መንግስታዊው "የፍቅር ቀን "

Image copyright ROBERTO SCHMIDT
አጭር የምስል መግለጫ ሚሌኒየሙ ከተከበረ ከአስር ዓመት በኋላ አዲስ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአስር ቀናት በፊት መከበር ይጀምራል

መንግስት የኢትዮጵያን የ2010 ዓ.ም አዲስ አመት አቀባበል በልዩ ዝግጅት ለማክበር ያወጣውን እቅድ ዛሬ ተጀምሯል።

"መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው" በሚል መሪ ቃል ከሚሌኒየሙ በዓል በኋላ የተሰሩ መልካም ስራዎችን እዘክራለሁ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታትም ህዝቤን በአስር ቀናት አነቃቃለሁ ብሏል።

የበዓላቱ ሁሉ ጅማሬ ደግሞ ፍቅር ሆኗል። ስለዚህ ዛሬ በኢትዮጵያ አረፋም ፍቅርም በጋራ ይከበራሉ።

ከዛሬ እስከ ጳጉሜ 5 ያሉት ቀናት እንዲህ ተሰይመዋል

  • ነሃሴ 26----የፍቅር ቀን
  • ነሃሴ 27----የእናቶች ቀን
  • ነሃሴ 28----የአረጋውያን ቀን
  • ነሃሴ 29----የአንድነት ቀን
  • ነሃሴ 30----የንባብ ቀን
  • ጳጉሜ 1----የአረንጓዴ የልማት ቀን
  • ጳጉሜ 2----የመከባበር ቀን
  • ጳጉሜ 3----የሀገር ፍቅር ቀን
  • ጳጉሜ 4----የሰላም ቀን
  • ጳጉሜ 5----የኢትዮጵያ ቀን

ግን ለብዙኃን ጥያቄው የበዓሉ ፋይዳ ምንድነው ዛሬ የሚከበረውስ ምን ዓይነት ፍቅር ነው የሚል ነው ?

ምክኒያቱም ጳጉሜ 3 ደግሞ ለ"ሀገር ፍቅር" ተሰይሟል።

የኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ደ/ር ነገሪ ለንጮ ሁነቶቹ የአንድ ወቅት ስራ ብቻ ሆነው የሚቀሩ ሳይሆን በቀጣይነት ተሰርቶባቸው ባህል እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል፡፡

በዓሉም በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ በድምቀት የሚከርበት ለመጪው ዘምንም ቃል የሚገባበት ነው ባይ ናቸው ሚኒስትሩ።

ለበዓሉ አከባበር ደግሞ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ይደረጋል።

ይህ ሁሉ ወጪ አሰፈላጊነቱ ምንድነው? ይላሉ ጦማሪያን- የሆርን አፌርሱ ዳንኤል ብርኃኔ እቅዱ ፋይዳ እንደሌለው የሚገለጽ ጽሁፍ በገጹ ላይ አስፍሯል

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የወሊሶ ካምፓስ መምህር ስዩም ተሾመ ደግሞ "በዓሉ" ፌዝ ነው ይላል።

ተያያዥ ርዕሶች