ የመሄድ ኣቅም አላቸው ።

ይሁን እንጂ መኪና ከመሆን ይልቅ አውቶቡስ መነደፍ ያለበት ለምንድን ነው?

"መኪና ከሠራን ከኤሌክትሪክ መኪና ከሚሠሩ ድርጅቶች ጋር ልንወዳደር ነዉ ነገር ግን በባትሪ ኃይል የሚሄዱ መኪኖች ለብዙ ሰዎች ጥሩ መፍትሄ እንደሆኑ እናምናለን" በማለት ቫን ካፕሊን ሓሳቡን አካፍሏል።

"ይሁን እንጂ የአውቶቡስ ኩባንያዎችን ፍላጎት የሚያሟላ አውቶቡስ እስከ 400 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችልና በፍጥነት ነዳጅ የሚሞላ አዉቶቡስ ማቅረብ እንደምንችል ብናሳይ ግን የሃይድሮዛይንን አቅምና ዘላቂነት ውድድር በሌለበት አሳየን ማለት ነዉ" በማለትም ጨምረው ተናግረዋል።

ሃይድሮዛይን የሚፈጠረዉ በውሃ (ኤችቱኦ) እና በካርቦን ዳይኦክሳይድ (ሲኦቱ) በሚደረገዉ የኬሚካል ልዉውጥ ነው ።

"በሃይል ማመንጫው ውስጥ ውሃና ካርቦን ዳይኦክሳይድ የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ይጣበቃል፤ይህ ቀጥተኛና ዘላቂ የኤሌክትሪክ ኬሚካላዊ ሂደት ነው" በማለት ቫን ካፕለን ያስረዳል ።

ሃይድሮዛይኑ በሌላ ኃይል ወደ ሃይድሮጅን እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ተከፋፍሎ በመቀየር እሱም ቲም ፋስት የፈጠራ ፈቃድ ለማግኘት እየሞከሩለት ባለዉ ሪፎርመር ብለዉ በሰየሙት መቀበያ ዕቃ ዉስጥ ይገባል ።

ይህ አዲስ ሪፎረመር ከዚህ በፊት ከተለመዱት ሪፎርመሮች ለየት የሚያደርገዉ በአንድ አስረኛ የሚያንስ ሆኖ በዚህም ምክንያት ለመጀመሪያ ጊዜ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ተግባራዊ መሆን ችሏል።

ከዚያም ሃይድሮጂኑ ወደ ነዳጅ ክፍል ዉስጥ ተጨምሮ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ከኦክሲጂን ጋር እንዲዋሃድ ይደረጋል እሱም ለመኪናዉ ሞተር ኃይል ማመንጨት ይጀምራል ።

አጭር የምስል መግለጫ አየር በማይበክል ነዳጅ የሚሽከረከሩ አውቶብሶች በከተማው መንገዶች እየበዙ ነዉ

የቪዲኤል ኢኔብሊንግ ትራንስፖርት ሶሉሽንስ ሥራ ኣስኪያጅ የሆኑት ሜኖ ክሌይንጌልድ ድግሞ "አየር የማይበክሉ ኣዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ ለማስፋፋት ያለማሳለስ እየፈለግን ነዉ" ብለዋል ።

ቀጥሎም "የፎርሚክ አሲድ ወደ ሃይድሮጅን መከፋፈል ከተስፋ ሰጪዎቹ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መሃል አንዱ ነው" በማለትም ገልጸዋል ።

ጥያቄው ይህ ቴክኖሎጂ ግን በርግጥ ይሳካል ማለት ነዉ?

"በዓለም ከሚገኙት የተለመዱትን የነዳጅ ማደያዎች ወደ የሃይድሮዛይን ማደያዎች ለመቀየር ወደ 35,000 ዩሮ (1 ሚልየን የኢትዮጵያ ብር ገደማ) የሚፈጅ ሲሆን ይህም ደግሞ ቧንቧዎቹን መተካትና ታንከሮቹን መከላከያ ቀለም መቀባትን ያካትታል " ይላል ቫን ካፕለን።

"በአሁኑ ጊዜ ኔዘርላድ ዉስጥ ሃይድሮዛይን ከቤንዚን ነዳጅ ቢረክስም ከናፍጣ ግን ይወደዳል፤ ወደፊት ደግሞ ዋጋዉ እየቀነሰ ይመጣል ብለን እናስባለን" ብሏል።

ምንም እንኳን ይህ አውቶቡስ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ቢያመነጭም ቲም ፋስት ግን ከኣየር ወይም ከጭስ ማዉጫ እንደመሳሰሉት ካሉ ምንጮች ሃይድሮዛይን ለመሥራት ስለሚጠቀሙበት ተጨማሪ ካርቦን ዳይኦክሳይድ እንደማያመነጩ በማሳወቅ የገጠመ የካርቦን ዑደት እንደሆነ ገልጸዋል ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ኣንዳንድ የጉንዳን ዘሮች ኣራሳቸዉን ለመከላከል ፎርሚክ ኣሲድ ያመነጫሉ

አንዳንድ ባለሙያዎች ቴክኖሎጂው ተስፋ እንዳለዉ ያምናሉ ።

የደች ኢንስትትዩት የኃይል ምርምር ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ቫን ዲ ሳንደን "ቲም ፋስት ጥሩ ሥራ ነዉ የሠሩት" ብለዋል ።

"እጅግ በጣም አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ላይ ነዉ የሚሠራው፤ እሱም ታዳሽ ኃይልን ተጓጓዥ በሆነ መልኩና መጠቀም በሚቻልበት መንገድ መሠራቱ ነዉ" በማለትም ተናግረዋል ።

በርካታ ኩባንያዎችም ፕሮጀክቱን ደግፈዋል።

የተማሪዎቹ ቁርጠኝነት እጅግ አስደናቂ የሚያስደንቅ ነዉ ከ 40ዎቹ መካከል 15ቱ ሙሉ ጊዜያቸዉን ሰዉተዉ እዚህ ፕሮጄክት ላይ እየሠሩ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ በሳምንት ከ 20 እስከ 325 ሰዓታት ይሠራሉ ።

ለዚህ ፕሮጄክት ከዩኒቨርስቲዉ ምንም ዐይነት ነጥብ እንደማያገኙበት በተለይም ደግሞ የተሟላ እዉቀት ከዩኒቨርሲቲ ብቻ እንደማይገኝና ተግባራዊ ሥልጠናዎች ኣስፈላጊ እነደሆኑም ቫን ካፕለን ይናገራል።

" የራሳችን የወደፊት ሕይወታችንን እየገነባን ነዉ " በማለትም ያጠቃልላል ።

ተያያዥ ርዕሶች