የስደተኞች ቀውስ፡ በሊቢያ ዳርቻዎች ብዙዎች እንደሰጠሙ ስጋት አለ

የአደጋ ጊዜ ጃኬት Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ከሰጠመው ጀልባ የመጣ እንደሆነ የታመነበት የአደጋ ጊዜ ጃኬት በሊቢያ የባህር ዳርቻ ተገኝቷል

በሊቢያ ዳርቻ ስደተኞችን የጫነ ጀልባ ነዳጅ አልቆበት በመስጠሙ ቢያንስ 50 ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰግቷል።

በምዕራብ ሊቢያ ከምትገኘው ሳብራታ የተነሳው ጀልባ ቢያንስ 100 ሰዎችን ጭኖ እንደነበር የአካባቢው ኃላፊዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጀልባው ከመስጠሙ በፊት በገጠመው ችግር ለቀናት ያለቁጥጥር መጓዙና በመጨረሻም በዙዋራ ከተማ አቅራቢያ ባለፈው ረቡዕ መታየቱ ተዘግቧል።

እስካሁን 35 ሰዎች ከአደጋው ሲተርፉ 8 አስክሬኖችም መገኘታቸውን ኃላፊዎቹ ገልጸዋል።

የሊቢያ የባህር ኃይል ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት የተረፉት ተጓዞች ሁሉም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት እንደሚለው በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት 100,000 ስደተኞች ሚዲትራኒያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያን ሲሻገሩ ከ2400 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በመንገድ ላይ ሞተዋል።

በሊቢያ የሚያዙ ስደተኞች ደግሞ በትሪፖሊ ብዙዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ወደታጨቁባቸው ማቆያዎች ይወሰዳሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ