ብርሃን በየዘመኑ ያስከፈለው ዋጋ

Image copyright Thinkstock

በ1990ዎቹ አጋማሽ ዊሊያም ኖርዶስ በብርሃን ዙሪያ ቀለል ያሉ ተከታታይ ሙከራዎችን ያደርግ ነበር።

መጀመሪያ በቀድሞ ታሪኮች የተመዘገቡትን ቴክኖሎጂዎች ነበር የተጠቀመው - በእንጨት እሳት ማቀጣጠል።

ሆኖም ፕሮፌሰር ኖርዶስ የብርሃን መጠንን የሚለኩ ዘመናዊ መሳሪያዎችም ነበሩት።

9 ኪሎግራም የሚመዝን እንጨት አንድዶ ለምን ያህል ጊዜ እንደነደደ ፣እንደጠፋና እሳቱ የፈጠረውን ብርሃን በጥንቃቄ መዘገበ ።

በመቀጠልም የጥንቱን ከጥፍጣፋ ድንጋይ የሚሰራውን የሮማውያንን ኩራዝ አምጥቶ የጋዝ ክር ካሰረበት በኋላ በቀደዳው ውስጥ ደግሞ የሰሊዝ ዘይት ያደርግበታል።

ኩራዙን ለኩሶ ዘይቱ ነዶ እስኪያልቅ የሰጠውን ብርሃንናን የክሩን ፍም መጠን መዘገበ።

Image copyright iStock
አጭር የምስል መግለጫ ኖሮዶስ የሮማውያን ኩራዝ ከክምር እንጨት የተሻለ ብርሃን መስጠቱን ተረዳ

ኖሮዶስ ያቀጣጠለው 9 ኪሎግራም እንጨት የነደደው ለሶስት ሰዓታት ብቻ ነበር።

በትንሽ ጠርሙስ ላይ የነደደው ኩራዝ ግን ለሙሉ ቀን ሲነድ የተሻለ ብርሃን ስጥቷል።

ይህንን ሁሉ ነገር ማድረግ የፈለገው ደግሞ በተለያዩ ዓመታት ብርሃኑን ለማግኘት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎች የሚጠይቁትን ወጪ በማስላት ምጣኔ ሃብታዊ ጥቅማቸውን መለየት ነው።

ብዙ ወጪ የሚያስወጡ ዘዴዎች

ብርሃን የሚለካው በሰዎች ዓይን ላይ በሚፈጥረው ድመቀት ነው (ሉመንስ).

ለምሳሌ ሻማ ሲለኮስ 13 "ሉመንስ" ብርሃን ይሰጣል።

የተለመዱት ዘመናዊ አምፖሎች ደግሞ ከዚህ 100 እጥፍ የሚሆን ድምቀት ይሰጣሉ።

እስኪ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በቀን ለ10 ሰዓታት እንጨት ስትለቅሙና ስትፈልጡ መዋልን አስቡት።

በዛ ላይ ከ60 ሰዓታት ልፋት በኋላም ሊገኝ የሚችለው 1000 ሉመን ብርሃን ነው።

ዘመናዊ አምፖሎች ግን ይህንን ብርሃን በ54 ደቂቃዎች ውስጥ መስጠት ይችላሉ።

በርግጥ እንጨት የሚነደው ለብርሃን ብቻ አይደለም፡ ለሙቀትም ፣ምግብ ለማብሰልም ፣የዱር አራዊትን ለማስፈራራትም ሊሆን ይችላል።

ነገር ግን ብርሃን ቢያስፈልግና እንጨትማንደድ ብቸኛ አማራጭዎ ቢሆን ፀኃይ እስክትወጣ ለመጠበቅ ይወስኑ ይሆናል።

ከሺህ ዓመታት በፊት ግን ግብፅና ግሪክ ሻማን ፣ ባቢሎን ደግሞ ኩራዝን ለዓለም አስተዋወቁ።

የሚሰጡት ብርሃንም ዘላቂና ለመቆጣጠርም የሚመች ቢሆንም በጊዜው ዋጋቸው ውድ ነበር።

በአውሮፓውያን 1743 የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኤድዋርድ ሆሊያክ ባሰፈሩት በማስታወሻቸው እንዳሰፈሩት ቤተሰበቸው ከቀለጠ ስብ 35 ኪሎግራም የሚመዝን ሻማ ለመስራት ሁለት ቀናት ፈጅቶበታል።

ከስድስት የበጋ ወራት በኋላ ደግሞ " ሻማዎቹ በሙሉ አልቀዋል" ብለው ጻፉ።

ታዲያ እነዚህ ሻማዎች እንደአሁኖቹ ከሰም በጥራት የሚዘጋጁ አልነበሩም።

ባለጸጋዎቹ ከማር እንጀራ የሚሰራውን ሲያበሩ ብዙኃኑ ግን መጥፎ ጠረንና ጭስ ያላቸውን የስብ ሻማዎች ነበር የሚጠቀሙት።

ይህ ደግሞ በቀለጠው ስብ ውስጥ የፈትል ክርን ልክ እንደጧፍ መልሶ መላልሶ መክተትን ይጠይቃል ፤ ስራው በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ነበር።

Image copyright WORLD HISTORY ARCHIVE / ALAMY STOCK PHOTO
አጭር የምስል መግለጫ የስብ ሻማ ስራው በጣም አድካሚና ጊዜ የሚወስድ ነበር።

በፕሮፌሰር ናርዶስ ጥናት መሰረት በአንድ ዓመት ውስጥ ለአንድ ሳምንት ወይም ለ 60 ሰዓታት ለሻማ መስሪያ ወይም እነሱን ለመግዛት ለሚያስችል ስራ ቢውል ማግኘት የሚቻለው ለሁለት ሰዓታትና 20 ደቂቃዎች ብቻ የሚበራ ሻማ ነው።

በ18ኛውና በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ግን ሁኔታዎች ይበልጥ መሻሻል ጀመሩ።

ከሞቱ አሳነባሪዎች ከሚገኝ ዘይት መሰል የሚያጣብቅ ወፈር ያለ ፈሳሽም ሻማ መሰራት ተጀመረ።

ሻማው በሚሰጠው ጠንካራ ብርሃን ፣ በእጅ ለመያዝ ምቹ በመሆኑንና በሞቃት አየርም እንደጠነከረ በመቆየቱን ተወዳጅ ሆነ።

ታላቁ እመርታ

አዳዲሶቹ ሻማዎች አስደሳች ቢሆኑም ዋጋቸው ግን ለብዙኃን የማይቀመስ ነው።

ጆርጅ ዋሽንግተን ይህንን ሻማ በአመት በየቀኑ ለአምስት ሰዓታት ለማብራት 9 ዶላር እንደሚያስወጣው ተናግሯል ። ይህ ገንዘብ አሁን 1000 ዶላር ያወጣል ።

ከጥቂት አስርት ዓመታት በኋላ ደግሞ የነጭ ጋዝና በሌሎች ጋዞች የሚሰሩ ፋኖሶች በአንጻራዊ አነስተኛ ዋጋ መቅረብ ጀመሩ።

ነገር ግን እነሱም ቢሆኑ አዘገጃጀታቸው አድካሚ ነበር።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን ሁሉንም የሚለውጥ አዲሱ የአምፖል ግኝት መጣ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የኤዲሰን የአምፖል ግኝት ከሰው ሰራሽ ብርሃን ፈጠራዎች ሁሉ ታላቁ ተደርጎ ይወሰዳል

በ1900 የቶማስ ኤዲሰን አምፖሎች ከሻማ 100 እጥፍ የሚሆን ብርሃን ያለማቋረጥ ለ 10 ቀናት ይሰጡ ነበር።

በ1920 አምፖሎቹ ዋጋቸውም እየረከሰ አቅማቸውም እያደገ ለአምስት ተከታታይ ወራት ብርሃን መስጠት ጀመሩ።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደግሞ የፍሎረሰንት አምፖሎች ተፈጠሩና ቀድሞ ለ54 ደቂቃዎች ብርሃን የመስጠት አቅም የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አሁን ለ52 ዓመታት ማቆየት ቻለ።

የፈጠራ ተምሳሌቶች

ዘመናዊዎቹ የኤልኢዲ መብራቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየቀነሰ መጣ።

በእርግጥም ከፋኖሶችና ሻማዎች በተለየ እነዚህ መብራቶች ንጹህ፣ ለአደጋ የማያጋልጡና ለቁጥጥርም የሚመቹ ናቸው።

እናም ግኝቱ የፈጠራዎች ተመሳሌት ተደርጎ መወሰድ ጀመረ።

ዓለማቀፉ ማሀበረስብም የመሥራት ፣ የማነበብና የመጫወት ፍላጎቱ በፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት መገደቡ ቀረ።