የሳምንቱ ቡድን ውስጥ ኬይን፣ ኩቲንሆ፣ ደብሩይንና ራሽፎርድ ተካተዋል

የቀድሞ ማንችስተር ዩናይትድና የቶተንሃም ተጫዋች የነበረው የጋርስ ክሩክስ የሳምንቱ ምርጥ ቡድን!

በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲዎች ቸልሲን በስታንፎርድ ብሪጅ ካሸነፉ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ አናት ላይ መቆየት ችለዋል።

በጋርዝ ክሩክስ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ 11 ውስጥ ኬይን፣ ኩቲንሆ፣ ደብሩይንና ራሽፎርድ ተካተዋል።

  • የሳምንቱ ምርጥ ቡድን

ግብ ጠባቂ - ኤደርሰን (ማንችስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ኤደርሰን በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ሌላ ተጨማሪ ተከላካይ እንዳሰለፈ ነው የሚታሰበኝ። ከቤኔፊካ በ35 ሚሊየን ፓወንድ ወደ ሲቲ የመጣው ይህ ብራዚላዊ ግብ ጠባቂ ከቸልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ሃላፊነቱን በሚገባ ተወጥቷል።

ኤደርሰን ጨዋታውን የጀመረበት መንገድ ዓይን የሚይዝ ነበር። የአዝብሉኬይታን ኳስ ያዳነበት ሁኔታም እጅግ አስደናቂ ነበር። በፍጥነት ኳስ ለቡድን አጋሮቹ ያሳልፍ ነበር። ኤደርሰን ሲቲ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ከፍተኛ ድርሻ ነበርው።

ተከላካይ- ማያ ዮሺዳ (ሳውዝሃፕተን)

Image copyright Getty Images

ማያ ዮሺዳ ጎል ከማስቆጠሩም በላይ 75 ኳሶችን ማቀበል ችሏል። ምንም እንኳ ሳውዝሃፕተን በስቶክ ቢሸነፍም ማያ ባስቆጠራት ጎል ሳውዝሃፕተን አቻ መሆን ችሎ ነበር።

ተከላካይ- ጀምስ ታርኮዊስኪ (በርንሌይ)

Image copyright Getty Images

ጀምስ ታርኮዊስኪ የፕሪሚየር ሊጉ የሳምንቱ ምርጥ 11 ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መካተት ችሏል። ከኤቨርተን ጋር በነበራቸው ጨዋታ ጀምስ ያሳየው ብቃት እጅግ አስገራሚ ነበር።

ተከላካይ- ሞንርያል (አርሰናል)

Image copyright Getty Images

ናቾ ሞንሪያል ከበርካታ ጎል አልባ የፕሪሚያር ሊግ ጨዋታዎች በኋላ አርሴናል ከብራይተን ጋር በነበረው ጨዋታ የመክፈቻ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ሞንሪያልን ከቀደሙት የአርሴናል ተከላካዮች ከእነ ዊሊያም ጋላስ፣ አሽሊ ኮልና ሶል ካምቤል ጋር ማነፃፀር ከባድ ቢሆንብኝም ሞንሪያል በአርሴናል ቤት ውስጥ ጥሩ የሚባል ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።

የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርገው ሞንሪያል፣ የአርሰን ቬንገርን ሙሉ እምነት ያገኘ ይመስላል።

አማካይ- ኬይራን ትሪቲየር (ቶተነሃም)

Image copyright Getty Images

ኬይራንን ዓይኔ ውስጥ የገባው የበርንሌይ ተጫዋች ሆኖ በዋይት ሀርት ሌን ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታ ነው።

ይህ ተጫዋች ወደ ቶተንሃም ሲመጣ የሚጫወትበት ቦታ ብዙ ፉክክር የነበረበት ቢሆንም ባለፉት በርካታ ጨዋታዎች ውስጥ በቡድኑ የቋሚ አሰላለፍ ቦታን ማግኘት ችሏል።

ሃሪ ኬይን ያስቆጠራት ጎል በኬይራን ጥረት የተገኘች ነበረች።

አማካይ- ፊሊፕ ኩቲ (ሊቨርፑል)

Image copyright Getty Images

ወደ ፕሪሚር ሊጉ ከመጣ ጀምሮ ከየትኛውም ተጫዋች በላይ ኩቲንሆ ከሳጥኑ ውጪ 17 ጎሎችን ማስቆተር ችሏል።

ከኒውካስል ጋር በነበራቸው ጨዋታ ኩቲንሆ አስገራሚ አቋሙን አሳይቷል።

ምንም አንኳ ኩቲንሆ ሊቨርፑልን ቀዳሚ የሚያደርገውን ጎል ቢያስቆጥርም ሊቨርፑል ከኒውካስል አቻ ተለያይቷል።

አማካይ- ማርዋን ፌላኒ (ማንችስተር ዩናይትድ)

Image copyright Getty Images

በዘንድሮ ሊግ ፌላይኒ ለማንችስተር ዩናይትድ ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

የቀድሞ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ከኤቨርተን በ2013 ካስፈረሙት በኋላ ቤልጅየማዊው ፌላይኒ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።

ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ፌላይኒ ባሳየው አቋም አስደምሞኝ ነበር።

የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ስሙን እያነሱ ሲያዜሙም ነበር።

አማካይ- ኬቪይን (ማንችስተር ሲቲ)

Image copyright Getty Images

ባለፉት አራት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዴ ብሩይን አንድ ጎል ሲያስቆጥር ሶስት ጎል የሆኑ ኳሶችን አቀብሏል።

በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ዴ ብሩይን በቸልሲ ላይ ያስቆጠረው ድንቅ ጎል ተፅዕኖ ፈጣሪነቱን ያረጋገጠ ነበር።

የሰሞኑ የሲቲ ብቃት በፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ ላይ በእኩል ነጥብ የሚገኙት ማንችስተር ዩንይትዶችን ማስጨነቁ አይቀርም።

አማካይ- ቤን ዴቪስ (ቶተሃም)

Image copyright Getty Images

ቤን ዴቪስ ባለፉት ዘጠኝ የፕሪሚያር ሊግ ጨዋታዎች ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ አራት ጎል የሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።

ቶተንሃም እያሳየ ላለው ብቃት ቤን ዴቪስ ትልቅ ድርሻ አለው።

አጥቂ- ማርከስ ራሽፎርድ (ማንችስተር ዩናይትድ)

Image copyright Getty Images

ማርከስ ራሽፎርድ በዩናይትድ ቆይታው ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሁለት ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።

ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበው ጨዋታ ራሽፎርድ የፓላሶችን ተከላከይ መስመር ተጫዋቾች ሲያስጨንቅ ውሏል።

አጥቂ- ሪ ኬን (ቶተሃም)

Image copyright Getty Images

አሁን ሃሪ ኬን የሚገኘበትን አቋም ሳስብ ከጥቂት ዓመታት በፊት የቶተንሃም የነበረውን ጋርዝ ቤልን ያስታውሰኛል።

ባለፈው ቅዳሜ ከሃደርስፊልድ ጋር በነበረው ጨዋታ ኬን አስገራሚ ብቃት አሳይቷል።