ማሪያ አውሎ-ንፋስ የፖርቶ ሪኮን የኤሌትሪክ ሃይል ሙሉ በሙሉ አቋርጧል

የፖርቶ ሪኮ ጎዳና Image copyright AFP

ማሪያ የተባለው አውሎ-ንፋስ የ3.5 ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያ የሆነችውን የፖርቶ ሪኮን ደሴት የኤሌትሪክ ሃይል ሙሉ በሙሉ እንዳቋረጠ ተነገረ።

ማሪያ ተብሎ የተሰየመው አውሎ-ንፋስ ፖርቶ ሪኮና ቨርጅን ደሴቶች ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

ማሪያ አውሎ-ንፋስ በካረቢያን ዶሚኒካ ደሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰ በኋላ ነበር ወደ ፖርቶ ሪኮና ቨርጅን ደሴቶች የተሻገረው።

አብነር ጎሜዝ የተባሉ የፖርቶ ሪኮ የአደጋ ዝግጁነት ኤጀንሲ ሃላፊ እንዳሉት አንድም ሰው በደሴቷ ላይ የኤሌትሪክ አቅርቦት የለውም።

ማሪያ አውሎ-ንፋስ ፖርቶ ሪኮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

የፖርቶ ሪኮ ገዢ የሆኑት ሪካርዶ ሮሴሎ እንዳረጋገጡት እስካሁን አንድ ግለሰብ በንፋስ ሃይል በሚበር ስብርባሪ ተመቶ ህይወቱ አልፏል።

የማሪያ አውሎ-ንፋስ ሃይል ከምድብ አምስት ወደ ሁለት ዝቅ ቢልም አሁንም የአሜሪካ ግዛት ከሆነችው ፖርቶ ሪኮ ወደ ዶሚኒካን ሪፓፕሊክ አቅጣጫውን አድርጓል።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ማሪያ በፖርቶ ሪኮ ያደረሰው ጉዳት

ለከባድ አውሎ ነፋሶች ማነው ስም የሚያወጣው?

''ከቤታችን መውጣት ስንችል ደሴታችን እንዳልነበር ሆና ነው ምናገኛት" ብለዋል የፖርቶ ሪኮ የአደጋ ዝግጁነት ኤጀንሲ ሃላፊ የሆኑት ጎሜዝ።

ከዚህ በተጨማሪም እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዘናብ የመሬት መንሸራተት ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት ስለነበረ ነዋሪዎች ለተወሰኑ ሰዓታት በቤት ውስት እንዲቆዩ ማስጠንቀቂያ ተላልፎ ነበር።