በማሽን የሚነበበው ባርኮድ ግብይትን በምን መልኩ ቀየሮ ይሆን?

ጆዜፍ ውድላንድ Image copyright IBM
አጭር የምስል መግለጫ ጆሴፍ ውድላንድ እ.አ.አ በ1952 የማንበብያ መሣሪያውን ሙከራ እያስረዱ

እ.አ.አ በ1948 በፊላደልፍያ ከሚገኘው ድሬክሴል ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው ጆሴፍ ውድላንድ አንድ የሱቅ ባለቤት አድካሚ በሆነ መንገድ ክፍያ የሚፈፀምበትን መንገድ በማየት የክፍያን ሂደት 'አውቶማቲክ' በማድረግ ስራን ማፋጠን የሚቻልበትን ሁኔታ ለመቀየስ መነሳሻ ፈጠረለት።

በተለያዩ ምርምሮቹና ስራዎቹ የሚታወቀው ጆሴፍ ከዚህ ቀደምም በጦርነቱ ወቅት 'ማንሃታን' የሚባለው ፕሮጀክት ላይ በአሳንሰር ውስጥ በተሻለ መልኩ ሙዚቃ የማጫወቻ ዘዴንም ቀይሶ የነበረ ቢሆንም ግራ መጋባት ላይ ነበር።

በአጋጣሚም አያቶቹን ለመጠየቅ ወደ ማያሚ ባህር ዳርቻ ባቀናበት ወቅት በእጁ አሸዋውን እየዳሰሰ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት።

የአሸዋውም ስሪት ነጥቦችንና መሥመሮችን በመጠቀም መልዕክት ለማስተላለፍ የሚጠቀሙትን የሙርስ ኮድ ቋንቋን አስታውሰው።

ያንንም መሠረት በማድረግ ቀጫጭንና ወፋፍራም መስመሮችን በመጠቀም አንድን መረጃ ማስቀመጥ የሚቻልበትንም ቀመር ጠነሰሰ።

የምርቱን ዓይነትና ዋጋ ዝርዝር ሊያሳይ የሚችል ክብና የተዥጎረጎረ ቀለም ያለውን ባርኮድ በማስተዋወቅ ማሽኖች የሚያነቡበትንና የሚመዘግቡበትን መንገድ መፍጠር ቻለ።

ምንም እንኳን ይህ ሀሳብ ሊሠራ የሚችል ቢሆንም በጊዜው በነበረው የቴክኖሎጂ ፈታኝነት ሂደቱን ውድ አደረገው።

በጊዜ ሂደት ግን ኮምፒዩተሮች እየረቀቁና የሌዘር ቴክኖሎጂም ዓለምን መቀላቀል ሲጀምር የጆሴፍ ሕልምም መተግበር ጀመረ።

በዓመታት ውስጥ ፈጠራዎች እየተጨመረበት እየተሻሻሉ መጥተዋል።

ክብና የተዥጎረጎረ ቀለም ያለውን "ባርኮድ"ም በ በ1970ዎቹ ጅማሬ ጆርጅ ላውረር የተባለ መሓንዲስ ቅርፁ ወደ አራት ማዕዘን ቢቀየር የበለጠ ጠንካራ ሊሆን እንደሚችል በማወቁ ሊሻሻል ችሏል።

ከዚህም በተጨማሪ በሌዘርና ኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ በመታገዝ የግብይት ሂደትን ሊያፋጥን የሚያስችል ስርዓትም መዘርጋትም ችሏል።

ቸርቻሪዎችና አምራቾች

የጆሴፍ ውድላንድ የባህርዳርቻ ሙከራ ለዓለም አዲስ ሁኔታን የፈነጠቀ የቴክኖሎጂ ግኝት ሆኗል።

ከዓመታትም አድካሚ ጉዞ በኋላ ነበር የአሜሪካ ሱቆች ለምርቶቻቸው ደረጃውን የጠበቀ ኮድ ወይም ዩፒሲ መስጠት የቻሉት።

የጆሴፍ ህልም እውን የሆነውም እ.አ.አ በ1974 በአሜሪካ ኦሃዮ ከተማ ውስጥ ማርሽ በተባለ ሱፐርማርኬት 16 ብር ዋጋ ያለውን ማስቲካ በመሳሪያው አማካኝነት አውቶማቲክ በሆነ መንገድ ሲመዘገብ ነበር።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የባርኮድ ቴክኖሎጂ ለትናንሽ ቸርቻሪዎች ውድ ነበር

የቴክኖሎጂ ለውጥ

ማስቲካውም ተሽጦ የባርኮድን መጀመር አበሰረ።

ባርኮድ ሲታሰብ ትልልቅ መደብሮች የግብይት ስርዓትን በቀላል ፈጣንና በተደራጀ መልኩ መፈፀም እንዲያስችላቸው ነበር። ነገር ግን ቴክኖሎጂው ከዚያ በላይ በኢንዱስትሪዎችና መደብሮች ላይ ስር-ነቀል ለውጥ ማምጣት ቻለ።

ጉዳዩ ግን አልጋ ባልጋ አልነበረም። አምራቾች ምርቶቻቸው ላይ ባርኮድ እስኪለጥፉ ድረስ የመደብር ባለቤቶች የማንበቢያ መሳሪያውን ሊገዙ አልፈቀዱም።

በተመሳሳይ ደግሞ አምራቾች የመደብር ባለቤቶች በቂ የማንበቢያ መሳሪያ እስኪገዙ ምርታቸው ላይ ባርኮድ መለጠፍ አልፈለጉም።

የባርኮድ መኖር በመደብር ባለቤቶች መካከል ከፍተኛ ልዩነትን መፍጠር ጀመረ።

የሸማቾች ሰልፍ እየቀነሰ በፍጥነትም መስተናገድ ከመጀመራቸውም በተጨማሪ የምርቶቻቸውንም ዝርዝር መመዝገብ አስችሏቸዋል።

በተቃራኒው ለትንንሽ መደብሮች ባለቤቶች ሸማቾች ጥቂት በመሆናቸው የማንበቢያ መሣሪያ አላስፈላጊ ወጭ ሆኖ ነው የታያቸው።

በእጅ በሚሰራበት ወቅት ክፍያዎች ሳይመዘገቡ ያለምንም ቁጥጥር ሊጠፉ የሚችሉበት ሁኔታንም ማስወገድ ችሏል።

በተለይም በ1970ዎቹ በነበረው የዋጋ ግሽበት ላይ ባርኮድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

ከጊዜ በኋላ ባርኮድ ያላቸው ቸርቻሪዎች ይበልጥ ተመራጭነት እያገኙ መጡ። ለጥቃቅን ሱቆች ግን መሣሪያውን ማስገባት ለሌሉባቸው ችግሮች አላስፈላጊ ወጪ ውስጥ መግባት ሆኖ ታያቸው።

ለትልልቅ ሱፐርማርኬቶች ግን የመሣሪያውን ዋጋ በሚሸጡት የዕቃዎች ብዛት ሊበትኑት ይችሉ ነበር። በተጨማሪም ገንዘብ ያዦቹ ጋር ያለውን ሰልፍ መቀነስ ስለሚፈልጉና የዕቃዎቻቸዉን ዝርዝር መቆጣጠር ስለሚያስችላቸው መሣሪያው ጠቃሚ ሆነላቸው።

አልፎም ቴክኖሎጂው በመደብር ሠራተኞች የሚፈጸሙ ስርቆቶችን ከበድ አደረገ።

ከዚያም በ1970ዎቹ በነበረው የዋጋ ግሽበት ሱፐርማርኬቶች እያንዳንዱ ዕቃ ላይ ያለዉን ዋጋ ሳይሆን በመደርደሪያው ላይ ያለዉን ብቻ ነበር መቀየር የነበረባቸው።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የዎል ማርት መሥራች ሳም ዋልትሰን

የብዛት ጥቅም

በሚያስደንቅ ሁኔታ እ.አ.አ በ70ዎቹና በ80ዎቹ በመስፋፋት የትልልቅ መደብሮችን በከፍተኛ ቁጥር መጨመር ባርኮድ ትልቅ አስተዋጽኦ አበረከተ።

የማንበቢያ መሳሪያዎቹም የሸማቾቹን መረጃ እንዲሁም የደንበኝነት ካርድ ለማግኘት አስችሏል።

ሻጮች የዕቃዎቻቸውን ዝርዝሮችም በቀላሉ ለመከታተልና ለመመዝገብ ስለቻሉ የተለያዩ ምርቶችንም በቀላሉ ወደተለያዩ ቦታዎች በአካል ማድረስም አስችሏቸዋል።

ባርኮድ የተወሳሰቡና ከበድ ያሉ ዕቃዎችን ግብይይት ቀለል አድርጓል።

በተለይም እንደ ዎልማርት ለመሳሰሉ ኮርፖሬሽኖች በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ትልልቅ መደብሮችን መክፈት ያስቻላቸው ባርኮድን ማስተዋወቃቸው ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች