ኬንያ ድጋሚ ምርጫ እንድታካሂድ ፍርድ ቤት ወሰነ።

አጭር የምስል መግለጫ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ጠቅላይ ፍርድ ምርጫው እንደገና እንዲካሄድ መወሰኑን ተከትሎ የናሳ ፓርቲ ደጋፊዎች ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁሩ ያሸነፉበት ያለፈው ምርጫ ተሽሮ በስድሳ ቀናት ውስጥ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላለፈ።

እ.አ.አ. ነሐሴ 8 2017 የተካሄደው የኬንያ ጠቅላላ እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫ አሁሩ ኬንያታን ድጋሚ መሾሙ ይታወቃል። ነግር ግን የተቃዋሚ ፓርቲው ናሳ ዕጩ ራይላ አዲንጋ ምርጫው በኮምፕዩተር አማካኝነት ተጭበርብሯል በማለት ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ፍርደ በመውሰድ ከሰዋል።

ጉዳዩን ለሳምንት ያህል የመረመረው የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ዛሬ መስረም 1 2017 ባሰታላለፈው ውሳኔ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። ሰባት ዳኛዎችን ያቀፈው የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ዳኛ በህመም ምክንያት መገኘት ባይችሉም አራት ለሁለት በሆነ አብላጫ ድምፅ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈው።

Image copyright KTN NEWS

በውሳኔው መሰረት ኬንያ በድጋሚ በስድሳ ቀናት ውስጥ ምርጫ ማከናወን ይጠበቅባታል።

ውሳኔውን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲው ናሳ ዕጩ ራይላ አዲንጋ ደጋፊዎች በርዕሰ መዲናዋ ናይሮቢ እና የአዲንጋ ደጋፊዎች ይበዙባታል በምትባለው ኪሱሙ ከተማ ደስታቸውን ሲገልፁ ተስተውለዋል።