የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ ኮሚሽኑን ወቀሰ

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኡሁሩ ኬንያታ በድጋሚ ለተመረጡበት ምርጫ ውጤት መሰረዝ የሃገሪቱን ምርጫ ኮሚሽን ተጠያቂ አድርጓል።

ዳኞቹ ነሃሴ 8, 2017 የተካሄደው ምርጫ ''ግልጽ አልነበረም፤ ማረጋገጥም አይቻልም'' ብለዋል።

የፍርድ ቤቱ ምክትል ዳኛ ፊሎሜና መዊሉ ኮሚሽኑ ይፋ ከማድረጉ በፊት ውጤቱን አላረጋገጠም ነው ያሉት።

የኤሌክትሮኒክ የምርጫ ስርዓቱን እንዲያስመረመር የተሰጠውን ትእዛዝም ለመፈጸም አልፈቀደም።

ይህ ደግሞ ''የኤሌክትሮኒክ ስርዓቱ ተጠልፎ ሊሆን ይችላል'' የሚለውን የኦዲንጋን ይግባኝ ዳኞች እንዲያምኑበት አድርጓል።

በምርጫው ኬንያታ 54 በመቶ ተቃዋሚያቸው ኦዲንጋ ደግሞ 44 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸው ይፋ ተደርጎ ነበር።