የእንግሊዝና የካናዳ መንግስታት አዲስ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ

አጭር የምስል መግለጫ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ድንበር አቅራቢያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ተላልፎዋል

የካናዳ መንግስት ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ላይ በሁለቱ ክልሎች ድንበር አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የጠለፍ ስጋት መኖሩንና ኢትዮጵያ በኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ላይ በምታካሂደው ወታደራዊ እረምጃ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ሰለባ ስለመሆናቸው ጠቅሶ የካናዳ ዜጎች በሁለቱ ክልሎች ድንበር አከባቢ ምንም አይነት ጉዞ እንዳያደርጉ አስጠንቅቋል።

የእንግሊዝ መንግስትም በሃረርና ባቢሌ አከባቢዎች ያለውን የጸጥታ ችግር በመጥቀስ በአከባቢው የሚገኙ ዜጎቻቸው ከፈተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክረዋል።

የካናዳ፣ የአሜሪካና የእንግሊዝ መንግስታት በኢትዮጲያና ኤርትራ ድንበር አቅራቢያ፣ በሰሜን ጎንደር፣ በየኢትዮጲያ ሱማሌ ክልል ውስጥ እንዲሁም በሱዳንና በደቡብ ሱዳን ድንበር አከባቢ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ዜጎቻቸው ከፈተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመክራሉ።

በሌላ በኩል የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚውንኬሽን ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እነዳሰፈሩት በኢትዮጵያ ሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል የተከሰተውን የድንበር አለመግባባት ለመፍታት በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ህዝባዊ ውሳኔ መሰረት የድንበር ማካለሉን ስራ ለመስራት በሁለቱ ክልሎች መካከል በሚያዝያ 2009 ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውሰው በቅርቡ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን 10 ሰላማዊ ሰዎች ከሱማሌ ክልል በመጡ ታጣቂዎች መገደላቸውንና በ12 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሃገራት የሚያወጡት የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዜጎቻቸው የሚያደርጉት ጉዞ በጥንቃቄ የተሞላ እነዲሆን ይረዳቸዋል።

ለመሆኑ የውጭ ጉዞ ማስጠንቀቅያ መቼና ለምን ይታወጃል?

በርካታ ኣገሮች የውጭ ጉዞ ማስጠንቀቂያ ያወጣሉ። ዜጎቻቸው ወደነዚህ አገሮች የሚያደርጉት ጉዞ በጥንቃቄ እንዲወስኑ ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ እንዳስቀመጠው በአንድ አገር ላይ ጉዞ ማስጠንቀቂያ የሚሰጠው በአከባቢው የልታሰበና ድንገተኛ የደህንነት ስጋት ሊከሰት መሆኑን ሲረዳ መሆኑን በድህረ-ገፁ አስፍሯል።

ለምሳሌ በምርጫ ወቅት የሚደረግ ሁከትና ብጥብጥ፣ ህዝባዊ እምቢተኘነት እንዲሁም ተፍጥሯዊ የሆኑ አደጋዎች እንደ የመሬት መንቀጥቀጥ ዓይነት አደጋ ሲከሰቱ የጉዛ ማስጠነወቀቂያዎች ይወጣሉ።

በተመሳሳይ የካናዳ መንግስት በደህንነትና ኢሚግሩሽን ድህረ-ገፁ እንዳሰፈረው፤ በአንድ አከባቢ የጉዞ ማስጠንቀቂያ የሚያወጣው የዜጎቹን ደህንነት የሚያሰጋ የደህንት ሁኔታ በማጥናት መሆኑን የገልፃል። በአንድ ኣከባቢ የጉዞ ማስጠንቀቂያ የሚያወጣው ከተለያዩ ኣካላት በቂ መረጃ ከሰበሰበና በባለሞያዎች ከካስተነተነ በሗላ መሆኑን የገልፃል።