በድጋሚ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ኡሁሩና ራይላ ብቻ ይሳተፋሉ

ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ራይላ ኦዲንጋን የሚያሳይ ምስል Image copyright AFP/Getty
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ (በስተግራ) ነሓሴ 8 ተካሂዶ በነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቢያሸንፉም ኦዲንጋ ባሰሙት አቤቱታ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የምርጫውን ውጤት 'ህገምንግስታዊ ያልሆነ' ብሎ ሸሮታል

ነሓሴ 8 ተካሂዶ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ያሸነፉበት የምርጫ ውጤት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከሰረዘው በህኃላ ቀጣይ ምርጫ ጥቅምት 17 እንዲካሄድ ቀን መቆረጡን የኬንያ ገለልተኛ የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አሰታውቆዋል።

የገለልተኛው የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አዲስ መሪ ሆነው የተመረጡት ዋፉሉ ቼቡካቲ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ላይ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ ብቻ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል።

ነሓሴ 8 ተካሂዶ በነበረው ምርጫ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው ይታወሳል ይሁን እንጂ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋን ኤቤቱታ ሰምቶ ከመረመረ በኃዋላ የምረጫውን ውጤት 'ህገ-ምንግስታዊ አይደለም' በማለት ሽሮታል።

ይህ አይነት ውሳኔ በአፍሪቃ ታሪክ የመጀመሪያው ነው።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ውሳኔውን ሲያስተላልፉ የተወሰኑ የገለልተኛው የምርጫና የድንበር ኮሚሽን አባላት ''አግባብነት የሌለው እና የተዛባ ነገር'' ፈጽመዋል ብለዋል።