የሰሜን ኮርያ የኒዩክሌር ችግር፡ የኪም ጆንግ ኡን የጦርነት ልመና ጥሪ።

ኪም ጆንግኡን Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ኪም ጆንግኡን የሃይድሮጅን ፈንጂ ከተባለው አጠገብ ቆሞ

የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በቅርቡ የካሄዱት የኒዩክሌር ሙከራ የጦርነት ልመና ጥሪ እያደረጉ እንደሆነ ያሳያል ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ ልዑክ ኒኪ ሄሊያ ተናግረዋል።

ኒኪ ሄሊይ በትላንትናው ዕለት በኒይው ዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ምክር ቤት ድንገተኛ ስብሰባ ላይ አሜሪካ የጦርነት ፍላጎት ባይኖራትም የማያመነምን ትዕግስት ግን እንደሌላት ተናግረዋል።

ይህን ይህን የተባበሩት ምንግስታት አስቸኳይ ስብሰባ ኢትዮጵያ ትመራዋለች

በጥቂት ጊዜ ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኮሪያ ላይ ማዕቀቦችን ለማጠናከር ለተባበሩት መንግሥታት አዲስ አማራጮችን ታቀርባለች።

የሰሜን ኮርያ ዋና ወዳጅ የሆነችው ቻይና ለሌላ ድርድ እነዲቀመጡ ስትጠይቅ ስዊዘርላንድ ደግሞ ድርድሩን ለመምራት ፈቃደኛ መሆንዋን ግልጻለች።

በሌላ በኩል የደቡብ ኮርያ ባህር ኃይል በባህር ላይ የጦር ልምምድ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ዮንሃፕ የሚድያ ኤጀንሲ እነደዘገበው የደቡብ ኮርያ ባህር ሃይል ሰሜን ኮርያ ነገር የምትፈልጋቸው ከሆነ "ያለ ምንም ማመንታት ምላሽ በመስጠት በባህር ላይ እንቀብራቸዋለን" ሲሉ ዝተዋል።

አሁን እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ሰሜን ኮርያ አዲስ የሚሳይል ሙከራዎች ልታካሂድ እየተዘጋጀች እነደሆነ ያሳያሉ።

ባለፈው እሁድም የመሬት ውስጥ የፈንጂ ሙከራ አካሂዳ ነበር። ይህም ፈንጂ ከ 50 ኪሎቶን እስከ 120 ኪሎቶን የሚያክል ኃይል ነበረው።

የውይይት ሰዓት

ኒኪ ሄሊይ በሰሜን ኮርያ ላይ ከባድ ቅጣቶችን በመጣል ብቻ ችግሩን በዲፕሎማሲያቂ መፍታት እነደሚቻል ገልጸዋል።

በመቀጠልም "ምንግዜም ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነትን አትመርጥም" ብለዋል "አሁን ባንፈልገውም የሃገራችን ትዕግስት ግን እያመነመነ ነው" በማለት አቋማቸውን ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የቻይና ልዑክ የሆኑት ሊዩ ጂዬዪ በድጋሚ ሁሉም ወገኖች በጠረጴዛ ዙሪያ እነዲነጋገሩ አጥብቀው ጠይቀዋል።

ሊዩ ጂዬዩም "ይህ እሰጣ-ጋባ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ሊፈታ ይገባዋል" በለዋል። በመቀጠልም " ቻይና መቼም ቢሆን እዚች ብጥብጥና ጦርነት እንዲኖር አትፈቅድም" በማለት ተናግረዋል።

የሰወዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ዶሪስ ለታር ከቤርንዝ ከተማ ሆነው የሃገራቸውን በታሪክ የተመዘገበውን ገለልተኝነቷንና የምታካሂደውን ጥንቁቅ ዲፕሎማሲ አስታውሰዋል።

እሳቸውም "ለውይይት ሰዓቱ የደረሰ ይመስለኛል" በማለት ተናግረዋል። "ያለንን የሸምግልና ጥሩ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፈዋደኛም ነን። በፊታችን የሚመጡት ቀናትም ሁኔታ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስና በቻይና አቋም ላይ እጅጉን የሚወሰን ይሆናል" በማለት ተናግረዋል።