አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 1

ለአእምሮዎ ጊዜ በመስጠት ይህንን እንቆቅልሽ ይፍቱ።

አንደኛ እንደሚወጡ ተስፋ እናደርጋለን።

እንቆቅልሽ 1

ሰባት የወርቅ ጥፍጥፎች አልዎት እንበል። አንዱ ግን ትክክለኛ ወርቅ ካለመሆኑም በላይ ክብደቱም ከእውነተኛዎቹ ወርቆች ያነሰ ነው። በግራና ቀኝ ዕቃ በማስቀመጥ የሚመዝን አንድ ሚዛን ቢኖሮትም ከሁለት ጊዜ በላይ መመዘን አይችሉም።

እንዴት አድርገው ወርቅ ያልሆነውን ይለያሉ?

መልሱን ለማግኘት ወደታች ይውረዱ

መል

ሶስት ሶስት የወርቅ ጥፍጥፎቸን በሁለቱም የሚዛኑ ጎኖች ላይ ያስቀምጡ።

ሁለቱ እኩል ከመዘኑ ሚዛን ላይ ያልተቀመጠው ዘንግ ወርቅ አይደለም ማለት ነው።

ካልሆነ ግን በአንድ ጎን አነስተኛ ክብደት ይኖረዋል ማለት ነው። አነስተኛ ክብደት ካለው የሚዛኑ አንድ ወገን የሚገኙትን ሶስት የወርቅ ጥፍጥፎችን ያንሱ።

ከሶስቱ ዘንጎች ሁለቱን በሚዛኑ ግራና ቀኝ በኩል ያስቀምጡ።

ሚዛኑ ላይ ያሉት የወርቅ ጥፍጥፎች እኩል ከሆኑ ሚዛን ላይ ያልተቀመጠው ሶስተኛ ዘንግ ወርቅ አይደለም።

ካልሆነ ደግሞ ሚዛን ላይ ካሉት ውስጥ ክብደቱ አነስ ያለው ወርቅ እንዳልሆነ ለመለየት ቻልን ማለት ነው።