የህንድ አርሶ አደሮች የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት አያስፈልገንም አሉ

A farmers in Nalgonda Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አርሶ አደሮቹ የኤሌክትሪክ ኃይሉ የከርሰ ምድር ውሃን ለማጥፋት ተግባር እየዋለ ነው ይላሉ።

ቴላንጋና በተሸኘው ደቡባዊው የህንድ ግዛት የሚኖሩ አርሶቶ አደሮች በኤሌክትሪክ መኖር ምክንያት የከርሰ ምድር ውሃ ያልቃል በሚል ስጋት የአካባቢው ባለስልጣናት አገልግሎቱን እንዲያቋርጡ ጠየቁ።

"የውሃ መሳቢያዎች ውሃ ከከርሰ ምድር ስለሚስቡ ጉድጓዶች ሊደርቁ ይችላሉ" ሲሉ የራም አንጂሬዲይ የተባሉ አርሶ አደር ለቢቢበሲ ተናግረዋል።

የህንድ መንግስት ባለፈው ሰኔ በግዛቱ የሚገኙ ሶስት አካባቢዎች የ 24 ሰዓት የመብራት አገልግሎት እንደሚያገኙ አስታውቆ ነበር።

አርሶ አደሮቹ ግን የተፈቀደላቸው የኤሌክትሪክ ኃይል በዘጠኝ ሰዓታት እንዲገደብ ይፈልጋሉ።

ብዙዎች የ 24 ሰዓታት የኤሌክትሪክ ኃይል በሚፈልጉባት ህንድ የአርሶ አደሮቹ ጥያቄ አስጋራሚ ነው ተብሏል።

ብዙ አርሶ አደሮች መብራት በሚመጣበት ወቅት እራሱ ውሃ የሚቀዳላቸውን ውሃ መሳቢያ በቀዬአቸው ተክለዋል።

አጭር የምስል መግለጫ "የውሃ መሳቢያዎች ጉድጓዶች እንዲደርቁ እያደረጉ ነው" ይላል አንጂሬዲይ።

ሆኖም የውሃ መሳቢያው በራሱ ውሃ መሳብ እንዲያቆም ቢያደርጉትም ሁሉም አርሶ አደሮች ይህንን ሊያደርጉ ስለማይችሉ የከርሰ ምድር ውሃ ሊያልቅ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

ለድርቅ የተጋለጠ ነው በሚባልበት በዚህ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ከወዲሁ እየቀነሰ መሆኑ ይነገራል።

"ሙሉ ለሙሉ በጉድጓድ ውሃ ላይ ጥገኛ በመሆናችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ትልቅ ፈተና ደቅኖብናል" ይላሉ አንጂሬዲይ።

ይህን መሰሉን ጥያቄዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ከሚኖሩባቸው ሦስት ግዛቶች እንደቀረበላቸው ባለስልጣናት ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ባለስልጣናቱ የኤልክትሪክ ኃይሉን እንደሚያቋርጡ በይፋ ባይገልጹም አገልግሎቱን ወደ 12 ሰዓታት ዝቅ ማድረጋቸውን አንድ ባለስልጣን ተናግረዋል።