አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 10

ይህንን እንቆቅልሽ ለመስራት ተዘጋጅተዋል?

ብዮችዎን እንደሚያገኙ ተስፋ አለን።

መልካም ዕድል

ብይ Image copyright Getty Images

መልመጃ 10

አያድርገውና የሞት የተፈረደበት እስረኛ እንደሆኑ እናስብ። ነገር ግን ዳኛ አንድ ቀላል ጨዋታ ተጫውተው ህይወትዎትን እንዲያተርፉ ዕድል ሰጠችዎ።

ዳኛዋ 50 ጥቁር ብዮች፣ 50 ነጭ ብይ እና ሁለት ባዶ ጉድጓዳ ሳህኖችን ትሰጥዎታለች።

እሷም "መቶዎቹን ብዮች በሁለቱ ሳህኖች ውስጥ ከፋፍለው ያስቀምጧቸው። ሁሉንም ብይ እስከተጠቀሙ ድረስ በየትኛውም ሁኔታ መከፋፈል ይችላሉ።"

" ከዚያም ዓይኖችዎ በጨርቅ ተሸፍነው የሳህኖቹ ቦታ እንዲቀያየር ይደረጋል። በመጨረሻም አንዱን ሳህን በመምረጥ ከውስጡ አንድ ብይ ያነሳሉ። የተነሳው ብይ ነጭ ከሆነ በሕይወት ይተርፋል፤ ጥቁር ከሆነ ደግሞ የሞት ፍርዱ ተፈፃሚ ይሆናል" ትላለች።

እንዴት አድረገው ብዮቹን ቢከፋፍሉ ነጭ ብይ የመግኘት ዕድልዎን ከፍ በማድረግ ህይወትዎን ማትረፍ ይችላሉ?

መልሱን ለማግኘት ከታች ይመልከቱ

መል

አንዱን ነጭ ብይ በአንዱ ሳህን አድርገው ሌሎቹን ብዮች ደግሞ በሌላኛው ሳህን ያስቀምጡ (49 ነጭና 50 ጥቁር)።

በዚህ መንገድ አንድ ነጭ ብይ የያዘውንና ህይወትዎትን የሚያተርፈውን ብይ የመምረጥ እድልዎት 50 በመቶ ነው።

ሌላኛውን ማስቀመጫ ቢመርጡም ከ49ኙ ነጭ ብይዎች አንዱን በመምረጥ ህይወትዎትን የማትረፍ ዕድልዎ 50/50 አካባቢ ይሆናል።

አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 9

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ