የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ለሮሂንጂያ ሙስሊሞች አልደረሰላቸውም ተባለ

ሮሂንጂያዎች ወደ ባንግላዴሽ ይሸሻሉ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከ500 ሺ በላይ ሮሂንጂያዎች ከማይናማር ሸሽተዋል

በሚያንማር የሚገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አመራሮች የሮሂንጂያን ጉዳይ መንግሥት እንዳይመለከተው ማድረጉን የቢቢሲ ምርመራ ይፋ አደረገ።

የድርጅቱ የቀድሞ አመራር እንዳሉት በሚያንማር የሚገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊ የሰብዓዊ መብት ተማጓቾች ውጥረት ወዳለበት የሮሂንጂያ አካባቢ እንዳይጎበኙ አድርገዋል።

500 ሺህ የሚሆኑ ሮሂንጂያዎች በመከላከያ ሠራዊት የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት ሸሽተው አብዛኛዎቹ ባንግላዲሽ ደርሰዋል።

በሚያንማር የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ግን የቢቢሲን ዘገባ አስተባብሏል።

Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ በሰሜናዊ ራክሂን የሚገኙ ጥቂት የሮሂንጂያ መንደሮች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል።

ሮሂንጂያዎች ወደ ባንግላዲሽ መሰደዳቸውን ተከትሎ ድርጅቱ ድጋፍ በማድረግ ቀዳሚ ነው። ከድጋፉ በተጨማሪም የበርማ ባለስልጣናትንም ሲኮንን ተስተውሏል።

ይሁን እንጂ የአሁኑ ችግር ከመከሰቱ ከአራት ዓመት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃገሪቱ ቡድን መሪ ካናዳዊቷ ሬናታ ሎክ-ድሳሊየን፡

  • የሰብዓዊ መብት ቡድን አባላት ወደ ሮሂንጂያ አካባቢዎች እንዳይሄዱ ጥረት አድርገዋል
  • በጉዳዩ ላይ ቅስቀሳ እንዳይካሄድ ጥረዋል
  • የዘር ጭፍጨፋ ሊካሄድ ይችላል ሲሉ ያስጠነቀቁ ባልደረቦችን እንዲገለሉ አድርገዋል
Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሮሂንጂያዎች ወደ ባንግላዴሽ ይሸሻሉ።

ውስብስብና ግጭት

እ.አ.አ በ 2012 በሮሂንጂያ ሙስሊሞችና በራክሂን ቡዲስቶች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከ 100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሲሞቱ፤ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የሮሂንጂያ ሙስሊሞች ደግሞ መጨረሻቸው በመጠለያ ጣቢያዎች ሆኖዋል።

ከዚያ በኋላ ደግሞ ግጭቶች በየጊዜው የተከሰቱ ሲሆን የሮሂንጂያ ወታደራዊ ቡድንም ተቋቁሟል። ለተጎጂዎች ድጋፍ እንዳይደርስ ደግሞ በራክሂን ቡዲስቶች የተለያዩ ሥራዎች ተሠርተዋል።

ይህም የሮሂንጂያዎች መሠረታዊ እርዳታ እንዳየገኙ እንቅፋት ሆኗል።

Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የባንግላዲሽ ወታደሮች ለሮሂንጂያ ህፃናት ምግብ ሲያከፋፍሉ

የሮሂንጂያን ችግር ወይም ዘር ጭፍጨፋ እንደሚመጣ በዋና ዋና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባዎች ላይ መናገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደረሰ ሲሉ አንድ ድርጅቱ የቀድሞ አመራር ተናግረዋል።

በ2015 ድርጅቱ የአካባቢውን ችግር ለመፍታት ያቀደበት መንገድ ለቢቢሲ እነዳጤነው የችግር አፈታቱ መንገድ ብዙ ክፍተት ያለበት ነው።

"የሰብዓዊ መብት ችግሩን የሚቀረፈው ኢኮኖሚ ዕድገት በማምጣት ነው በሚል ታልፏል።"

ይህንን አስመልክቶ ድሳሊየን ከቢቢሲ ለቀረቡላቸው ጥኣቄዎች ምላሽ ለመስተት ፈቃደኛ አልሆኑም።