የሰሜን ኮርያ የኒዩክሌር ሚሳየል ሙከራ ደቡብ ኮርያንም ልምምድ እንድታካሂድ አስገድዷል

የደቡብ ኮርያወታደራዊ የሚሳይል የሙከራ ፎቶግራፎች Image copyright AFP/Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሰኞ ዕለት ደቡብ ኮርያ በምዕራብ ዳርቻዎቿ ያካሄደችውን ወታደራዊ የሚሳይል የሙከራ ፎቶግራፎች ለቀቀች

ለፕዮንግያንግ ስድስትኛ ሙከራ ምላሽ ደቡብ ኮርያ የሰሜን ኮርያን የኒዩክሌርን ሊመታ የሚችል የሚሳያል ሙከራ አከናወነች።

ይህ ቀጥተኛ የጦር ልምምድ ከጦር ጄቶችና ከመሬት የሚወረወሩ የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን የምወርወር ሙከራ ያካተተ ነበር። ይህም የተከናወነው የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የጦር ሃላፊ የሆኑት ጄምስ ማቲስ ከፒዮንግያንግ የሚመጣ ማናኛውም አይነት ማስፈራሪያ በአሜሪካና ወዳጆቿ ከባድ ወታደራዊ ምልሽ እንዲጠብቁ ከማስጠንቀቃቸው ነበር።

ሰሜን ኮሪያም የረጅም ርቀት ሚሳይል ሚያክል ሃይድሮጂን ቦምብ ሙከራ እንዳካሄደች አሳውቃለች።

ፒዮንግያንግ የተለያዩ የኒዩክሌር መሣሪዎችን በመሥራትና ሚሳይሎችን በመሞከር በተደጋጋሚ ለተባበሩት መንግሥታት ማዕቀቦችና ለዓለም አቀፍ ጫናዎች የእምቢተኛነት መንፈስ አሳይታለች።

ባለፉት ሁለት ወራትም ጃፓንን አቋርጦ ወደ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የተላከ አህጉር አቋራጭ የሆነ የረጅም ርቀት ሚሳይል ሙከራ ከብዙዎቹ አንዱ ነበር። የአሜሪካ ግዛት ወደሆነችዉ ግዋን ወደተሰኘችው ደሴት ሚሳይል እንልካለን በማለት አስፈራርተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ምክር ቤት ስለሚኖረው ምላሽ ለመነጋገር በዛሬው ዕለተሰኞ የሚካሄድ የአሳቸኳይ ሁኔት ስብሰባ ጠርተው ነበር። ባለፈው ዕለተአርብም የተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ምክር ቤቱ የጠራዉን ስበስባ ሊቀመንመበር የሚትሆነው ሃገር ኢትዮጵያ መሆንዋን ገልጸዋል።

ከተጠራው ስብሰባ አስቀድመው የደቡብ ኮርያና ጃፓን መሪዎች በስልክ ባካሄዱት ንግግር ላይ ሰሜን ኮርያ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ከፍተኛ እነዲሂሆን ተስማምተዋል እንዚህም ከተባበሩት መንግሥታት ከባድ መፍትሔዎችን እንጠብቃለን በማለት የደቡብ ኮርያ የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

የሙከራዎቹ ትርጉም ምን ይሆን?

በሴዑል ያለው የቢቢሲው ሮብን ብራንት ሙከራው የአገሪቱን መረጋጋት ከፍተኛ መጠንቀቅ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ብሏል። አገሪቷ የኒዩክሌር አቅም ስለሌላት መደበኛ መሣሪያዎችን ነው የሞከረችው።

ነገር ግን የደቡብ ኮርያ ወታደራዊ ኃይል የማስመሰያው ሙከራ የተካሄደው ሰሜን ኮርያ ሙከራዎቹን ያካሄደበትን የፑንግዬሪ ጣቢያ በግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነበር በማለት ሰኞ ዕለት አሳውቀዋል።

"ሙከራው የየደቡብ ኮርያን ወታደራዊ ኃይል የማስፈራሪያውን መነሻ ብቻ ሳይሆን የጠላትን አመራር እና አጋዥ ኃይሎቹን ለማጥፋት ያለውን ቆራጥ ውሳኔ የሚያመላክት ነው" በማለት የወታደራዊው ኃይል ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሮህ ጄይችዎን በደቡብ ኮርያ ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ላይ ተጠቅሰዋል። ዮንሃፕም ደቡብ ኮርያና ዩናይትድ ስቴትስ ያሉትን መመሪያዎች ቀይረው ደቡብ ኮርያ ያላትን የረጅም ርቀት ሚሳይል ገደብ ለመጨመር በመርህ እንደተስማሙም ዘግቧል።

Image copyright AFP/GETTY IMAGES
አጭር የምስል መግለጫ ሴዑል ሂዩንሙ የተሰኙትን ሚሳይሎች ከቦታ ቦታ ሞክረዋል

ሙከራዉ እነዴት ተካሂዶ ይሆን?

እሁድ ዕለት ሴይዝሞሎጂስቶች ማለትም የምድርን እንቅስቃሴ የሚለኩ ባለሞያዎች ከዚህ ቀደም ሰሜን ኮርያ የኒዩክሌር ሙከራዎችን አካሂዳበት በነበረበት አካባቢ የምደር መንቀጥቀቶችን አነበቡ።

የአሜሪካው ጂዮሎጂ ጠናትም የዚህ መንቀጥቀጥ ኃይሉን ልኬት መጠኑን በ6.3 አስቀምጦታል።

የሰሜን ኮርያም የመንግሥት ሚድያ የመሬት መንቀጥቀጥ አለመሆኑን አረጋገጡ በመቀጠልም ስድስተኛውና በጣም ኃለኛው የኒዩክሌር ሙከራቸው በረጅም ሚሳይል ላይ የሚጫን የሃይድሮጅን ፈንጂ የሚያፈነዳ መሆኑን አሳዉቀዋል።

በመቀጠል ፒዮንገያንግ የመሪያቸውን የኪም ጆንግኡንን ምስሎች ከሃይድሮጅን ፈንጂ አጠገብ ቆሞ ያሉትን በመንግሥት ሚዲያዎች አስተላለፉ።

Image copyright Reuters/KCNA
አጭር የምስል መግለጫ ኪም ጆንግኡን የሃይድሮጅን ፈንጂ ከተባለው አጠገብ ቆሞ

ባለሞያዎች ትንቃቄ ቢያበረታቱም የእሁዱ ክንውን ግን ለሰሜን ኮርያ እስከዛሬ ትልቁና በይበልጥ የተሳካላቸው የኒዩክሌር ሙከራ በመሆኑ መልክቱም ግልጽ ነው።

ምላሹስ ምንድን ነበር?

የኒዩክሌሩ ሙከራ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የንዴት ምላሽ አስከትሏል እሱም ሙከራውን ጠበኘነትና አደገና በማለት ተቃውመውታል በመወጠልም ሰሜን ኮርያን ሕግ ተላላፊ ሃገር በማለት ሴይሟታል።

በመጨመርም አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ ጋር ግንኙነት ላሏቸው ሃገራት በሙሉ የንግድ ልውውጦችን እንደምትቋጭ አሳውቋል ደግሞም ሰሜን ኮርያም ከቻይና ጋር ባላት የንግድ ግንኙነት 90% ጥገኛ ናት።

አቶ ማቲስም ከዚያ ቀጥሎ ለጋዜጠኞች እነደተናገሩት አሜሪካ ለማንኛዉም ማስፈራሪያ በከባድ ውጤታማና አስደናቂ ወታደራዊ ምላሽ መስጠት እንደምትችል ተናግረው የትኛውንም ሃገር በተሌይም ሰሜን ኮርያን የማጥፋት ፍላጎት እነደሌላቸው አሳውቀዋል።

የዋይት ሃውስ መግለጫ ዋሺንግተን ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ መደበኛና የኒዩክሌር ችሎታዎች በመጠቀም ሃገሪቱንም ሆነ ወዳጆቹን እንደሚከላከል ተናግሯል።

የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄይኢን ሙከራውን የማይረባ የስልት ስህተት በማለት በተቻለ መጠን ኃይለኛ ለሆነ ምላሽ በተለይም ከተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ምክር ቤት አዳዲስ ማዕቀባት እነዲጣልባትና ሃገሪቷን ሙሉ በሙሉ ለማግለል አበረታትቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቻይና ከባድ ተቃውሞዋን በመግለጽ ሃገሪቷ ዓለም አቀፋዊ ሆነውን ተግጻስ እንደናቀች ተናግረዋል።

የሃይድሮጅን ፈንጂዎች ከአቶሚክ ፈንጂዎች የበልጠ ኃይል አላቸው። አቶሞችን በማዋሃድ የማቀላቀልን ምፍትሔ በመጠቀም ሰፊ የኃይል ስብስብን በመልቀቅ የሚፈነዳ ሲሆን አቶሚክ ፈንጆዎች ግን የኒኡክሌር መፋጨትን በመጠቀም አቶሞችን የሚሰነጥቅ ምፍትሔ ነው።

አናሊስቶች የሰሜን የይገባኛል ትያቄዎች በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው መሆኑንና የኒየዑክሌር አቅሟ እያደገ መምተቀቱን ገልጸዋል።

ሙከራው ምን ይነግረናል?

የደቡብ ኮርያ ባለሥልጣኖች የቅርብ ጊዜው ሙከራ በፑንግዬሪ ኒዩክሌር ሙከራ ጣቢያ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የመንግሥት የአየር ሁኔት ድርጅት እንደገለጸው የዚህ የሰው ሠራሽ መንቀጥቀጥ ሰሜን ኮርያ ባለፈው ዓመት ካካሄደችው አምስተኛው ሙከራ መንቀጥቀጥ በ9.8 ይበልጥ ነበር ብለዋል።