በትላንትናው ዕለት የኡጋንዳ ፓርላማ ተበጥብጦ ውሏል

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
የኡጋንዳ ፓርላማ አባላት እርስ በርስ ተደባደቡ

ኡጋንዳውያን የፓርላማ አባላት በትላንትናው ዕለት የፕሬዝደንታቸውን የስልጣን ዘመን ዕድሜ ገደብ ለመወሰን ተሰብስበው ነበር።

በዚህ ሂደት ላይ እያሉ በመካከላቸው ሽጉጥ የያዘ ሰው እንዳለ በተሰማ ጭምጭምታ በፓርላማ አባላቱ መካከል ግብግብ ይጀመራል።

የፓርላማው አፈ-ጉባዔም ሽጉጥ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ፍተሻ እንዲካሄድ ያዛሉ። ነገር ግን ሽጉጥ አለመገኘቱን የኡጋንዳ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የፕሬዝደንትነት ዕድሜ በኡጋንዳ አጨቃጫቂ የሆነበት ምክንያት የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ዩዌሪ ሙሴቬኒ አሁን ላይ ዕድሜያቸው 73 ሲሆን የሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ግን አንድ ፕሬዝደንት ከ75 ዓመት በላይ እንዲያገልግል አይፈቅድም።

የሀገሪቱ ሕገ-መንግስት ፕሬዝደንቱን በ2021 ለሚደረገው ምርጫ ለስድስተኛ ጊዜ እንዳይወዳደሩ ያግዳቸዋል።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ ፕሬዝደንት ሙሴቬኒ እ.አ.አ. ከ1986 ጀምሮእ በስልጣን የቆዩ ሲሆን በፕሬስደንትነት ግን ከ1996 ጀምሮ እያገለገሉ ይገኛሉ።

የኡጋንዳ ገዢው ፓርቲ 'ናሽናል ሬዚዝስታንስ ሙቭመንት' ሕገ-መንግስቱን በመቀየር ሙሴቬኒ ዳግም ለፕሬዝደንትነት ምርጫ ብቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እየጣረ ይገኛል።

እ.አ.አ. በ2005 ዓ.ም. ሕገ-መንግስቱ ላይ ሰፍሮ የነበረውን አንድ ግለሰብ ከሁለት ጊዜ በላይ በፕሬዝደንትነት እንዳያገለግል የሚያግደውን አንቀፅ በመሻር ሙሴቬኒ ዳግም እንዲሚረጡ መደረጉ ይታወሳል።

ግብግቡ ተፈጠረው የፓርላማው አፈ-ጉባዔ አንቀፁን ለፓርላማው አባላት ለውይይት እንዲቀርብ ከወሰኑ በኋላ ነው። የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ግርግሩ ለ20 ደቂቃዎች ያህል የቆየ ነበር።

ከፓርላማ ስብሰባው በፊት በዋና ከተማዋ ካምፓላ ተቃዋሚዎች ሀሳቡን በመቃወም ሰልፍ ወጥተው ነበር። አንድ ታዋቂ የተቀዋሚ አባልም ሰልፉ እንዲካሄድ ቀሰቅሷል በሚል መታሰሩም ተሰምቷል።

ባለፈው ሳምንት በነበረው ጉባዔ ተቃዋሚዎች በጭብጨባ፣ በፉጨት እና በጩኸት በጉዳዩ ላይ ለመምከር የተሰበሰበውን ፓርላማ እንዲበተን ማደረጋቸው የሚታወስ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች