ላውሮ የስድስተኛውን ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች እንዲህ ገምቷል

ለሊቨርፑል ከ200 በላይ ጨዋታዎችን ያደረገው ማርክ ላውረንሰን የዚህን ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ገምቷል።

ከዚህ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች መካከል ያለፈው ዓመት ባለድል ቼልሲ ዘንድሮ ያለሽንፈት ሊጉን የሚመራው ማንቸስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ይጠበቃል።

ላውሮ ሲቲ ያለምንም ነጥብ ከስታምፎርድ ብሪጅ አይመለስም ብሎ ያምናል።

"ቼልሲ ባለፈው ዓመት ማንቸስተር ሲቲን በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ በማሸነፍ ስድስት ነጥብ አግኝቷል። ሲያሸንፍ ግን የተወሰነ ዕድልም አለበት። ይህ ግን በዚህ ዓመት ይደገማል ብዬ አልጠበቅም" ይላል ላውሮ።

በዚህ ግምት ይስማማሉ?

በዚህ ሳምንት ላውሮ ግምቱን የሚሰጠው ከታዋቂው አሜሪካዊ ጊታር ተጫዋች ክሪስ ሺፍሌት ጋር በመሆን ነው። ሺፍሌት የአርሴናል ቀንደኛ ደጋፊ ነው።

Image copyright Rex Features
አጭር የምስል መግለጫ ታዋቂው አሜሪካዊ ጊታር ተጫዋች ክሪስ ሺፍሌት (ቀኝ) እንደሚለው ከባንዱ አባለት ማናቸውም እግር ኳስ አይከታተሉም

የላውሮ ግምት

ቅዳሜ

Image copyright BBC Sport

ሃደርስፊልድ ከቶተንሃም

ሃደርስፊልዶች እስካሁን በሜዳቸው ሽንፈት አላስተናገዱም። ሆኖም ይህ የሚቀጥል አይመስለኝም።

ቶተንሃሞች ከሜዳው ውጭ ሲጫወቱ ጠንካራ አቋም አላቸው። በሰባት ቀን ውስጥ ከሜዳ ውጭ ሶስተኛ ጨዋታቸውን ያሸንፋሉ ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 0-2

የሺፍሌት ግምት: ቶተንሃም ይህን ጨዋታ ያሸንፋል። 0-2

Image copyright BBC Sport

ርንማውዝ ከሌስተር

ጄሚ ቫርዲን ከሌይስተር ብናስወጣው ቡድኑ በማጥቃቱ በኩል መካከለኛ ቡድን ሊመስል ይችላል።

ቦርንማውዝ ተመሳሳይ ቢሆንም በሜዳው መጫወቱ የተሻለ ዕድል ይሰጠዋል።

የላውሮ ግምት: 2-1

የሺፍሌት ግምት: 3-1

Image copyright BBC Sport

ማንቸስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ

ባለፈው ሳምንት ለ44 ደቂቃም ቢሆን ክሪስታል ፓላሶች ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ጥሩ ፉክክር አድርገዋል።

ጨዋታው ሲጠናቀቅ ግን በሰፊ የጎል ልዩነት ነው የተሸነፉት። አሁንም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ነው የሚጠብቃቸው።

ማንቸስተር ዩናይትዶች በተለይ ደግሞ በአጥቂያቸው ሮሜሉ ሉካኩ በመታገዝ ውጤታማ በመሆን ላይ ይገኛሉ።

የላውሮ ግምት: 3-0

የሺፍሌት ግምት: 4-0

Image copyright BBC Sport

ስቶክ ከሳውዝሃምፕተን

ስቶኮች ዘንድሮ ሁለት ጥሩ ውጤቶችን ቢያስመዘግቡም በቼልሲ ግን በሰፊ ጎል ልዩነት ተሸንፈዋል።

ሳውዝሃምፕተኖች ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ጥሩ ቢጫወቱም ስቶክ ጠንክሮ ይቀርባል ብዬ አስባለሁ።

የላውሮ ግምት: 2-1

የሺፍሌት ግምት: ስቶክ በሜዳው ውጤታማ ይሆናል ብዬ አስባለሁ። 2-1

Image copyright BBC Sport

ዌስት ብሮም ከዋትፎርድ

ዌስት ብሮሞች ብዙ ጎል ባያስቆጥሩም መረባቸውንም በተደጋጋሚ አያስደፍሩም።

ዋትፎርዶች በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጭ ያደረጓቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ አስደምመውኛል።

ይህን ጨዋታ ዌስት ብሮም በጠባብ ጎል ልዩነት የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት: 1-0

የሺፍሌት ግምት: 0-0

Image copyright BBC Sport

ዌስት ሃም ከስዋንሲ

ዌስት ሃሞች አጀማመራቸው ጥሩ ባይሆንም አሁን እየተነቃቁ ነው።

ስዋንሲዎች ወደፊት ሲሄዱና ሲከላከሉ ጥሩ አይደሉም።

የላውሮ ግምት: 2-0

የሺፍሌት ግምት: ዌስትሃሞችም ሆኑ ስዋንሲዎች ጥሩ እየተንቀሳቀሱ አይደለም። 1-0

Image copyright BBC Sport

ቼልሲ ከማንቸስተር ሲቲ

ቼልሲዎች የማንቸስተር ሲቲን ያህል ጎል እያገቡ አይደለም።

አልቫሮ ሞራታ የሌሎቹን አጥቂዎች ያህል ባይወራለትም ውጤታማ እየሆነ ይገኛል።

ሁለቱም ቡድኖች ተቀራራቢ ፉክክር ያደርጋሉ።

የላውሮ ግምት: 1-1

የሺፍሌት ግምት: ማንቸስትር ሲቲ እያሳየ ከሚገኘው አቋም አንጻር በሰፊ ጎል ልዩነት የሚያሸንፍ ይመስለኛል። 2-5

እሁድ

Image copyright BBC Sport

አርሴናል ከብራይተን

ብራይተኖች ባለፈው ሳምንት ኒውካስትልን ማሸነፋቸው ትልቅ ውጤት ቢሆንም ኤምሬትስ ላይ ግን ነጥብ የሚያገኙ አይመስለኝም።

የላውሮ ግምት: 2-0

የሺፍሌት ግምት: አርሴናሎች በሰፊ ጎል ልዩነት ያሸንፋሉ። 4-0

Image copyright BBC Sport

ኤቨርተን ከበርንሌይ

ኡማር ኒያሴ ባለፈው ሳምንት ሶስት ነጥብ ካስገኘላቸው በኋላ ሮናልድ ኩማን ማንን የፊት አጥቂ አድርገው እንደሚመርጡ ማየት ያጓጓል።

በርንሌይዎች እስካሁን ከሜዳው ውጭ ባይሸነፉም ከኤቨርተን ጋር ግን የሚያሳኩት አይመስልም።

የላውሮ ግምት: 2-1

የሺፍሌት ግምት: ኤቨርተን ማሸነፍ ስለሚፈልጉ ለእነሱ ግምቴን አስቀምጣለሁ። 2-0

Image copyright BBC Sport

ኒውካስል ከሊቨርፑል

ኒውካስሎች በፕሪሚየር ሊጉ ለመቆየት ብዙ መስራት ይጠበቅባቸዋል።

የቆሙ ኳሶችን በመጠቀም በኩል ኒውካስሎች ጠንካሮች ሲሆኑ ሊቨርፑሎች ደግሞ በዚህ ረገድ ደካማ ናቸው። ሆኖም ቀያዮቹ መረባቸውን የሚያስደፍሩ አይመስሉም።

ሊቨርፑሎች ሶስት ነጥቦችን የሚያገኙበት ጨዋታ ይመስለኛል።

የላውሮ ግምት: 0-2

የሺፍሌት ግምት: 2-3

ተያያዥ ርዕሶች