ፖሊስ የላስ ቬጋሱ ታጣቂ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ጥቃቱ እንዴት ተፈፀመ?

ፖሊስ 59 ሰዎችን ለሞት፣ ከ500 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ለጉዳት የዳረገው ሰቴፈን ፓዶክ ጥቃቱን ለመፈፀም ምን እንዳነሳሳው እያጣራ ነው ።

የ64 ዓመት ታጣቂ ማንዳላይ ቤይ ከተሰኘ ሆቴል 32ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በአቅራቢያው ይካሄድ በነበረና 22 ሺህ ሰዎች በታደሙበት የሙዚቃ ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ነው ጉዳቱን ያደረሰው።

በነበረበት የሆቴል ክፍል ውስጥ ፖሊስ 23 የጦር መሳሪያዎችን ያገኘ ሲሆን ከ19 በላይ ደግሞ በመኖሪያ ቤቱ ተገኝቷል።

ፖሊስ እንዳለው እሳካሁን ለጥቃቱ ግልፅ የሆነ ምክንያት አልተገኘም።

ምንም እንኳ አይኤስ አይኤስ (ISIS) እያለ ራሱን የሚጠራው የሽብር ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ ቢልም መርማሪዎች እሳካሁን ባለን መረጃ ጥቃቱ ከዓለም አቀፍ የሽብር ቡድን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል።

ጥቂት መርማሪዎች ስቴፈን ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ ነበር ይላሉ።

ዶናልድ ትራምፕ ድርጊቱን ''እኩይ'' ሲሉ ኮንነውታል።