አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 8

ራስዎን ይፈትኑ።

የዛሬውን እንቆቅልሽ ለመስራት ይሞክሩ። መልሱን ያገኙታል?

መልካም ዕድል!

በትልቅ ቀዳዳ የሚያይ ሰው Image copyright Getty Images

እንቆቅልሽ 8

ወደ ጠላት የሚሳኤል ማስወንጨፊያ ሥፍራ ለመግባት የሚያስችሎትን ምስጢራዊ የይለፍ ቃል ለማወቅ ጥረት እያደረጉ ነው እንበል።

አንድ ሳይንቲስት ወደ በሩ ይደርሳል፤ በዚህ ወቅት በር ላይ ያለው ጠባቂ "አስራ ሁለት?" ሲል ይጠይቀዋል። ሳይንቲስቱም "ስድስት" ብሎ ሲመልስ ወደ ውስጥ እንዲገባ ይፈቅድለታል።

ሌላ ሳይንቲስትም ተከትሎ ይመጣል፤ በዚህ ወቅት ጠባቂው "ስምንት?" ብሎ ሲጠይቀው ሁለተኛው ሳይንቲስት "አራት" ብሎ ይመልስና ወደ ውስጥ እንዲገባ ይፈቅድለታል።

መቼም ከዚህ በመነሳት ወደ ውስጥ ለመግባት የሚያስችሎትን ምስጢራዊ የይለፍ ቃል ደርሰውበታል!

ስለዚህ ወደ መግቢያው ደርሰው ጠባቂው "ዘጠኝ?" ሲል ይጠይቃል። ታዲያ ለምንድን ነው እርሶ "አራት ተኩል" ብለው ሲመልሱ ጠባቂው የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ደወሉን የደወለው?

መልሱን ለማግኘት ከታች ይመልከቱ

መል

ለጠባቂው ሊነግሩት የሚገባው መልስ ሶስት ነበር።

ምክንያቱም እንዲገቡ የተፈቀደላቸው ሳይንቲስቶች ጠባቂው የሚጠይቀውን ቁጥር ግማሽ ሳይሆን የሚመልሱለት የሚጠይቀውን ቁጥር የሆሄያት ብዛት ስለሆነ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ