አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 7

የዛሬውን እንቆቅልሽ በመፍታት ራስዎን ይፈትኑ።

ንግሥቲቱን መርዳት ይችላሉ?

እስኪ ይሞክሩ።

ንግስት Image copyright Getty Images

እንቆቅልሽ 7

የካርታዋ ንግሥት ብስኩቷን ካስቀመጠችበት አጥታዋለች።

በዙሪያዋ ያሉትን ብትጠይቅ ብስኩቷን ያልበሉት እውነቱን እንደሚነግሯት፤ የበሉት ደግሞ እንደሚዋሿት እርግጠኛ ሆናለች።

አምስቱን ስትጠይቃቸው የሚከተለውን ምላሽ ሰጧት...1ኛው፡ 'አንዳችን በልተነዋል'

2ኛው፡ 'ከመሃላችን ሁለቱ በልተዋል'

3ኛው፡ 'ከመሃላችን ሦስቱ በልተዋል'

4ኛው፡ 'ከመሃላችን አራቱ በልተዋል'

5ኛው፡ 'አምስታችንም በልተናል'

ምን ያህሎቹ ሃቀኛ ነበሩ? የትኛው/የትኞቹ ናቸው እውነቱን ተናገሩ?

መልሱን ለማግኘት ከታች ይመልከቱ

መልስ

መልሱ - አራተኛው ተጠያቂ ብቻ ነው እውነቱን የተናገረው። ለዚህ ጥያቄ በተለያየ መንገድ ምላሽ መስጠት ቢቻልም አንዱ መንገድ የሚከተለው ነው።

ምንም እንኳን የተጠየቁት በሙሉ የተለያየ ምላሽ ቢሰጡም፤ የአንዱ መልስ ብቻ ነው እውነተኛ የሚሆነው።

አንዱ ብቻ እውነቱን ከተናገረ ደግሞ አራቱ ዋሽተዋል፤ ብስኩቱን የበሉት አራቱ ናቸው። ስለዚህ አራተኛው ተጠያቂ ብቻ ነው እውነቱን የተናገረው።

ሁሉም ተጠያቂዎች ቢዋሹ ኖሮ አምስቱም ብስኩቱን በልተውታል ማለት ይቻል ነበረ። ይህ የአምስተኛውን ተጠያቂ መላሽ እውነት ቢያደርገውም ተቃርኖ ግን አለው።

ስለዚህ አራተኛው ብቻ ነው እውነቱን በትክክል የተናገረው።

ይህ እንቆቅልሽ በዴይሊ ፕሮግራም በኩል ከካምብሪጅ ዩንቨርሲቲ ኤን አር አይ ሲ ኤች ፕሮጀክትየተገኘ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ