ኪም ጆንግ ኡን ፡ 'እብዱ' ትራምፕ የኑክሊዬር መርሃ ግብርን አስፈላጊነት አሳይቶኛል

ፕሬዝዳንት ኪም Image copyright Reuters/KCNA

'እብዱ' የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለሰሜን ኮሪያ የኑክሊዬር ጦር መሳሪያ ማበልጸጌ ትክክል እንደሆነ አሳምነውኛል ሲሉ ኪም ጆንግ ኡን ተናግረዋል።

በመንግስት መገናኛ ብዙኃን ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ በሰጡት መግለጫ ትራምፕ በተባበሩት መንግስታት ላይ ያደረጉት ንግግር 'ትልቅ ዋጋ ያስከፍላቸዋል' ብለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባለፈው ማክሰኞ ሃገራቸው ራሷን ለመከላከል በመገደዷ ሰሜን ኮሪያን 'ሙሉ በሙሉ ልታጠፋት ትችላለች' የሚል ንግግር አሰምተው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ ኪምን 'ራሱን የማጥፋት ተልእኮ ላይ ያለ ባለሮኬቱ ሰው'' ሲሉም ተሳልቀውባቸው ነበር።

ሁለቱ ሃገራት ከቅርብ ወራት ወዲህ ጥላቻ የተሞላበትን የቃላት ጦርነት እያዘወተሩ መጥተዋል።

የሰሜን ኮሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም የትራምፕን ንግግር 'ከሚጮህ ውሻ' ጋር አመሳስለውት ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ