ትራምፕ ለእርዳታ አጃቸውን ወደ ኮንግረሱ ዘርግተዋል

Image copyright Getty Images

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ቢያንስ የ5.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ኮንገራሳቸውን ሊጠይቁ እንደሆነ ተሰምቷል። የቴክሳስ ክፍለ ግዛት ገዥ ግሬግ አቦት ከዚህ ቀደም ብሎ በጎርፍ የተጎዳው የቴክሳስ ክፍል ለማገገሚያ በትንሹ 125 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሻ ተናግረው ነበር።

በቴክሳስ ሂዮስተን ክፍለ ግዛት ሀሪኬን ሀርቪይ የተባለው ጎርፍ እና ነፋስ የቀላቀለው ተፈጥሯዊው አደጋ ባደረሰው ጥፋት እስካሁን ቢያንስ 39 ሰዎች መሞታቸውን እና 311 ሺህ ሰዎች ደግሞ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚሹ ተዘግቧል። ቢሆንም ግን እስካሁን እርዳታው በምን ፈዕትነት ሊደርስ እንደሚችል የታወቀ ነገር የለም።

ነጩ ቤት እንዳስታወቀው ከሆነ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከግል ኪሳቸው በማውጣት 1 ሚሊዮን ዶላር ለአደጋው ተጎጂዎች ረድተዋል።

ከጎርፍ ጥፋቱ በኋላ ሰዎችን ከማዳን ወደ መልሶ መገንባት አቅጣጫውን ያደረገው የአሜሪካ መንግስት የአደጋው ተጎጂዎች በይፋ እስካልተነገራቸው ደረስ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ አሳስቧል።

ቀደም ብሎ የነጩ ቤት ሰራተኛ እንደተናገሩት ወደ መቶ ሺህ የሚሆኑ ቤቶች በሀሪኬን ሀርቪይ ተፈጥሯዊ አደጋ ምክንያት ተጎድተዋል። በይፋ አካባቢያቸውን ለቀወ እንዲወጡ ከተነገራቸው 779 ሺህ የቴክሳስ ነዋሪዎች በተጨማሪ 980 ሺህ የሚሆኑት በፈቃደኝነት ቤታቸውን ለቀው መውጣታቸውን የአሜሪካ ሀግር ውስጥ ደህንነትን ጠቅሶ ሬውተርስ ዜና ወኪል ፅፏል።

የአሜሪካ ፌዴራል አደጋ ማስተባበር ኤጀንሲ እንደገለጠው ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን ከአደጋው አትርፎ ወደ 90 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ አስቸከወይ ጊዜ እርዳታ እንዲደርግላቸው ረድቷል። ኤጀንሲው ሲናገር አንዳንድ ሰዎች አደጋውን ምክንያት በማድረግ ሰዎችን ሊያጭበርብሩ እሞከሩ እንደሆነ አስረግጧል።

Image copyright Getty Images

ከአደጋው በኋላ

የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ አደጋው በደረሰበት ቦታ የሚኖሩ ሰዎችን ከውሃ ባክቴሪያ እና መሰል አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል። አሁን ትልቁ ችግር ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ነው ሲልም ዘግቧል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ያለ ንፁህ መጠጥ ውሃ መቅረታቸውንም አክሏል። በምስራቅ ሂዮስተን የሚገኝ ሆስፒታል በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ምክንያት መዘጋቱም ታውቋል።

በአደጋው የተጠቁ አካባቢዎችን ተዘዋውረው የጎበኙት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀዳሚውት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ እንደገና ቅዳሜ ዕለት ወደ ቴክሳስ ተመልሰው ሁኔታቸውን እንደሚቃኙ ተነግሯል።

እንደ አሜሪካ ብሕራዊ የአየር ሁኔታ አገለግሎት ዘገባ ሀርቪይ አሁን ላይ አቅሙ እየቀነሰ መጥቷል። በመጪው ቅዳሜም ወደ ኦሃዯ አካባቢ ሊበተን እንደሚችልም ይጠበቃል።

በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በአርካንሳስ፥ ሚሲሲፒ፥ ቴነሲ፥ ኬንታኪ፥ ትክሳስ እና ሉዊዚያና ከበድ ኣለ ዝናብ የሚጠበቅ ሲሆን የጎርፍ አደጋ ማስጠንቀቂያ አዋጅም ታውጇል።