አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 2

አዕምሮዎን ይፈትኑ... ከቢቢሲ አማርኛ የቀረበውን ይህን እንቆቅልሽ መመለስ ይችላሉ?

ማን እየዋሸ መሆኑን መለየት ይችላሉ?

መልካም ዕድል!

ጨዋታ Image copyright Getty Images

እንቆቅልሽ 2

ማሞ ከበደ ውሸታም ነው አለ።

ከበደ ደግሞ አበበ ውሸታም ነው አለ።

አበበ ደግሞ ከበደም ማሞም ውሸታሞች ናቸው አለ።

ታዲያ ከሦስቱ አንድ ሰው እውነቱን ተናግሯል። የትኛው እውነቱን ተናገረ?

ማብራሪያ፡ ለዚህ እንቆቅልሽ ሲባል ለመነሻ የተወራውን እውነት ቢሆን ወይም ውሸት ቢሆን ብለን በማሰብ ለመፍታት እንሞክር።

መልሱን ከታች ማግኘት ይችላሉ

መል

እንቆቅልሹን የፈጠረውአሌክስ ቤሎስ

ከበደ ብቻ ነው እውነቱን የተናገረው።

እውነት ተወራ ብለን ብንነሳና አበበ የተናገረው እውነት ቢሆን ብለን እንጀምር። አበበ በተናገረው መሠረት ከበደም ማሞም ውሸታሞች ናቸው። ነገር ግን ማሞ ከበደ ውሸታም ነው ቢልም እሱ አበበ በተናገረው መሠረት ውሸታም ስለሆነ ስለ ከበደ የተናገረውን ሐሰት በማድረግ ከበደን እውነተኛ ያደርጋል። በተጨማሪም የከበደ እውነተኛነት አበበን ውሸታም በማለቱ ይረጋገጥልናል። ምክንያቱም አበበ ከበደንም ጭምር ውሸታም በማለቱ ስለ ማሞ የተናገረው እውነተኛ ቢሆንም አብሮ ከበደን ማካተቱ ግን ውሸታም ያደርገዋል።

ውሸት ነው የተወራው ብለን በምንነሳበት ጊዜ ደግሞ አበበ ስለ ከበደና ስለ ማሞ የተናገረው ውሸት ቢሆን ብለን እናስብ። አበበ ማሞም ከበደም ውሸታሞች ናቸው ሲል ውሸቱን ከሆነ ብለን እናስላው። አበበ ውሸታም በመሆኑ የተናገረውን ሐሰት በማድረግ ማሞንም ከበደንም እውነተኛ ያደርጋል። በመቀጠልም ከበደ አበበን ውሸታም በማለቱ እወነተኛ ነው ማለት ይሆናል። ነገር ግን ማሞ ከበደን ውሸታም በማለቱ የማሞን እውነተኛነት ያፈርሰውል ማለት ነው ምክንያቱም የከበደን እውነተኛነት በተናገረው መሠረት ስላረጋገጥን።

ስለዚህ ከሦስቱ መካከል ሁልጊዜ እውነቱን ሲናገር ነበረው ከበደ የሚሆነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ