አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 6

የዛሬውን እንቆቅልሽ ለመሞከር ተዘጋጅተዋል?

ፍጥነት ይፈልጋል። እርስዎስ በፍጥነት እንቆቅልሹን ለመፍታት ይችላሉ?

መልካም ዕድል!

ድብ Image copyright Getty Images

እንቆቅልሽ 6

ለአንድ ተልዕኮ ተሰማርተዋል እንበል። ወደ ደቡብ አቅጣጫ 5 ኪሎሜትር ተጓዙ፣ ቀጥሎ ወደ ምዕራብ 5 ኪሎሜትር ተጓዙ፣ በመጨረሻም ወደ ሰሜን 5 ኪሎሜትር ከተጓዙ በኋላ ራስዎን መጀመሪያ ከተነሱበት ቦታ ላይ አገኙ።

በተልዕኮዎ ወቅት ድብ አይተዋል። ድቡ ምን ዓይነት ቀለም ነበረው?

መልሱን ለማግኘት ከታች ይመልከቱ

መልስ

ድቡ ነጭ ነው።

ዓለማችን ላይ ወደ ደቡብ 5 ኪሎሜትር፣ ምዕራብ 5 ኪሎሜትር እና ሰሜን 5 ኪሎሜትር ተጉዘው የተነሱበት ቦታ የሚደርሱት በሰሜን ዋልታ አካባቢ ብቻ ነው።

በሰሜን ዋልታ የሚገኙት ድቦች ደግሞ ነጫጭ ናቸው።

ይህ እንቆቅልሽቱዴይ ፕሮግራም በኩል የተወሰደ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ