ከመርሳት በሽታ ጋር መኖር

የአልዚመር ማህበር እንደሚለው በዓለም ላይ 45 ሚሊዮን ሰዎች የማሰብም ሆነ የማስታወስ ችሎታን በሚያሳጣ በሽታ ተይዘዋል።

አልዚመር ደግሞ የዚህ በሽታ ዋናው መንስኤ ነው።

በሁሉም የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ቢያጠቃም በእድሜ የገፉት ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው።

የፎቶግራፍ ባለሙያዋ ሊያ ቢች በኬንያ ተዘዋውራ በሽታው የሚያሳድረውን ተጽእኖ በካሜራ አስቀርታለች።

ያረጁ እናት እጅ Image copyright Leah Beach
አልጋቸው ላይ የተቀመጡ እናት Image copyright Leah Beach

እኚህ እናት በቤተሰቦቻቸው ቤት አንዲት ክፍል ውስጥ ነው የሚኖሩት። ቤተሰቦቻቸው ሊጠፉ ወይም በመንደር ሲባክኑ ሊውሉ ይችላሉ በሚል ስጋት አንድ ክፍል ውስጥ ይዘጉባቸዋል፤ከማንም ሰው ጋር መነጋገርም ሆነ መገናኘት አይችሉም።

በዚህች አነስተኛዋ የምክዊሮ መንደር ውስጥ እኚህ ፊት ለፊት የሚታዩት አባት ምንም እንኳን እርሳቸው ባያስታውሷቸውም የረጅም ጊዜ ጓደኛቸውን በየቀኑ እየተመላለሱ ይጎበኟቸዋል።

መኝታ ቤት የተቀመጡ ሁለት አዛውንቶች Image copyright Leah Beach
መኝታ ቤት የተቀመጡ ሁለት አዛውንቶች Image copyright Leah Beach
ሻርፕ ያደረጉ እናት Image copyright Leah Beach

የምክዊሮ መንደር በእጅ በሚሰሩ የሰምበሌጥ ስፌቶች ትታወቃለች ፤ እኚህ እናት ደግሞ በሙያው የተካኑ ናቸው፤ በማህብረሰቡ ለሚገኙ ሴቶች ባህላዊውን ጥበብ ያስተማሩትም እርሳቸው ናቸው።

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሰራሩ እየጠፋባቸው ስለሆነ ከዚሀ በኋላ መስራት አለመቻላቸው በጣም ያስጨንቃቸዋል።

ቦርሳ የያዙ እናት Image copyright Leah Beach
አልጋ ላይ የተቀመጡ አባት Image copyright Leah Beach
ውጭ የተቀመጡ አባት Image copyright Leah Beach

እነዚህ ሁለቱም ሰዎች በአካባቢያቸው ታዋቂ ናቸው። አባወራው እንደ መንደሩ መሪ ይታያል፤ ባለቤታቸው ደግሞ እርሳቸውን በመንከባከብ፣በማልበስና በቀን ውሏቸው ነገሮችን እንዲያስታውሱ በማገዝ የድርሻቸውን ይወጣሉ።

ምንም እንኳ ማስታወስ እንደማይችሉ ቢታወቅም አሁንም በአክብሮት ነው የሚስተናገዱት።

አንዲት እናት Image copyright Leah Beach

እኚህ እናት የቀድሞ ባላቸው ሌላ ሴት ካገባ ጊዜ ጀምሮ ሴት ልጆቻቸውን ሲንከባከቡ ቆይተዋል።

ቀሰ በቀስ ግን ትውስታቸውን እያጡ በመሆኑ ለረጅም ጊዜ ትተዋቸው ለመሄድ የሚገደዱት ልጆቻቸው እንዳይጠፉባቸው ይጨነቃሉ።

አንዲት እናት ወደላይ የሚያዩ Image copyright Leah Beach

እኚህ ደግሞ ከመንደሩ ሴቶች በእድሜ የጠኑት ናቸው ፤ የአምስት ትውልድ ቤተሰባቸው እርሳቸውን ይንከባከባል።

ቀጥሎ የሚታዩት አዛውንት ደግሞ ሙሉ ህይወታቸውን በመንደሩ አሳ በማጥመድ የሚተዳደሩ የቤተሰባቸው ዋነኛ የገቢ ምንጭ ነበሩ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አሳ እንዴት እንደሚጠመድ ማስታወስ ባለመቻላቸው ቤት ውስጥ ለመዋል ተገደዋል።

የሚከታተላቸው ሰው ከሌለ ደግሞ ይጠፋሉ፤ ለቤተሰባቸው ሸክም ከመሆን ሞትን እንደሚመርጡ ይናግራሉ።

አዛውንት አባት Image copyright Leah Beach
ሻርፕ ያደረጉ እናት Image copyright Leah Beach

እኚህ እናት በእህታቸው ክብካቤ ይደረግላቸዋል። በውሃ ውስጥ የሚበቅል እጽወትን ይሰበስቡ ነበር።

አሁን ግን እንዲት እንደሚሰበሰብ አያስታውሱም። ባህር ላይ አንዳች ቢገጥማቸው ቤተሰባቸው ቤት እንዲቀመጡ እንዳያስገድዳቸውም ይሰጋሉ።

ሁሉም ፎቶግራፎች በሊያ ቢች የተነሱ ናቸው። የአልዛይመር ማህበር የዓለማቀፉ አልዛይመርና የዲሜንሺያ ጥምረት መስራች አባል ነው።