አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 5

ራስዎን ይፈትኑ።

ነፍሰ ገዳዩን መለየት ይችላሉ?

የዛሬውን እንቆቅልሽ ለመፍታት ይዘጋጁ

በከረሜላ የተሰሩ ፖሊሶች Image copyright Getty Images

እንቆቅልሽ 5

አምስት ሰዎች አሉ፤ ከአምስቱ መካከላ አንዱ ሽጉጥ ተኩሶ ሌላኛውን ገድሎታል።

ስለአምስቱ ሠዎች ያሉ እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው።

1. አየለ በግድያው እጃቸው ከሌለበት ሰዎች መካከል ከአንዱ ጋር ትናንት ማራቶን ሮጧል።

2. ታደለ ወደ ከተማ ከመምጣቱ በፊት አርሶአደር መሆን ያስብ ነበር።

3. ሳሙኤል የኮምፒውተር ባለሙያ ሲሆን በሚቀጥለው ሳምንት የሰለሞንን አዲስ ኮምፒውተር ለመግጠም አስቧል።

4. ከጥቂት ቀናት በፊት የገዳዩ እግር ተቆርጧል።

5. ሰለሞን አሰፋን የተዋወቀው ከስድስት ወራት በፊት ነው።

6. አሰፋ ከግድያው በኋላ ራሱን ከሰዎች አግልሏል።

7. አየለ አብዝቶ ይጠጣ ነበር።

8. ሰለሞንና ሳሙኤል የመጨረሻ ኮምፒውተራቸውን በጋራ ገጥመዋል።

9. ገዳዩ የአሰፋ ወንድም ሲሆን ሲያትል ውስጥ አብረው አድገዋል።

ይህ ምርጥ የወንጀል መርማሪ ሊያስብልዎ የሚችል አጋጣሚ ነው። ገዳዩ ማነው?

መልሱን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

መል

ሳሙኤል ነው ታደለን የገደለው።

እነዚህን ነጥቦች ልብ ይበሉ፡

1. አሰፋ የገዳዩ ወንድም በመሆኑ ገዳዩ እሱ ሊሆን አይችልም።

2. አየለ ትናንት በማራቶን ሩጫ ላይ በመሳተፉ ገዳይ ሊሆን አይችልም ፤ ምክንያቱም ገዳዩ በቅርቡ እግሩ በመቆረጡ በማራቶን ላይ ሊሳተፍ አይችልም።

3. አሰፋና ሰለሞን በቅርቡ በመተዋወቃቸውና ገዳዩ ደግሞ ከአሰፋ ጋር አብሮ አደግ በመሆኑ ሰለሞን ገዳይ አይደለም።

4. በዚህም ምክንያት ቀሪዎቹ ሳሙኤልና ታደለ ናቸው።

ሳሙኤል በህይወት ስላለ (በቀጣይ ሳምንት ኮምፒውተር ለመግጠም ማቀዱ በህይወት እንዳለ ያሳያል) እሱ ገዳይ መሆኑን ያሳያል። ታደለም ከአሰፋ ጋር አብሮ አደግ አይደለም። አሰፋ አየለና ሳሙኤል በህይወት አሉ። ሳሙኤል የሰለሞንን ኮምፒውተር በሚቀጥለው ሳምንት ሊገጥምለት በመሆኑ ሰለሞንም በህይወት አለ። ይህ ደግሞ ሳሙኤል ታደለን መግደሉን ያሳያል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ