የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔና የሃገሪቱን የፍትሕ ሥርዓት ችግር አለበት ብለው ተናገሩ።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስከትሎ ራይላ ኦዲንጋ ደስታቸውን ገለጹ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስከትሎ ራይላ ኦዲንጋ ደስታቸውን ገለጹ

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባለፈው ወር የተካሄደውን የፕሬዚዳንት ምርጫ ካፈረሰ በኃላ የሃገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት ችግር አለበት ብለው ተናገሩ።

በቴሌቪዥን የተላለፈውን የቀጥታ ሥርጭት ላይ ተመልሶ የሚመረጥ ከሆነ የሃገሪቱን የፍርድ ቤት አሠራር እንደሚያስተካክል ቃል ገባ።

ይህ ውሳኔ ይፋ የተደገረገው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተደረው የምርጫ ሥነ-ሥርዓት ላይ ያዩአቸውን ልዩነቶች በመግለጽ ነበር በተጨማሪም ከ60 ቀናት በኃላ ሌላ ምርጫ እንዲካሄድ አዘዙ።

ፕሬዚዳንት ኬንያታ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚያከብር ከተናገረ በኃላ በፍራቻና በውጥረት ወቅትም መረጋጋት እነዲኖር ጥሪ አቅርቧል።

ሆኖም ግን ባለፈው አርብ ዕለት በተደረገው አድማ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ዳኛዎች አጭበርባሪዎች በማለት ሰይሟቸዋል።

ባለፈው 2 ነሐሴ 2009 የተደረገው የምርጫ ሥርዓት በብዙዎች ዘንድ እነደ ታሕሳስ 2000 ምርጫው ይታወካል የሚል ስጋትና ፍራቻ ፈጥሮ ነበር።

ዊልያም ሩቶ ምክትል ፕሬዚዳንት የምርጫውን ኮሚሽን ቀን እነዲወስን በመግፋት ገዢው የጁቢሌ ፓረቲ ዝግጁ እነደሆነ አሳውቋል።

የተቃዋሚው ፓርቲ ተወዳዳሪ ራይላ ኦዲንጋ ደግሞ ኮሚሽኑ እምነት እሚጣልበት ባለመሆኑ ከናካቴው እንዲቀየር ጥያቅ አቅርበዋል።

"ይህን ጉዳይ መልሰን መመልከት ይኖርብናል ምክንያቱም የማይካድ ችግር ነው ያለው" በማለት የፍትሕ ሚኒስቴሩን ቅዳሜ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።

"ማን ሾማችሁ? ተሹማእኃልስ? ችግር ስላለ መጠገን አለበት" በማለትም ቀጥለው ተናግሯል።

በዚህ ዓመት የነበረው የምርጫ ውጤት ውጥረት እንደ 2000 ዓ.ም ባይሆንም ቢያንስ 28 ሰዎች ሞተዋል።

የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን አቶ ኬንያታን የምርጫው በ1.4 ሚልዮን ድምጽ ብልጫ አሸናፊ መሆናቸውን ባሳወቀ ከጥቂት ጊዜ በኃላ ነበር ተቃዋሚው ኦጊንጋ ወደ አቅራቢያ ፍርድ ቤት ክሳቸውን ያቀረቡት።

ባለፈው እርብ ዕለት በተደረገው ውሳኔ የፍትሕ ኃላፊ የሆኑት ዴቪድ ማራጋ የዚህ ዓመት ምርጫ ሥርዓት ሕገ-መንግሥቱን ያልተከተለ ሂደት በመሆኑ ትክክል ያልሆነና የሚሻር ምርጫ ነው በማለት ተናግረዋል።

ውሳኔው የፕሬዚዳንቱን ፓርቲ ወይንም ዘመቻ በምንም አይነት ወቀሳ አላቀረቡበትም።

የ72 ዓመቱ አቶ ኦዲንጋ ይህን ውሳኔ "ለኬንያውያን በሙሉና ለመላው አፋሪካ የሚበቃ ታሪካዊ ክንውን ነው በማለት ተናግረዋል"።

ይህንም ምርጫ አስከትሎ ከአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪካ ሕብረትና ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተውጣጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምንም አይነት ማጭበርበር እነዳልነበረና አቶ ኦዲንጋም በዕሺታ ውሳኔውን እንዲቀበሉ አበረታተውታል።