አዕምሮዎን ያዳብሩ - እንቆቅልሽ 13

የዛሬውን እንቆቅልሽ እንዲፈቱ እነሆ አቅርበናል።

እንኳን ደህና መጡ!

የመዝናኛ ዝግጅት Image copyright Getty Images

መልመጃ 13

በቅርቡ በተዘጋጀ አንድ ድግስ ላይ ላይ ከተገኙት 100 ሰዎች መካከል፤ 90ዎቹ ኦሮምኛ ይናገራሉ፣ 80ዎቹ አማርኛ ይናገራሉ፣ 75ቱ ደግሞ ትግርኛ ይናገራሉ።

ከእነዚህ ሠዎች መካከል ቢያንስ ምን ያህሎቹ ሶስቱንም ቋንቋዎች ይናገራሉ?

መልሱን ለማግኘት ይህንን ይጫኑ

መል

45 ሠዎች ናቸው።

10 ሰዎች ኦሮምኛ አይችሉም። 20ዎቹ ደግሞ አማርኛ አይችሉም። 25ቱ ደግሞ ትግርኛ አይችሉም። ስለዚህ ሁለት ቋንቋ ብቻ ሊናገሩ የሚችሉ ሰዎች ቁትር ቢበዛ 25 ነው።

ስለሆነም ይህ ሶስቱንም ቋንቋ የሚናገሩ ሠዎችን ቁጥር ከፍ ያደርጋል፤ እንቆቅልሹ ደግሞ ቢያንስ ምን ያህል ሠዎች ሶስቱንም ቋንቋዎች ይናገራሉ የሚል ነው።

ስለዚህ ከላይ የተገለጹት 10፣ 20 እና 25 ሠዎች የተለያዩ ናቸው እንበል።

ከሦስት ቋንቋዎች በታች የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር 55 ነው ካልን፤ ሦስት ቋንቋዎችን ሚናገሩት ደግሞ 45 ይሆናል ማለት ነው።